ባለንበት የመረጃ ዘመን፤ ሳይበር (ለምሳሌ ኢንተርኔት) ለፍትህ፣ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ትግል ከሚደረግባቸው አውድማዎች አንዱ ሆኗል። ለሰሜን አፍሪቃና መካከለኛ ምሥራቅ ህዝባዊ አብዮቶች ኢንተርኔት ስለተጫወተው ሚና ብዙ የተባለ ስለሆነ እዚህ ላይ ደግሞ ማንሳት አያስፈልግም። መረሳት የሌለበት ሃቅ ግን አምባገነኖችም ይህንን ስለሚያውቁ እነሱም የሚዘጋጁበት መሆኑ ነው። የዘመናችን አምባገነን መንግሥታት የምድር፣ የባህርና የአየር ኃይሎቻቸውን ከማፈርጠም ጎን ለጎን “የሳይበር ኃይላቸውን” ማጎልበት […]

ወያኔ ብሶት የወለደው የህዝብ ልጅ ነበር። አሁን ያ የህዝብ ብሶት የወለደው ድርጅት ሙቶ በቀበሩ ላይም መለስ ዜናዊ የሚባል ጣኦት ቁሟል።ኢትዮጵያዊያንም ለዚህ ጣኦት መስዋእት ሁነው ቀርበውለታል። ጣኦቱም በፈለገው መንገድ የቀረበለትን መስዋእት እየበለተ ምሱን እየወሰደ ነው። ይህ ጣኦት ይሁን ያለው እየሆነ አይሁን ያለው ደግሞ ሳይሆን እየቀረ እነሆ ሁለት አስርተ ዓመታት ተቆጠረ። ይህ ክፉ ጣዖት አማራና ኤምፔሪያሊዝም የትግራይ […]

ወያኔ በትግራይ ህዝብ ሥም ባቋቋመውና ለጥቂት የህወሃት ባለሥልጣኖች እንደግል ንብረት እያገለገለ ያለው የ ኤፈርት ኩባንያ  ስራ አስኪያጅ አባዲ ዘሙ ከሥራ አስኪያጅነቱ ተነስቶ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ  በዘረኛው ቡድን ቁንጮ መለስ ዜናዊ ባለቤት  አዜብ መስፍን እጅ  መውደቁ ተዘገበ። አዲስ ቮይስ በመባል የሚታወቀው የመረጃ አውታር እንደዘገበው፤ በህወሓት ውስጥ ረጅም ዓመታት ቁልፍ ቦታዎችን ይዞ ሲያገለግል የቆየውና የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ […]

የከተማ ቦታን በሊዝ ለማስያዝ  በሚል ድንጋጌ የወያኔ ምክር ቤት በቅርቡ ያወጣው የከተማ ቦታ አዋጅ የዜጎችን ነባር ይዞታ ለመቀማት የታሰበና ባለንበርቶች ቤታቸውን ለልጅ ልጆቻቸው ለማውረስ ያላቸውን ህጋዊ መብት የሚያሳጣ እንደሆነ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የህግ ባለሙያዎች ገልጸዋል። ኢ-ፍትሃዊ የነበረውን የአገራችንን የመሬት ይዞታ ስርዓት በ1967ቱ ስርነቀል የመሬት ላራሹ አዋጅ የለወጠው ደርግ ፤ የከተማ ቦታን በምሪት የመጠቀም መብት ሰጥቶ […]

የጀርመን ፓርላማ ምክር ቤት አባላት በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ 09.11.2011 በሰጡት መግለጫ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የረጂም ጊዜ ግንኙነት በአገሪቱ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያየን ዝም እንድንል የሚያደርገን አይደለም አሉ። በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ጉብኝት ያደረጉት የሊበራል ፓርቲ ተወካዩዋ ወይዘሮ ማርቲና ሹስተር  በጉብኝታቸው ወቅት ያስተዋሉትን እውነታ ሲገልጹ “ህግ ይፈቅድልኛል እያሉ አንድን ሰው […]

ዕሁድ ጥቅምት 26 ቀን ተከብሮ የዋለውን የኢድ-አልፈጥርን በዓል በቤልጂዬም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አንድ ላይ በመሰባሰብ በደማቅ ሁኔታ ማክበራቸውን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከስፍራው በላከልን ሪፖርት ገለጸ። በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በየአመቱ በደማቅ ሁኔታ በሚከበረው በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ሥነሥርዓት ላይ የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መካከል እልቂት ሊያስነሳ የሚችል ክፍፍል ሆን ብሎ እየፈጠረ መሆኑን በድምጽና በቪዲዮ ማስረጃ የተደገፈ […]

