“በኢትዮጵያ ያለው የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ምን ይመስላል?” ስትል ጽዮን ግርማ የሂዩማን ራይትስ ዎች የጥናት ባለሞያ ፍሊክስ ሆርንና የደህንነት ጥናት ተቋም የጥናትና ምርምር ባለሞያ ሃሌሉያ ሉሌን ጠይቃለች። ሁለቱም ባለሞያዎች በኢትዮያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት እጦት ተባብሷል ይላሉ። ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ → listen

ገጣሚ ናቸዉ። ፀሐፌ ተዉነትም። ከብዙ የግጥምና የተዉኔት ድርሰቶቻቸዉ መሐል ጣልቃ የገባች አንዲት የታሪክ መፅሐፍ አለቻቸዉ። መፅሐፏ በ19ኛዉ መቶ ክፍለ-ዘመን በሥነ-ፅሑፉ መድረክ ዓለም አቀፍ ክብርና ሞገሥ ያተረፈዉ የሩሲያዊዉ ባለቅኔ የአሌክሳንደር ሰርግዬቪች ፑሽኪን ታሪክን ነዉ የምትወሳዉ። በእሳቸዉ አገላለፅ «ሕዝባዊ» የሚሉት ለገበሬዉና ለዝቅተኛዉ …

ባለቅኔ እና ፀሐፌ-ተዉኔት አያልነህ ሙላቱ – ዶይቸ ቬለ Read more »

ሃይለማርያም ደሳለኝ ውበታቸውን ለማስተካከል የፊት ቀዶ ሕክምና በጀርመን ሊያደርጉ ነው:: #Ethiopia …… ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሕወሓት ጠ/ሚኒስትሩ ከቀናት በፊት የግል አውሮፕላን ተከራይተው ባደን ባደን በተባለ የጀርመን ከተማ የገቡ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው በስፍራው ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል። አቶ ሃይለማርያም በጀርመን የእረፍት ጊዚያቸውን የሚያሳልፉበት ለእረፍት በሚል …

ሃይለማርያም ደሳለኝ ውበታቸውን ለማስተካከል የፊት ቀዶ ሕክምና በጀርመን ሊያደርጉ ነው:: Read more »

የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነኝ ባዩ አቶ ዮሀንስ ሳህሌ 10 ወራት ብቻ ቆይቷል። በአጠቃላይ 25 ጨዋታዎችን በአሰልጣኝነት መርቶ ከ 630ሺ ብር በላይ ተቀብሏል። የተጣራ 50ሺ የወር ደመወዝ፣ 55,000 የኢንተርናሽናል ስልክ ወጪ፣ 27,500 የመኪና ነዳጅ ሲደማመር 632,500 ብር ተከፍሎት ከሃላፊነቱ እንዲለቅ ተደርጓል፡፡ …

የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነኝ ባዩ ዮሃንስ ሳህሌ በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ከባድ ዘረፋ ፈጽሟል:: Read more »

በመተከል ዞን ኦሜድላ ሰርገው የገቡ የሱዳን ወራሪ ወታደሮች 70 ኢትዮጵያውያን አፍነው ወሰዱ:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Sudan‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Metekel‬ ‪#‎Omedla‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ባለፉት ሁለት ሳምንታት በምእራብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ጉምዝ የኢትዮ ሱዳን ድንበር አከባቢ አድፍጠው የነበሩ የሱዳን ወራሪ ወታደሮች ካለፈው አርብ …

በመተከል ዞን ኦሜድላ ሰርገው የገቡ የሱዳን ወራሪ ወታደሮች 70 ኢትዮጵያውያን አፍነው ወሰዱ:: Read more »

በኩራዝ አንድ ስኳር ልማት ሙስናው ቅጥ አጥቷል፣ በጀት ምዝበራው እየከፋ መጥቷል // የፕሮጀክቱ ሠራተኞች– ፋሲካን በግማሽ ደመወዝ፤ በደቡብ ኦሞ ዞን ሳላማጎ ወረዳ እየተገነባ ያለው የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ያለ ዝርዝር ጥናትና ዕቅድ እየተከናወነ የመሆኑ ጉዳይ በአካባቢው አርብቶአደር ነባር ነዋሪዎች ላይ ካስከተለው …

በደቡብ ኦሞ ዞን በኩራዝ አንድ ስኳር ልማት ሙስናው ቅጥ አጥቷል፣ በጀት ምዝበራው እየከፋ መጥቷል Read more »

ኢቢሲ/ኢቲቪ ፋሲካን በጂንካ // ፡ ‹‹ላም ባልዋለበት –ቁበት ለቀማ›› Girma Bekele የደቡብ ቴሌቪዥን ሰፊ የአየር ጊዜ ሰጥቶ ‹‹ፋሲካን በቴሌቪዥን›› እያስኮመኮመን በቲቪ ቁንጣን ስንሰቃይ አሳልፈናል፡፡ እኛና ህዝብ በክልላችን ታሪክ አይተን በማናውቀው ፈተና ውስጥ ነን እያልን ነው፡፡ በዓሉም ቢሆን ያለፈው ቅቤ በለመድንበት …

ኢቢሲ/ኢቲቪ ፋሲካን በጂንካ // ፡ ‹‹ላም ባልዋለበት –ቁበት ለቀማ›› Girma Bekele Read more »

