በኦሮሚያ ክልል የተበተኑት ጆሮ ጠቢዎች ከነአለቆቻቸው ለግምገማ ተጠሩ::

በኦሮሚያ ክልል የተበተኑት ጆሮ ጠቢዎች ከነአለቆቻቸው ለግምገማ ተጠሩ::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎TPLFSecurityForces‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኦሮሚያ ክልል በወያኔ የደህንነት ተቋም ለስለላ የተበተኑ የወያኔ አሽከሮች ስራቸውን በአግባቡ አልተወጡም በሚል ለግምገማ መጠራታቸውን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል::በኦሮሚያ ክልል ለሁለት አመታት ያህል የኦሕዴድ አባላት ከሕዝቡ ጋር በመቀናጀት በጸረ ሰላም ሃይሎች እየታገዙ በመንግስት ላይ ከፍተኛ የማይፈታ ደንቃራ ሲፈጥሩ አባሎቻችን ስራቸውን በአግባቡ ሳይሰሩ በመቅረታቸው ከፍተኛ የመረጃ ክፍተት በመፈጠሩ የሕዝብ ተቃውሞ መነሳቱ ስለሚታወቅ በዚህ ዙሪያ ለመነጋገር እና ለግምገማ በቅርብ አለቆች አማካኝነት በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንድትገኙ ሲል የወያኔ የደህንነት ተቋም በስልክ ቀጭን ጥሪውን አስተላልፎላቸዋል::

Minilik Salsawi's photo.

በኦሮሚያ ክልል ያለው ጉዳይ እስካሁን በቁጥጥር ስር ማዋል ያቃተው ወያኔ ያሰለጠናቸውን ኬንያዊ ኦሮሚኛ ተናጋሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ የደህንነት አባላትን ደጋግሞ ቢያሰማራ በፍጹም ሊሳካለት እንዳልቻለ እና የኦሕዴድ አባላት ራሳቸው ለተግባራዊ ስራ ታማኝነት ሊያሳዩ ባለመቻላቸው በተለያየ መልኩ የታቀዱ ግቦች ሁሉ እንዲጠመዘዙ በመደረጉ አጣብቂኙ እየጨመረ እንደሄደ የውስጥ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::በትግሪኛ ተናጋሪ የሕወሓት ሰዎች ሰንሰለትነት የተያዘው የደህንነት ተቋሙ ታማኝ ይሆኑኛል ያላቸውን በርካታ የድህነት አባላት እያጣ ሲሆን በዙሪያው የተኮለኮሉ ሆዳም አባላትም በጥርጣሬ ቀለበት ውስጥ መግባታቸውን ምንጮቹ አጠንክረው ይናገራሉ::

ክዚህ ቀደም ወደ ተለያዩ ክፍለጦሮች የተላኩ እና ከሲቭል ወደ ወታደራዊ ደህንነት የተዛወሩ አባላትን መልሶ አምጥቶ አዳዲስ ወታደራዊ የደህንነት ምልምሎችን በየክፍለጦሩ የመመደብ እቅድ መኖሩንም ለተቋሙ ሹሞች ቅርበት ያላቸው ምንጮች ሲናገሩ በኢሚግሬሽን አከባቢ ያሉ የብኣዴን አባላትን አጣርቶ ለማባረር እንደታሰበም ተናግረዋል::እንዲሁም በባህርዳር ጎንደር ደሴ ደብረብርሃን የሚገኙ የደህንነትን አባላት ላይ ተጨማሪ ሃይል ለማድረግ መታቀዱ በአማራ ክልል ይነሳል ተብሎ የተሰጋውን የሕዝብ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ከወዲሁ መታለሙን ምንጮቹ ገልጸዋል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

