ለኢትዮ ኬንያ አገናኝ መንገድ ከ740 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተመድቧል

•    ሁለቱ አገሮች በመንገድ ትራንስፖርትና መሠረተ ልማት ላይ ስምምነት አደረጉ

ኢትዮጵያና ኬንያ የጋራ አገናኝ መንገድ ለመገንባት ባደረጉት ስምምነት መሠረት የአፍሪካ ልማት ባንክ ለሁለቱም አገሮች የ743 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት ተዘጋጅቷል፡፡