መምሰል ክፉ በሽታ ነው! ያልሆኑትን ሆኖ ለመታየት መሞከር ዕውነተኛ ማንነትን ማጣት ከመሆኑም በተጨማሪ የተነቃለታ ትልቅ ኪሣራ ያስከትላል፡፡ ወገን የሚመስሉን ወገኖችም ቢሆኑ “ከጠላትህ ውሰድኀ ወደ ዘመድህ ዞረህ ጉረስ” የሚለውን ተረት አሳምረው ያውቁታል፡፡ ይህን አለማስተዋል የማታ ማታ ዋጋ ያስከፍላል! “መሆንህ እንጂ፣ መምሰልህ፣ …

መምሰል ክፉ በሽታ ነው! ይህን አለማስተዋል የማታ ማታ ዋጋ ያስከፍላል! Read more »

በዘረኝነት ላይ ኢንተርኔት በጋምቤላ የተፈፀመው የጅምላ ግድያና የህፃናት እገታ፤ ዛሬ የተፈጠረ አዲስ አይነት ተግባር አይደለም፡፡ በጐሳ የተቧደኑ ሰዎች፤ በጭፍን እምነትና ክፉ የዘረኝነት ጥላቻን እየዘመሩ፤ በአጐራባች አካባቢዎች ላይ መዝመት፣ መግደልና መዝረፍ፤ አዲስ ፈጠራ አይደለም፡፡ በጋምቤላ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች፣ በመላ …

“ዘመኑ የጡዘት ነው” – ዮሃንስ ሰ. – በዘረኝነት ላይ ኢንተርኔት Read more »

“ትርፍ ፀጉርና ትርፍ ዳሌ እየገዛችሁ … የምበላው አጣሁ” እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ! እንዴት ሰነበታችሁሳ! ምስኪኗ ሀበሻ አንድዬ ዘንድ ተመልሳ ሄዳለች፡፡ ምስኪኗ ሀበሻ፡— አንድዬ… አንድዬ፡— መጣሽ! አንቺና ምስኪኑ ሀበሻ ነገር ከያዛችሁ አትለቁም ማለት ነው! ምስኪኗ ሀበሻ፡— ምን ላድርግ አንድዬ፣ ምን ላድርግ! …

‘ምስኪኗ ሀበሻ’ እና የኑሮ ነገር… ኤፍሬም እንዳለ Read more »

በየዓመቱ አሳሳቢነቱ እየጨመረ የመጣው የትራፊክ አደጋ በዚህ ዓመት የከፋ መሆኑን፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ የሟቾች ቁጥር 2,978 መድረሱን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ በንብረትም በ ኩል ያደረሰው ጉዳት እየጨመረ የመጣ መሆኑን፣ በተመሳሳይ ወቅት ግምቱ ከ564 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት እንደደረሰም ተገልጿል፡፡ …

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በትራፊክ አደጋ 2,978 ሰዎች ሞተዋል::ከ564 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል Read more »

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሰሚት ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ በተለምዶ እንዶዴ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ሚያዝያ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ከንጋቱ 12፡30 ሰዓት ላይ የተደረመሰው ባለአምስት ፎቅ ሕንፃ ምክንያቱ የጥራት ችግር መሆኑ ተጠቆመ፡፡ ሕንፃው አቶ ዓለማየሁ ታዬ የሚባሉ ግለሰብ ንብረት መሆኑን …

ሰሚት አካባቢ የተደረመሰው ባለአምስት ፎቅ ሕንፃ በጥራት ችግር መሆኑ ተጠቆመ Read more »

News Ethiopia Wetatoch Dimts – መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ [youtube http://www.youtube.com/watch?v=xescidXIGow]

ከታገቱ የኢትዮጵያ ህጻናት 32 ተለቀቁ ከታገቱ የኢትዮጵያ ህጻናት 32 ተለቀቁ ከደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ሰርገው በገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከታገቱ 125 ህጻናት መካከል 32 መለቀቃቸውን የደቡብ ሱዳን መንግሥት ባለሥልጣናት አስታወቁ። በደቡብ ሱዳን የቦማ ግዛት ተጠባባቂ አስተዳዳሪ ኦጋቶ ቻን ከሊኳንጎሌ …

ከታገቱ የኢትዮጵያ ህጻናት 32 ተለቀቁ Read more »

የዋጋ ንረት በአማካኝ – የኑሮ ውድነት የወያኔው ስርአት የተጭበረበረ ፖለቲካ አስተዳደር የፈጠረው ችግር ነው:: —- + ዶሮ = 400 —– ፍየል = 4500 —— በግ = 6000 —— በሬ = 35 000 —— እንቁላል አንዱ = 4.00 ብር ወዘተረፈ — …

የዋጋ ንረት በአማካኝ – የኑሮ ውድነት የወያኔው ስርአት የተጭበረበረ ፖለቲካ አስተዳደር የፈጠረው ችግር ነው:: Read more »

በተለያዩ የአዲስ አበባ የገበያ ስፍራዎች ተዟዙረን የበዓል ገበያ ዋጋን ለመቃኘት እንደሞከርነው፤ በአብዛኛው ከዓምና ተመሳሳይ የበዓል ገበያ ዋጋ ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡ በአቃቂ ቄራ ገበያ የበሬ ዋጋ ከ5 ሺህ እስከ 22 ሺህ ብር ድረስ ሲሆን ዓምና በተመሳሳይ በዓል የበሬ ዋጋ ከ8 ሺህ …

