እስክንድር ነጋና አንዷለም አራጌ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
ናትናኤል መኮንን ክፉኛ መደብደቡን ለፍርድ ቤት ገለጸ
Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም. November 10, 2011)፦ ልደታ በሚገኘው በከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ የቀረቡት ስምንት ተከሳሾች መካከል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዷለም አራጎ አንድ ላይ በካቴና ተጠፍረው መቅረባቸውና የአንድት ፓርቲ ምክር ቤት አባል የሆነው ናትናኤል መኮንን በፖሊሶች ክፉኛ መደብደቡን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።