የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኛ ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተያዘ
ካለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ ‹‹የልማታዊ ታክስ አስተዳዳር ሠራዊት ለመፍጠር›› በሚል እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2004 ዓ.ም. ድረስ ግምገማ ነክ ሥልጠና ሲያካሂድ የነበረው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ ሥልጠናውን ባጠናቀቀ በማግስቱ ከትናንትና በስቲያ፣ የመሥርያ ቤቱ የክትትልና የጥበቃ ሠራተኛ 150,000 ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተያዘ፡፡