የዘንድሮ የትንሳኤ በአል ገበያ … Read more »

የ25 አመቱ አጋጅ መሪ / ቢንያም ሙሉጌታ ከኖርዌይ ወያኔ በቆርጦ ቀጥል የቅንብር መርሁ መሰረት የህዝብን ጥያቄና እሮሮ ከሚፈልገው የበሬ ወለደ ዘገባው ጋር በማዛመድ 25 ለሚያህሉ በአምባገነናዊነት በተሞሉ አመታት በብቸኝነት በተቆጣጠረው የሀገሪቱ ሚዲያዎች፤ በጋዜጣ፣ በራዲዮ፣ በቴሊቪዥን፣ እና በመሳሰሉት የመገናኛ አውታሮች እውነታውን በመደበቅ …

የ25 አመቱ አጋጅ መሪ / ቢንያም ሙሉጌታ ከኖርዌይ Read more »

የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን ከእስር እንዲለቅ ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ አቀረበች ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Journalism‬ ‪#‎FreethePress‬ ‪#‎WoubishetTaye‬ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እ.አ.አ. ሰኔ 19, 2011 በመንግስት ባለሥልጣናት ታሰረ። ውብሸት በአማርኛ ቋንቋ የሚሰራጨው የአውራምባው ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነበር። አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንደገለጸው …

የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን ከእስር እንዲለቅ ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ አቀረበች Read more »

ሕዝቦችን ያማከለ አንድነት ለትግሉ ስኬት – ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው። ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthiopianOppositionparties‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Unity‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ኢትዮጵያዊነት ችሮታ አሊያም ስጦታ ሲልም በደረጃ የሚሰጥ ዜግነት ሳይሆን የእያንዳንዱ ሕዝብ የማንነት መሰረት የተፈጥሮ ማሕተብ እና …

የኢትዮጵያዊነት የደረጃ መዳቢ አድርጎ እራሱን ያስቀመጠው አደገኛ የአመለካከት ቡድን እስከአሁን በመወራጨት ላይ እንዳለ ነው። በአንድነት ሽፋን ዳግም ቅኝ ግዛት የለም:: Read more »

የኢትዮጵያው ፌዴራል ዐቃቤ ህግ 33 ሰዎችን በአገር ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን (የኦነግን) ድርጅታዊ ህዋስ በመመሥረት፣ በመምራትና አባላት በመሆን የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል ሲል በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መሠረተባቸው። ፍርድ ቤቱም፣ ተከሳሾቹ መልስ እንዲሰጡ በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ …

33 ሰዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ድርጅታዊ ህዋስ በመመሥረትና በአሸባሪነት ተከሰሱ – VOA Read more »

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ የአመራር አባል አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 በሽብር የተጠረጠሩ ተከሳሾች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ። እነ አቶ በቀለ በማረሚያ ቤት ስድብ ማስፈራራትና ሌሎችም ከፍተኛ ተጽኖዎች እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ …

የኦፌኮ ከፍተኛ የአመራር አባላት በማረሚያ ቤት ከፍተኛ በደል ይደርስብናል አሉ – VOA Read more »

የኢትዮጵያን ቋንቋ፣ ታሪክና ባህል ለበርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን በማስተማር ላይ ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል በሜሪላንድ የሚገኘው የደብረ ገነት መድሃኒያለም ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አንዱ ነው። በዚሁ ቤተክርስቲያን በምክትል አስተዳዳሪነትና በቅዳሴ በማገልገል ላይ የሚገኙት መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ገብረወልድ አገዝ ወደ …

የቆሎ ተማሪ በአሜሪካ – VOA Read more »

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት በሽብር ተግባር በተከሰሱ ሰባት ተከሳሾች ላይ ዛሬ ከሰባት እስከ ዘጠኝ ዓመት ፅኑ የእስራት ቅጣት በየነ። በብይኑ መሰረት፣ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ኦኬሎ ኦኳይ

