ቫይበርና መሰል የስልክ ጥሪ አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ለመጣል ባለሥልጣናት እየመከሩ ነው

ኢትዮ ቴሌኮም Ethio Telecom ና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የኢትዮ ቴሌኮምን መሠረተ ልማት በሚጠቀሙ ቫይበርና መሰል የስልክ ጥሪ አገልግሎቶች VoIP in Ethiopia ላይ ክፍያ ለመጣል፣ ወይም ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም እየመከሩ ነው፡፡

በኢንተርኔት አማካይነት የድምፅና የምሥል ጥሪዎችና መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ አፕሊኬሽኖች፣ ኢትዮ ቴሌኮም ከውጭ ጥሪዎች ማግኘት የሚችለውን ከፍተኛ ገቢ እንዳስቀሩበት ተገልጿል፡፡

እነዚህ የአፕሊኬሽን ዓይነቶች በተለይም በኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች ዘንድ በስፋት የሚታወቁትን ቫይበርና ዋትስአፕ የመሳሰሉትን ለመቆጣጠር፣ ኢትዮ ቴሌኮም ‹‹ፖሊሲ ቻርጅ ኤንድ ኮንትሮል ሲስተም›› የተባለ ቴክኖሎጂ ባለቤት መሆኑን፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዱዓለም አድማሴ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹በአሁኑ ወቅት ክፍያ ለማስከፈልም ሆነ በማጭበርበር ተግባር ላይ የተሰማሩትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ ባለቤት ነን፡፡ ነገር ግን ክፍያ ለመጣል አልወሰንም፤›› ብለዋል፡፡

በእነዚህ አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ለመጣል የብዙ አካላት ውሳኔን ማለትም የኢትዮ ቴሌኮም ቦርድን፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን፣ እንዲሁም የመንግሥትን ውሳኔ እንደሚጠይቅ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከአፕሊኬሽኖቹ ባለቤቶች ጋር መደራደርና ከዓመታዊ የትርፍ ድርሻቸው ክፍያ እንዲፈጽሙ መግባባት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኢትዮ ቴሌኮም በመሆኑ፣ ከአፕሊኬሽን ባለቤቶች ጋር የክፍያ ድርድር ማድረግ ለኢትዮ ቴሌኮም ጠቀሜታዊ ፋይዳው የተሻለ ከሆነ ቀላል አማራጭ እንደሚሆን አቶ አንዱዓለም ጠቁመዋል፡፡

የቫይበርና የመሰል አፕሊኬሽኖች ጉዳይ በየትኛውም አገር አጨቃጫቂ መሆናቸውን የሚገልጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ‹‹ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የወጣበትን የቴሌኮም መሠረተ ልማት ያለባለቤቱ ዕውቅናና ተጠቃሚነት የሚገለገሉና ከፍተኛ ትርፍ ለራሳቸው የሚያካብቱ ናቸው፤›› ብለዋል፡፡

አንዳንድ አገሮች እነዚህን አፕሊኬሽኖች ሙሉ በሙሉ የሚዘጉ ሲሆን፣ ሌሎች አገሮች ደግሞ ክፍያ በመጣል አልያም የትርፍ ድርሻ ድርድር ውስጥ እንደሚገቡ ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሁኔታ ግን ከተጠቀሱት አንዱን ለመምረጥ ሰፊ የትንተና ሥራ መሥራትና ለመንግሥት አቅርቦ ማስወሰንን እንደሚጠይቅ፣ በዚህ ረገድም ገና ውይይት በመካሄድ ላይ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮ ቴሌኮም ‹‹ኢኪዩፕመንት አይደንቲቲ ሬጂስተር›› ማለትም ያልተቀረጡ የሞባይል ስልኮች ወይም የተሰረቁ የሞባይል ስልኮችን ከአገልግሎት ውጪ ማድረግ የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ባለቤት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በመጪው ዓርብ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ከተደረገ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምርም አቶ አንዱዓለም ገልጸዋል፡፡

ይህ ተግባራዊ ከተደረገ ሳይቀረጡ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ስልኮች አገልግሎት መስጠት የማይችሉ ሲሆን፣ ከደንበኞች የተሰረቁ ስልኮችንም ደንበኞች ሲያሳውቁ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

በመጪው ዓርብ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ ውይይት በደንበኞች እጅ ላይ የሚገኙና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ፣ ነገር ግን ያልተቀረጡ ስልኮች ዕጣ ፈንታና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Reporter

11 Comments on “ቫይበርና መሰል የስልክ ጥሪ አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ለመጣል ባለሥልጣናት እየመከሩ ነው”

  1. Its a big resource Ethiopia should take
    a fast action the big Corporates don’t
    mind about Ethiopia . We should protect
    the national interest of our country .
    fast measure is needed .

