የመተማመን መትነን
ገለታው ዘለቀ
በመጀመሪያ ደረጃ መተማመን (Trsut) ስንል የአንድ ሕብረተሰብ የጋራ ሀብት ወይም የማኅበራዊ ካፒታል ዋና አካል መሆኑን እናንሳ። በአጠቃላይ ማኅበራዊ ካፒታል ስንል ደግሞ ልክ እንደሌሎቹ የሰው ልጆች ካፒታል የሚታይ ነው። ለምሳሌ የገንዘብ ካፒታል፣ የሰው ካፒታል (Human capital) እንደምንለው ማኅበራዊ ካፒታልም ካፒታል ይባላል። ካፒታል ነው እንደንል የሚያስችለን ምክንያት አንድም ልክ እንደሌሎቹ ካፒታሎች የሚመረት (Produce የሚደረግ) መሆኑና ለተለያዩ የማኅበረሰብ ልማቶች ኢንቨስት የምናደርገው ሀብት በመሆኑ ነው። እነዚህ ተፈጥሮዎቹ ከሌሎች ካፒታሎቻችን ጋር ያመሳስሉታል።