·         የ2008 ዓ.ም በዓለ ስቅለት በእመቤታችን ቀን ውሏል። እናም ይሰገዳል? ወይስ አይሰገድም?
·         ይኸው ገጠመኝ በ1913 ዓ.ም ተከስቶ በነበረበት ወቅት አበው ጉዳዩን እንዴት ፈቱት?
(መምህር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ):- በተወሰኑ ዓመታት መካከል የስቅለት ዕለት በየጊዜው ዘንድሮ እንደሆነው ሲገጥም ክርክር ይነሳል። አስታውሳለሁ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ ሳለሁ እንዲሁ ስግደት በእመቤታችን ዕለት በመዋሉ ምክንያት በተለያዩ አድባራት ተበታትነን በዓሉን የምናሳልፍ ተማሪዎች እንደየደብሩ አለቃ ስሜት ወይም ግንዛቤ አሳልፈን ተመልሰናል። ማለትም አንዱ ጋር ይሰገዳል አንዱ ጋር አይሰገድም። ይህ ክርክር ዘንድሮም ቀጥሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የማያዳግም ምላሽ ቢሰጥበት መልካም ነው። በቅድሚያ ጾሙን በጥሩ ሁኔታ የቻላችሁትን ያክል በትጋት ላሳለፋችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ድካም ባለው ተጋድሎዋችሁ ቸርነቱን አክሎበት የልባችሁን መሻት ይስጥልኝ። የጾምና ጸሎታችሁም በረከት ይድረሰን ለብርሃነ ትንሳኤውም በሰላም ያድርሰን እላለሁ።
ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ ዘንድሮ ስቅለት በእመቤታችን ቀን ውሏል። እናም ይሰገዳል? ወይስ አይሰገድም? በሕማማት ውስጥ ከትንሳኤ በፊት ያለችው ቅዳሜ የተሻረች ሰንበት ትባላለች (ቀዳሚት ስዑር) ሃይማኖተ አበው እንደሚያዝዘን በቅዳሜ ቀን መጾም ክልክል ነው። ከቀዳሚት ስዑር በቀር ይላል ስለተሻረች የሕማማትን ቅዳሜ እንጾማታለን በሕማማት ውላለችና። ልክ እንደዚሁ በሕማማት ማንኛውም በዓል ቢውል አይከበርም።
የእመቤታችን በዓል ስለሆነ ስግደት የለም ካልንና ካልሰገድን ቅዳሴ ሊኖር ይገባ ነበር። ቅዳሴ ሳይቀደስ የሚከበር የእመቤታችን በዓል የለንምና ስለዚህ የነገው አርብ ይሰገዳል። ይህ የኔ አሳብ አይደለም የአባቶቼ ትምህርት እንጂ። እስቲ የዛሬ ዘጠና አምስት ዓመት ገደማ ስቅለት እንደዛሬ ውሎ የተፈጸመውን ክስተት ላቅርብላችሁ። የታሪኩ ጸሐፊ ክቡር ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደቂርቆስ ናቸው። ዓመተ ምህረቱም ሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፫ ዓ.ም( ሚያዝያ 21/ 1913 ዓ.ም ነው)። ምንም ያልተጨመረበትና ያልተቀነሰለት ታሪኩ እንዲህ ይላል።

“የስቅለት በዓል በዚህ ዘመን ሚያዝያ ፳፩ ቀን ላይ ውሎ ነበር። የአዲስ አበባ አድባራት ሊቃውንትም እኩሌቶቹ በማርያም በዓል ምክንያት ስግደት መስገድ አይገባም ሲሉ እኩሌቶቹ መስገድ ይገባል ብለው ነበርና የአሳብ ልዩነት ተፈጥሮ ዋለ።
ግርማዊት ንግሥትና ልዑል አልጋወራሽ በሚገኙበት ቤተ ክርስቲያን በሥዕል ቤት ኪዳነ ምህረት (በዓታ ያለችውን ኪዳነ ምህረት ነው) ባንድ ወገን መምህር ደስታ “መስገድ አይገባም ሲሉ” ግማሹ ሕዝብ እሳቸውን ተከትሎ አንገቱን ብቻ ጎንበስ እያደረገ ጸሎቱን ያደርስ ጀመር። እሳቸው ለማስረጃ ያቀረቡትም “መቅድመ ተአምር የማርያምን በዓላት እንደ እሁድ ሰንበት አድርጋችሁ አክብሩ ይላልና በእሁድ ቀን ምን ጊዜም ስግደት ስለሌለ ዛሬ መስገድ አይገባም” የሚል ቃል ነው።
በሁለተኛው ወገንም አለቃ ገብረ መድኅን “ስግደት መስገድ ይገባል” ስላሉ ግማሹ ሕዝብ እሳቸውን ተከትሎ ይሰግድ ጀመር። ለማስረጃም ያቀረቡት “የዛሬው በዓል በስግደት የሚከበር በዓል ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታ በተሰቀለበት ቀን በመስቀሉ ስር ቆማ እያለቀሰች እና እየተጨነቀች በብዙ ድካም የዋለችበት ቀን ነው። ከዚህም በላይ ከእመቤታችን በዓል ይልቅ የክርስቶስ በዓል ይበልጣልና እንደ አበው ሥርዓት በዓሉ በስግደት ሊከበር ይገባል” የሚል ነበር። ይህ የአለቃ ገ/መድኅን አሳብ በትልቁ መምህር በአለቃ ወልደማርያም የጊቢ ገብርኤል አለቃ ሲደገፍ
የመምህር ደስታም አሳብ በሌሎች አለቆች ተደገፈ።
ከዚህም በኋላ ግርማዊት ንግሥትና ልዑል አልጋወራሽ ይህን የሊቃውንቱን ልዩነት ለማስቀረት እና አንድ ነገር ለማስወሰን ስለፈለጉ ወደ አቡነ ማቴዎስ ሁለት መልእክተኞችን ላኩ። እነርሱም የንግሥት መምህረ ንስሐ መላከ ገነት ተድላና የልዑል አልጋወራሽ መምህረ ንስሐ አባ ወልደማርያም ናቸው። እኔ ራሴ አባ ወልደማርያምን ተከትዬ ሄጄ ነበርና የሆነውን ሁሉ በቅርብ ተከታትዬዋለሁ።
መልክተኞቹ ከሊቀ ጳጳሱ ፊት ቀርበው የነገሩን አኳኋን ካስረዱ በኋላ በዛሬው ቀን ይሰገድ እንደሆነ ወይም አይሰገድ እንደሆነ ለመጠየቅ እና ውሳኔዎን ለመቀበል መጥተናል ብለው ተናገሩ። አቡነ ማቴዎስም ያለምንም ማመንታት ለአልጋወራሽ አሳወቋቸውና ይሰገድ ጀመረ።
የሆነው ሆኖ አብዛኛው ሰዓት በክርክርና በጥያቄ ምክንያት ባክኖ ነበር። እኔም ይህን ታሪክ መጻፌ ወደፊት የዚህ ዓይነት ነገር ቢያጋጥም ማስታወሻ እንዲሆን በማሰብ ነው።”
ምንጭ።- መርስዔ ኀዘን ወልደቂርቆስ “የሃያኛው ክ.ዘ. መባቻ የዘመን ታሪክ ትዝታዬ ካየሁትና ከሰማሁት” (1896-1923 ገጽ 237/38።)
++++++
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የብሔራዊ ቡድኑ የአሰልጣኞች እና ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በሙሉ ከስራቸው እንዲሰናበቱ መወሠኑን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሪሽን ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ የሆኑትን ኢንስትራክተር ዮሀንስ ሣህሌ ፣ ምክትል አሰልጣኝ የነበረው ፋሲል… Continue Reading →