ኢትዮጵያዊያንን በሰበብ አስባቡ በመከፋፈልና በማበጣበጥ ራሱን ስልጣን ላይ የማቆየት አባዜ የተጠናወተው ከፋፋዩ የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ማጋጨቱን እንደቀጠለ ሲሆን ግጭቱን ወደ ከፋ ደረጃ ለማድረስ “አህባሽ” ለተባለው ቡድን ወታደራዊ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ከአገር ውስጥ አልፎ በውጪ አገር የሚኖሩትንም ሙስሊም ህብረተሰብ  እጅግ እያሳሰበና እያስቆጣ መሆኑ ተገለጸ። በተለያዩ የአውሮጳ፤ የሰሜን አመሪካና ኤዥያ ከሚኖሩ የሙስሊም ኮሚኒቲዎች ጋር የጋራ ህበረትና […]

ከሁለቱ ስዊድናዊያን ጋራ በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በዋና ወንጀል አድራጊነት የተከሰሱት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) አባላት የሆኑት አብዲወሊ መሐመድ እስማኤል እና ከሊፍ ዐሊ ዳሂር የ17 ዓመት ጽኑ እሥራት ሲፈረድባቸው የስዊድን ሃገር ጋዜጠኞች ክስ ግን በቂ መረጃ አልተገኘም በሚል የቀረበባቸው ክስ ውድቅ መሆኑ ታወቀ፡፡ በእለቱ የፍርድ ቤቱን ታዳሚዎች […]

የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ከሪፖርተሮቹ የደረሰውን መረጃ ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው በውጪ ምንዛሪ በውድ ዋጋ ታትመው ወደ አገር ቤት የገቡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መጻህፍት ለተማሪዎችና መምህራን ከተከፋፈሉ ቦኋላ ነበር ባለሥልጣናቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፉት። ይሁን እንጂ መጽሀፉ ባለፈው መስከረም ወር በሚታደልበት ጊዜ  ተማሪዎች መጽሀፉን ቀድደው ቢገኙ 100 ብር እንደሚቀጡ በመምህራን በኩል ተነግሮአቸው እንደነበር ታውቆአል። የአማራ ክልል ባለስልጣናት ተማሪዎችና መምህራን […]

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ /አንድነት/ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት አላፊ አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 24 ሰዎች በዛሬው ቀን ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ከሰዓት በኋላ የተሰየመው የፌድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛው ወንጀል ችሎት 8 ተከሳሾች ቀርበው የክስ ቻርጅ የተቀበሉ ሲሆን ከተራ ቁጥር 9-24 ያሉት ተከሳሾች በሌሉበት ክሳቸው ተመስርቶአል፡፡ በቁጥር የፍ/ሚ/ፌ/ማ/መ/ቁ 00180/04 ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም. […]

“ኦነግን ሳላውቅ የኦነግ አባል የሆንኩ መሰለኝ” የሚለውን ቃል የተናገሩት ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት በፊት አንድ ዩኒቨርስቲ መምህር ናቸው፡፡ በ1994 ዓ.ም ክረምት ላይ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊና አቶ ተፈራ ዋልዋ የከፍተኛ ትምህረት ተቋም መምህራንን ረዘም ላሉቀናት ያወያዩ ነበር፡፡ አንድ የዩኒቨርስቲ መምህር የኢህአዴግን የፍረጃ ፖሊሲ መግለጽ ሲሉ የተጠቀሙበት ቃል ነበር፡፡ “እኔ የማንም ድርጅት አባል አይደለሁም፡፡” አሉ መምህሩ ሲናገሩ “የማንም […]

1 ጐሣዊ የፖለቲካ አመለካከት መንስዔው ና መዘዙ በኢትዮጵያ 2 ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታና የጐሣ ድርጅቶች 3 የጐሣ ፖለቲካ የወደፊት ዕጣ ችግሮቹና መፍትሄዎች በተሰኙት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በዋሽንግተንና አካባቢው የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ ወገናችንን ለማወያየት 1 ዶ/ር ኣሰፋ ነጋሽን ከአምስተርዳም 2 አቶ ጁሓር መሃመድን ከኒወዮርክ እንዲያወያዩን ጋብዘናቸዋል:: ውይይቱ ለማንኟውም ኢትዮጵያዊ ክፍት ነውና እርሶዎም ይገኙ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል:: ቦታው Best […]

ቀደም ሲል ማብራሪያ የሰጡ የህግ ባለሙያ ኣዋጁን ከአስራ ዘጠኝ ስድሳ ሰባቱ የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት አዋጅ ቀጥሎ የመጣ  ስር ነቀል አዋጅ ሲሉ ገልጠውታል ።

ሚስስ ሃይዲ ሃውታላ፣ የፊንላንድ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር
ሚስስ ሃይዲ ሃውታላ የፊንላንድ የዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ናቸው፡፡ የአውሮፓ ፓርላማ የ

ወንዝን የሚያሻግሩ፣ ጥልፍልፍ መንገዶችን የሚያሸጋግሩ፣ ከፎቅ ወደ ፎቅና ከአውራ መንገድ ወደ አውራ መንገድ የሚወረወሩ ድልድዮች ሠርተናል፤ ተሠርተዋል