ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ
ኢትዮጵያ ውስጥ በአሸባሪነት ተጠርጥረው የታሰሩት ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ጉዳዩን የሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት በተከሳሾቹ ላይ የቀረበውን የወንጀል ጭብጥ ለመስማት ለህዳር 3 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የተሰኘው ተቃዋሚ ፓርቲ ከፍተኛ የአመራር አባል አቶ አንዷለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ይገኙበታል ። በዛሬው ችሎት ላይ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ታደሰ እንግዳው ተገኝቶ ነበር። ያዳምጡ