ባለፈዉ ሐሙስ በጋምቤላ ክልል በጄዊ የስድተኞች መጠለያ ካምፕ አከባቢ ንብረትነቱ /ACF/ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት የሆነ አንድ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ ሁለት የስደተኞች ልጆች ከሞቱ በኋላ ስደተኞቹ 21 የአካባቢውን ነዋሪዎች ሲገድሉ፣ ከ10 በላይ መቁሰለቸዉን ዘገባዎች ያሳያሉ።

ተባራሪው ኣቶ ኣፅበሃ ኣረጋዊ  By Amdom Gebresilasie =========== በእምባ ስነይቲ ህዝብ “ውክልናችን ኣንስተናል” ተብለው በህዝቡ የተነሱት የህወሓት ተወካዩ ክቡር ኣቶ ኣፅበሃ ኣረጋዊ ወደ ፖርላማ ለመመለስ እየተራሯጡ ይገኛሉ። የተከበሩ ኣቶ ኣፅበሃ ግን ኣይገርሙም? እምባስነይቲን ወክለው ፓርላማ የገቡት ዘንድሮ ለ2ኛ ግዜ ነበር። …

በእምባ ስነይቲ ህዝብ “ውክልናችን ኣንስተናል” ተብለው በህዝቡ የተነሱት የህወሓት ተወካዩ ክቡር ኣቶ ኣፅበሃ ኣረጋዊ ወደ ፖርላማ ለመመለስ እየተራሯጡ ይገኛሉ። Read more »

ይገርምሃል ወንድሜ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም፡፡ አታየውም ቸልሲን መከራውን ሲቀበል፡፡ አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎችኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል፡፡ ለሚወጣ ሰው ግን መውረድ …

ሕይወት – ሌስተርና ቼልሲ (ዳንኤል ክብረት) Read more »

“የጸሃይ ብርሃን እንዳናይ፤ ውሃ እንኳን እንድንለምን ተደርገናል። ልጆቻችንና ዘመዶቻችን እኛን ለማየት እንዳይችሉ ተደርገናል።” አቶ ደጀኔ ጣፋ ታሳሪ የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባል። ዋሽንግተን ዲሲ — “ከማዕከላዊ ምርመራ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ስንመጣ መድሃኒት ውሰዱ ተባልን። መድሃኒቱንአንወስድም ሌላ አማራጭ ጠየቅን።” አቶ በቀለ ገርባ፤ …

“የጸሃይ ብርሃን እንዳናይ፤ ውሃ እንኳን እንድንለምን ተደርገናል። ልጆቻችንና ዘመዶቻችን እኛን ለማየት እንዳይችሉ ተደርገናል።” የኦፌኮ አመራር አባላት Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ እገኛለሁ:: በአዲስ አበባ ቆይታዬ ከሄድኩበት ጉዳይ ጎን ለጎን በኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ ሚና ከሚጫወቱ የማህበራዊ ድህረገጽ ጓደኞቼ ጋር ተገናኝቶ በሰፊው የመወያየቱ እድል ገጥሞኛል::ከነዚህ ወዳጆቼ ውስጥ የተወሰኑት በወያኔ አገዛዝ ውስጥ በስልጣን ላይ ተቀምጠው …

ኢሕኣዴግ የተረጋጋ መንግስት እየመራ አለመሆኑን የድርጅቱ ሰዎች እየተናገሩ ነው:: Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ባለፈው ሳምንት ከደቡብ ሱዳን ድንበሩን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል በመግባት በርካቶችን በመግደል ታዳጊ ሕጻናትን አፍነው የወሰዱት ታጣቂዎች አፍነው የወሰዷቸውን ታዳጊዎች በጆንግሌ ግዛት ዋት ተብሎ በሚጠራ አከባቢ አስፍረዋቸው ከደቡብ ሱዳን መግስት እና ከኢሕኣዴግ አገዛዝ ጋር …