3 Comments on “በኦሮሚያ ክልል የተበተኑት ጆሮ ጠቢዎች ከነአለቆቻቸው ለግምገማ ተጠሩ::”

  1. 1. HagosAbreha says:
    April 5, 2016 at 8:21 pm
    Negussu Motoma says:
    April 5, 2016 at 8:13 pm
    የዳግም አደዎ ዘመቻ
    ቁጥር 8 አሰቸኳይ መመሪያ
    +-+++++++++++++++
    ኢሐድግዬ(1000 ምርጥ ዘር አደዎዎች) እና ሆዳቸውን የመለኩ በቺሎቹ እስከ አሁን ሕዝባችንን በጭካኔ መግደሉን እና ስልጣኑን ላለመልቀቅ እንደ አበደች ውሻ ሆነዎል። ኢትዮጵያን ምን አይነት አገር እንደሆነች ሳያቋት፣ በሱዳን 17 አስማተኞች አህያዎች ይዘው በጎርፍ ጋኔን ቤተ መንግስት ተሳካላቸው፣ ሕዝባችንንም በዘር ፓለቲካ እንደ አህያ እንዲያስብ አረጉት። ኢትዮጵያ 41 ጊዜ በላይ በመፃፍ ቅዲስ የከበረች እና ሂዱ እዛ ኑሩ የኣላ ሰላም አገር ነች ብለው ነብዩ መሐመድ ያከበራት አገር ነች። አበው እንደሚሉት ይቺን የመከራ ጊዜ ካለፈን ኢትዬጰያዊ መሆን እንደ ሎተሪ የሚታይበት ቀን በቅርቡ ይደርሳል። የአገር ውስጥ ኦርሞዎች የዘር ፓለቲካ ነቃንብሸ ኢሐዲግዬ ብለውታል። የተደራጅው ንኡስ ኮር በወልቃይት፣ በትግራይ፣ በሐረ ር ፣ በአምቦ እና በመተከል ኮሩን ዘርግቶ በየአንዳንዱ ከተማ ሠራዊታችን ገብቷል። ሕዝባችን አየሞተ ነው በኢሕአዴግ አጋዚ እና በረሐብ እርዳታ የሚሰጠው ቅድሚያ ለሆዳሞች ብቻ ከዚያ በሚድያቸው ረዥሙን ይሉኝታ የሌለውን ምላስ ይለቁብናል። የሚከተለውን ተጨማሪ መምሪያ ሕዝባችን ተግባራዊ እንዲያረግ እንገልፃለን።
    1ኛ፣ እኛ የኢሕአዴግ ስላዬቸ እና ከታች ያለውን አብዛኛውን ፈሸካው ሲነፈ የአገር ግዴታ የሚሰሩትን አዘጋጅተን ጨርሰናል። ለምሳሌ በመተማ የሰፈረውን ጦር እንደቋንቋው መረጃውን አግኝቶ ከወገኔ ጋር ብሎ ኢትዬጰያዊነቱን አስቀድሞ በተጠንቀቅ ይጠብቃል። የጦር መሪዎች ስንት የሰረቁት ዶላር አስቀምጠው ጦር ሜዳአይሞክሩትም።
    2ኛ፣ ሕዝባችን በዚህ ጊዜ ያለውን ከአርበኞች ግንባር፣ ኢሳት፣ የአቶ ኦባንግን ድርጅት አንገብጋቢ ወቅት ላይ ስለሆን መርዳት አለበት። አቶ ኦባንግ ሰሞኑን ከዘር ነፃ የሆነ ተራማጅ አትዬጰያን የሚያሰቀድም በሙሁራኖች የተጨመቀ ሰለለውጡ ካርታ እንዴት አውራ ሸግግር መሪ እንደሚጓዝ እና በቋሚ ስርአት ለውጥ መረጃ ይሰጣሉ።
    እኛ አሁን ለወሬ እና ለዘር ፓለቲካ ጊዜ የለንም የፈለገ መሪ በቋሚ ሰርአትን ተከትሉ እኩል ማስተዳደር የሚችል ብቻ ነው የምንፈልገው ከዚህ ውጭ የሆናችሁ የራሳችሁን ሙያ ቀጥሉ እንጂ የማይሁን ቃላት አቁሙ እና ተራማጅ የለውጥ ሐዋሪያዎችን እንድትደግፍ እናሳስባለን።
    3ኛ፣ ሕዝባችን እንዲሁም የ አክሱም ትግራይ ጭቁን ወገኖቻችን፣ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አክብሮ የሰጣትን የሙሴ ፅላት አቡነ ማትያስ ሌሎችን ጳጳሳት ጉባኤ በማግለል ከገንዘብ አፍቃሪ ተሐድሶዎች ጋር በመሆን የውሸት ተቦት አስቀምጠው፣ ትክክለኛውን ለመሸጥ ውሉን ጨርሰዎል ከዚህ ቀን ጀምሮ አቡነ ማቲያስ እንቅልፍ የላቸውም፣ የሚሰሩትን ምንም አያቁም። የግፍ ወንበር በተራው እንደዚህ ያረጋል።