  2. የተሰጠው ሀሳብ ትክክል ነው ነገር ግን ሳይቀርጥ የሚገቡ ስልኮች ይኖራሉ ለምሳሌ ሴት እህቶቻችን ከአርብ ሀገር ይዘው የሚመጡ ስላሉ ግምት ውስጥ መግባት አለበት ሌላው ግን ቫይበር እና ዋተስአፕ ላይ ያለው በደንብ ቢታሰብበት

  3. Who say those voip applications are free any where? Everyone pay for Internet connection fee in both home or mobile phones. Ethio telecom like charge people twice and provide the shit service to its customers. They charge people every time you make a call for GERD without any consent. The network work system are worst than Somalia. Mass population migrated to other parts of world because of the policy of woyanne and lack job. Now they scum these people and families. Shame

  4. ይህ ማለይ መሰል voip የሚሰጥ app የሉክሰንበርግ ካንፓኒ ያዘጋጀው s.a.r.l ሳይሆን በኢንሳ የተዘጋጅ app የቀድሞውን በመዝጋት ሳንሱር የሚደረገውን እንድንጭን በማድረግ ታሪፍ በማዘጋጀት viber out ሆኖ ነፃ ጥሪን በማሥቀረት ማንኛውን ጥሪ በመቅዳት የማዳመጥ የመሠለል ሥራዎችን ለማከናወን ተዘጋጅተዋል ማርች 31 ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሙከራ እገዳ ማድረጋቸውን ሰምተናል ይህ በዚህ እንዳለ ለጣልያኑ የሥለላ ድርጅት 1ሚሊዬን ዶላር ተከፍሎ እንደነበርም አትርሱ አማራጭ መተላለፊያ ተነል ሥለሚዘጋጅ በንቃት ተጠባበቁ ወያኔን ለማሸነፍ የማንፈነቅለው ድንጋይ የለም ፋሽሥት ወያኔ በህዝብ አንድነትና ትግል ይወገዳል።

    ይህን አፈና ለመቃወም በአውሮፖ የምትገኝ ሀገር ወዳዶች ይህንን የወያኔ ተግባር እንዳይቀበሉት አሥፈላጊውን ግፊት እናድርግ

    ሞት ለወያኔ!!!

    የሳይበር ጦርነት ይፋ ይደረጋል

    ***********************************

  5. ይህንን የህዝብ የነፃ መገናኛ ዘዴ ማወክና ለማ
    ፈን መሞከር ተገቢ አይመስለኝም የመንግስት ተግባርም የህዝብን የነፃ መ ናኛ ዘዴዎች ማፈን ወንጀልም ነው ስለዚህ ከዚህ ተግባራቸው መታቀብ አለባቸው

  6. እንዲህ ከዜጎቹ ጋር ጠብ የገጠመ በዜጎች የቀለለ ኑሮ የሚቀና ሥርዓት እድሜው ይህን ያህል መርዘሙ አስገራሚ ነው ከዚህ በፊት አንድ ባለስልጣን እንዲህ ብሎ ነበር የማይረባ ቤት ሰርተው መንግስት መሰረተ ልማቶችን ዘርግቶ አካባቢውን ካለማ ቡሃላ የቤትና የመሬታቸው ዋጋ ይጨምራል እንግዲህ አስቡት በዚህ መንግስት ስለቀና በወቅቱ የነበረውን አዋጅ ማውጣት አስፈለገ

  7. ለህዝባዊ ተቃውሞ ዝግጁ ሁኑ አሁን ነው ሰአቱ መብታችን እየተረገጠ ነው ይህ ሌባ መንግሥት ለ1Mb ብር 0.45 በሜጋባይት እየከፈልን እንዲሁም ለድምፅ በደቂቃ 0.80 ብር እየተከፈለ ይህ ከፍተኛ ይህ ሆኖ ሳለ አሁን በሚሉት ሥሌት 1.25 ብር በደቂቃ ለማሥላትና ለማሥከፈል የታሰበ ሲሆን የኢትዬጵያ ህዝብ ከአለም ውጭ ለማድረግ ለማፈን ለመግደል በሽብርተኛ መፈረጅ ይህ ነው ውጥኑ ውጥረቱ እንደ ሚበጠሥ ጅማት የሆነበት ወያኔ ገና ምኑን አየው ወደ ወጣበት የበለስ ጫካ ይመለሳታል።

    ሞት ለወያኔ

    21 ክፍለ ዘመን መሆኑን ንገሩት

  8. እንኳን ደሥ አላችሁ! ወያኔ ላልሆናችሁ ሁሉ

    ዛሬ የ whatsapp ካምፓኒ የላኪ እና ተቀባይ መሀል ያለውን ሰጎ ገብ ሀከር ለመከላከል ሚሥጥራዊ encription code መጠቀም የሚያሥችለውን ፕሮግራም ይፋ አረገ ካሁን በሃላ እንደ ወያኔ ያሉ የህዝብን ሚሥጢር ማግኘት ህልም ሆኖ ይቀራል ብሎክ መሆኑን ወያኔ እያንባረቀ ቢሆንም ይህን ለመሥበር መላ ያለን በርካታ የተማረ ህዝብ ያላት ኢትዬጵያ እንደወያኔ ከጫካ ሳይሆን ከሰው ልጆች አብራክ የተፈጠርን ህዝቦች ነን መታችንን እናሥከብራለን መላውን በንቃት ተከታተሉ ይፋ ይሆናል።

  9. Belive me those who are advocating for free Viber access are those who do not like
    Ethiopia’s prosperity their eyes turned red when Ethiopia move
    forward. They are
    foreigners mercenaries.
    No free viber Anyone should pay.

  10. Beabzagnaw kifeya indaynor yemichohut
    Ye Ethiopyachin teltoh nachew Ethiopia yawetachiwn memeles
    alebat . Free
    yehone neger yemitela yelem gin
    Ingna Ethiopians inabezwaln .

  11. Its is becoming a tool for terrorist group that
    is why they feel shocked when they hear the news
    here in DC and else where . why the Government is
    so reluctant in this time where hard currency is
    is badly needed .

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*