ከጋምቤላ ታፍነው የተወሰዱት ሕጻናት በገንዘብ ለማስለቀቅ ድርድር ተይዟል:: Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የደህንነት ተቋሙን ምስጢር ለውጪ ሃይል አሳልፈው ሰጥተዋል የተባሉ የደህንነት ሃይሎች አስሯል::በተባለበት በዚህ ሳምንት ውስጥ ኢሕኣዴግ መራሹ መንግስት የውጪ ፖሊሲውን እንዲፈትሽ የቀረበለትን ሃሳብ እየመረመረው መሆኑን ለኢሕኣዴግ አገዛዝ የደህንነት እና የዲፕሎማሲ አማካሪዎች ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል:: በአራት …

ውጤት አልባው ኢሕኣዴግ የውጪና የደህንነት ፖሊሲውን እንዲፈትሽ የቀረበለትን ሃሳብ እየመረመረው ነው:: ‪ Read more »

News #Ethiopia Wetatoch Dimts –  መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ ። [youtube http://www.youtube.com/watch?v=olpzLQJW7DA]

ከርሳም መሬት!- ለእናቴ የጻፍኩት ጦማር – Muluken tesfaw እናቴ ዛሬ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ‹ሲከፋህ ቤተ ክርስቲያን ሂድ!› ባልሽኝ ምክር መሠረት እስከዛሬ አድባር ላድባር ስዞር ኖርኩ፡፡ ዛሬ ግን ቤተ ክርስቲያን ሂጄ ‹ምክርሽን ባልሰማ ኖሮ› እያልኩ ተጸጽቻለሁ፡፡ ይህች ከርሳም መሬት ይህን ሁሉ ሕዝብ …

ከርሳም መሬት!- ለእናቴ የጻፍኩት ጦማር – Muluken Tesfaw Read more »

በትግራይ ክልል የእምባስነይቲ ህዝብ ቀድሞ የነበረውን ወረዳ እንዲመለስለት ከ20 ዓመታት በላይ ጠይቆ አወንታዊ መልስ ባለማግኘቱ ምክንያት የተሰማውን ቅሬታ ትላንት በሰላማዊ ሰልፍ ገልጿል።

መንግስት የቆየውን ወረዳችን የማይመልስልን ከሆነ ከወረዳ እስከ ተወካዮች ምክር ቤት የወከልናቸውን ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ ውክልናችን ማንሳታችን እንገልፃለን ብሏል ህዝቡ።

ከ500 ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕለተ ስቅለትን እንዴት ታከብር እንደነበር በመጠኑ ሊያሳዩን ከሚችሉ መዛግብት አንዱ ‹ዜና ደብረ ሊባኖስ› የተሰኘው መዝገብ ነው፡፡ ዜና ደብረ ሊባኖስ በ1586 ዓም የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ አምስት ነገሮችን ይዟል፡፡ የደብረ ሊባኖስን ታሪክ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት …

ሥርዓተ ዕለተ ስቅለት ዘደብረ ሊባኖስ – ዳንኤል ክብረት Read more »

“ጠዋት ቂሊንጦ ስንሄድ አራቱ ሰዎች የሉም። ያሉበትን የሚነግረን አላገኘንም።” ወ/ሮ ዓይናለም ደበሎ፤ ላለፉት አራት ወራት በማዕከላዊ እሥር ቤት የነበሩትና ካለፈው አርብ አንስቶ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዛውረዋል፤ ከተባሉት የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባላት ቤተሰብ አባላት አንዷ ናቸው። ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ → …

እስር ላይ የሚገኙትን አራት የኦፌኮ አመራር አባላት መጠየቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ – VOA Read more »

በበፍቃዱ ኃይሉ

ዓይን የሚፈታተን ደብዛዛ ብርሃን ያለበት ክፍል ውስጥ አስገብተው ከኋላዬ ወፍራሙን የብረት በር፣ ልብ በሚያደባልቅ ጓጓታ ድብልቅ አድርገው ዘጉት፡፡ ወደመታሰሪያ ክፍል የገባሁት እንዲህ ነበር፡፡ ሰዓቱ ከምሽቱ 3፡00 ወይም 4፡00 ሰዐት ገደማ ነው፣ ሚያዝያ 17፣ 2006፡፡ ከውስጥ መሬት ላይ የተኙ ሰዎች ይታዩኛል፡፡ በእጄ ያንጠለጠልኩትን ፌስታል እንደያዝኩ ተራ በተራ አየኋቸው፡፡ አንደኛው ከተኛበት ተነስቶ ቁጢጥ አለ፡፡ ‹ካቦው ይሄንኛው ነው ማለት ነው› አልኩ በልቤ፡፡ ‹የሻማ ሲጠይቁኝ ኪሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ሰጥቼ ለመገላገል ፈልጌያለሁ› እነርሱ ግን የሻማ አልጠየቁኝም፡፡ ‹አረፍ በል› አሉኝ፡፡ ጠርዝ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ‹ራት በልተሃል?› አሉኝ፤ ‹አዎ በልቻለሁ›፡፡

‹ምን አድርገህ ነው?›
‹ጸሐፊ ነኝ፡፡›
‹አሃ፣ ጋዜጠኛ ነህ?›
‹አይ፣ ኢንተርኔት ላይ ነው የምጽፈው፡፡›
‹ሙስሊም ነህ?›
‹አይ አይደለሁም፡፡›