    4ኛ አቡነ መርቆርዮስ በሕገ ወንበር ላይ ስላሉ፣ የአባቶቻችን ድጐማ ና ቀኖና አንዲት ሳት ቀይር ለህዝባችን አንድነት ቡራኬ እና ጥሪ እንዲያደርጉልን በማክበር እንጠይቃለን። ይህንን ስንል የአቡነ ጴጥሮስ መስቀል እና ደም ከፊቶት ቆሟል ማለታችን ነው!!!
    የትግሉ መሪ እስከ ሽግግር ድረስ የተግባር ጀግኖቹ ዲ/ር ብርሀነ ነጋ እና የጦር አስተባባሪ አዛዥ ጀነራል ከማል ገልቹ። ለህዝባችነው መረጃውን አስተላልፍ በተዋረድ ትእዛዝ ተቀብላችሁ በፍቅር እንወጠዋለን። የኢሕአዴግን ስርአት እርቃናው ላይ አድርሰናል በመርᎊ ትንሽ መንካት ነው የቀረን። ትግሉ ወዲያውኑ ሲጀመር የአገር ውስጥ መገናኛ ስለምንቆጣጠር ከህዝብ ጋር የሆነ ትግል ቢበዛ 30 ቀናት ብቻ ነው ።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ከ እግዚአብሔር እርዳታ ጋር!!! ንጉሡ ሞቱማ አምቦ ኮር
    [Reply]
    Reply
    2. አብርሃም ተወልደ says:
    April 6, 2016 at 6:22 pm
    አብርሃም ተወልደ says:
    April 6, 2016 at 6:02 pm
    ጀግኖች ናቹ የሚያሳዝነው ነገር እንደ ተባለውእንደ አህያዋ በድን ሆኖ ስለ አገሩ ቅንጣት እንኳን የማይሰማው
    ብዞች አሉ። በስደቱ አለም ላይ የተዋረደውን ኢትዮጵያዊ አስቡት። ነገ ጠዋት በፍቅር የምንሰባሰበት አገር አለችኝ ግን እኔ ይህንን የጥላቻ አጥር ልበጣጥሰውብለን ዛሬ እርምጃ መወሰድ አለብን። የትም አገር በስደት ያለህው አገርህን እንዳይረሳ። በቅርብ ቀን ኢሐዲጎች በእራት ላይ ተሰባስበው እኛ በየጨቅጣጫው 25 አመት ሙሉ የሐይማኖት ታጋይ አንበሶች ኮራንባችሁ አንድም ቀን መንግሥትን አላወገዛሁም። በቁመና እያላችሁ ይችን ሸልማትአዘገጅተናላችሃለን ብለው ጠቅልለው አንድ አንድ ሽጉጥ አርገው አቦይ ስብሐት፣አባዬች ሆነው ሸለሟቸው። እንዲያውም የሉት በስተመጨረሻ የሚያስደስት ነገር ስላጣን ነው ይህንን ያበረከትናችሁ። የ25 አመት ታሪካችን ቀድመን ከሲቪል ኮሌጅ ለሲኦል የሚሆን ስለሆነ እወቁት ግን አሁን በእስር ቤት ያሉትን ጨካኝ ገራፈዎችን የዘን አንሄድም እዛው ያለው የሱዳኑ ጋኔን ይሻለናሉ አሉ እየሳቁ። አሰቡት እናንተ ስላላቹ ኦርቶዶክስ፣መስሊሙን ልናጣላ ሙከራን አልሆነም ግን ሰሰነጣጥቅናቸው። እና ፓስተር ዳንኤልን ሱቃችሁን አብዝታቹ ወንጌልና ትታዘቹ ይህንን ግራ የገባውን ህዝብ ቢዚይ አርፋችሁ ቸርቹ ውስጥ ታስረግጡታላችሁ አሉን ። እነዚህ ናቸው እንግዲ የአገር እና ሐይማኖትን መሪዎች። አይ 8ኛ ሺየመጨረሻ ሰአት።
    [Reply]
    [Reply]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*