የሚያስፈራ ዝምታ ሰፈነ፡፡ ‹እናንተስ?› አልኳቸው፤ ዝምታውን ለመስበር፡፡

ቁጢጥ ያለው፣ ‹እኔ እና እሱ› አለ ወደ አንደኛው ልጅ እየጠቆሙ ‹በሙስሊሞች ጉዳይ ነው፤ እነሱ› አለኝ ወደሌሎች ሦስት ልጆች እየጠቆመ ‹ከጋምቤላ ነው የመጡት፤ እኚህ ከሶማሊ ክልል ነው የመጡት፡፡ ያኛው› ወደጥግ ወዳለው እየጠቆመ ‹በግንቦት ሰባት ነው የተጠረጠረው› አለኝ፡፡ ሰባት ነበሩ፡፡ እኔ ስምንተኛ ሆንኩላቸው፡፡ በሳይቤሪያ የዘጠኝ ቁጥር እስረኛ ሆኜ ተቀላቀልኳቸው፡፡ ማብራሪያውን የሰጠኝ ረደላ ሸፋ ነበር፡፡ ሦስቱ አኙዋኮች ኡማን ኝኬው፣ ኡጁሉ ቻም እና ኝጎ ኩምቻሬ ነበሩ፡፡ ሶማሌው፣ እኔ በገባሁ በሁለተኛው ቀን ስለተፈታ ዘነጋሁት፡፡ የረደላ አባሪ ሐሰን ነው፡፡ ጥግ ላይ የነበረውና በክፍላችን ብቸኛው የግንቦት ሰባት ወታደርነት ተጠርጣሪ የነበረው አበበ ካሴ ነበር፡፡

ኒጎ ኩምቻሬ እሱ ተኝቶባት የነበረውን ፍራሽ ለቆልኝ እስከመጨረሻ ድረስ የቆየሁባትን ጥግ ላይ ያለች ምቹ ቦታ አወረሰኝ፡፡ ‹በቃ፣ አሁን ተኛ እና ነገ እናወራለን› አሉኝ፡፡ እሺ አልኳቸው፡፡ እነርሱ ተኙ፡፡

አበበ ካሴ እኔ በገባሁበት ሰዐት ምርመራ ጨርሶ ነበር፡፡ ነገር ግን በአስፈሪ ዝምታ የተዋጠ ሰው ነበር፡፡ ተሰብስበን ኮንከር (ካርታ) ስንጫወት ብቻ፣ እየዳኘ በተራው ይጫወታል፡፡ እየቆየን ስንመጣ ግን ቀስ በቀስ ያዋራኝ ጀመር፡፡ ጠርጣራ ስለነበር፣ ድምፁን በጣም ዝቅ አድርጎ በእርጋታ ነበር የሚያዋራኝ፡፡ ምርመራ አምሽቼ ስመጣ፣ እልሄን የምወጣው እነሱ ጋር ነበር፡፡ ያሉኝን ብስጭቶችና ብሶቶች ሁሉ እነርሱ ላይ እዘረግፈዋለሁ፡፡ እነርሱም፣ አብዛኞቹ ምርመራቸውን ጨርሰው ክስ የሚጠባበቁ ስለነበሩ፣ እኔን ከበው ማፅናናት ብቻ ሆነ ሥራቸው፡፡ አበበ አንድ ቀን ማታ መጥቼ እንደለመድኩት ‹ሊገሉኝ ነው፤ ካልገደሉኝ አይለቁኝም› እያልኩ ሳማርር፡፡

‹አሁን ይቺን ተመታሁ ብለህ ነው?› አለኝ፡፡

በአባባሉ ተናድጄ መልስ ከመስጠቴ በፊት የእጆቹን አይበሉባ አሳየኝ፡፡ ‹ጥፍሮቼን እያቸው› አለኝ፡፡ ጥፍሮቹ ጣቶቹ ላይ የሉም፡፡ ‹እኔ እንኳን እንዲህ አድርገውኝ ዋጥ ነው ያደረግኳት፡፡ ወንድ ልጅ ቻል ነው ማድረግ ያለበት፡፡ ወንድ አደለህ እንዴ?› እኔ የወንድነት ጀብድ የምመኝበት ጊዜ ላይ አልነበርኩም፡፡ ይልቁንም እሱ እኔን ለመምከሪያ ያሳየኝ ጣቶቹ ማስፈራሪያ ሆነው አረፉት፡፡ እኔም ባለተራ ነኝ ብዬ አሰብኩ፡፡

አበበ ካሴ ቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባል የነበረ፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተዋጋ፣ ከዚያ በኋላ ግን ለቅቆ ግንቦት ሰባትን የተቀላቀለ ወታደር ነበር፡፡ ሲራመድ ያነክሳል፡፡ ‹ምን አርገውህ ነው?› ስለው ‹ምኑን አውቄ› አለኝ፡፡ ሲደበደብ ራሱን ይስት ነበር፡፡ አበበ ካሴ ከኤርትራ ጎንደር የዘመዱን ሠርግ ለመታደም መጥቶ ነው የተያዘው፡፡ በምርመራ ወቅት የግንቦት ሰባት ወታደር መሆኑን በፍፁም አላመነም ነበር፡፡ ያደገበት እና የኖረበት ኩራት በዱላ ፊት መንበርከክ አልፈቀደለትም፡፡ ክስ ከተመሠረተበት በኋላ ግን ለፍርድ ቤቱ “አዎ፣ የግንቦት ሰባት ወታደር ነኝ፤ የሆንኩትም አምኜበት ነው” ብሏል፡፡

አበበ ካሴ ከኔ ክፍል ተቀይሮ ተስፋለም ታስሮበት ወደነበረው 4 ቁጥር የተዛወረው ከአጭር ቀናት በኋላ ነበር፡፡ ነገር ግን መልሰን ቂሊንጦ ዞን ሁለት ተገናኘን፡፡ አበበ መጀመሪያ የተከሰሰው በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ በአንቀጽ 4 ቢሆንም፣ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከተደመጡ በኋላ ተቀይሮለት 7/1 ሆኖለታል፡፡ የዛኔ ‹እንኳን ደስ አለህ› ልለው ክፍሉ ሄጄ ነበር፡፡ ሳቀብኝ፡፡ ‹ታስሬ እያለሁ ቁጥር ተቀነሰልኝ ብዬ የምደሰት ይመስልሃል?› ስሜቱን አላጣሁትም፡፡

እንደአበበ ካሴ በቂሊንጦ አስተዳደር የሚጠላ የፖለቲካ እስረኛ አልገጠመኝም፡፡ አበበ ሕክምና ተከልክሎ እግሩ ከጊዜ ወደጊዜ እየተሸመቀቀ አጥሮ ግቢ ውስጥ በምርኩዝ ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ ብልቱ ላይ በምርመራ ወቅት በደረሰበት ጉዳት የሚያዥ ነገር ተከስቶበት ሕክምና ሲጠይቅ ተከልክሏል፡፡ በጥቅሉ የሰው ልጅ ላይ የሰው ልጅ ሊያደርስበት የሚችለው በደል ሁሉ እየደረሰበት ነው፡፡
አበበ ካሴ አሁን 7 ዓመት ከዘጠኝ ወር ፅኑ እስራት ተፈርዶበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ገብቷል፡፡

እንደ አበበ ሁሉ አዱኛ እና መገርሳም በየቀኑ ሐሳቤ ናቸው፡፡ ማዕከላዊ ሳይቤሪያ የሚባለው ወንዶች ክፍል፤ ዘጠኝ ቁጥር ውስጥ ሁለት ሳምንት ከቆየሁ በኋላ ከክፍላችን የሚወጡ ሰዎች በዙ፡፡ ከሦስቱ የአኙዋ ልጆች አንዱ – ኝጎ ኩምቻሬ – ጓደኞቹ ላይ ሊመሰክር ተስማምቶ ወደጣውላ ክፍል ተዛወረ፡፡ ኡማን እና ኡጁሉ ክስ እስኪመሠረትባቸው ድረስ ወደሚቆዩበት ሸራተን ተዛወሩ፡፡ የሶማሊ ክልሉ ሰው ተፈታ፡፡ በምትካቸው ግን ብዙ ሰዎች መጡ፡፡

የአዳማ ዩንቨርስቲው አዱኛ ኬሶ መጣ፡፡ ገብረሚካኤል እና ሌላ ሥሙን የዘነጋሁት ሰው ከትግራይ ክልል መጡ፡፡ ሌላም ሰውዬ ከሶማሊ ክልል መጡ፡፡ አጀሌ ከቤንሻንጉል/ጉምዝ መጣ፡፡ ሁሉም የተጠረጠሩት በሽብርተኝነት ወንጀል ነው፡፡

ከሁሉም ሳቂታና ተጫዋች የነበረው አዱኛ ኬሶ ነበር፡፡ አዱኛ ከተያዘ 19 ቀናት እንደሆነው ነገረን፡፡ ‹የት ቆየህ?› አያውቀውም፡፡ ምክንያቱም፣ ወደቆየበት ቦታ ሲሄድም ሆነ ወደእኛ ሲመጣ ዓይኖቹ በጨርቅ ተሸፍነው ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ ወደሽንት ቤት ሲወሰድ እና ሲመለስ ዓይኖቹ በጨርቅ ይሸፈኑ ነበር፡፡ አዱኛ ወደኔ ክፍል ሲመጣ ግራ ዓይኑ ስር የበለዘ ነገር ነበረው፡፡ ‹ምንድን ነው?› ብዬ ስጠይቀው፣ ‹ሲይዙኝ በቡጢ የነረቱኝ ነው› አለኝ፡፡ አሁን ድረስ ያ የቡጢ አሻራ ጠባሳ ሁኖ ቀርቷል፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ በፖሊስ ተደግፎ መጥቶ፣ በፖሊስ ተደግፎ 8 ቁጥር (የብቻ ጨለማ ቤት) ሲወጣና ሲገባ የቆየው መገርሳ ወደእኛ ክፍል ገባ፡፡ መገርሳ ወርቁ የሐሮማያ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነበር፡፡ መገርሳ መጀመሪያ የተያዘው ሐረማያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ በተወረወረ ቦምብ ተሳትፈሃል በሚል ተጠርጥሮ ነበር፡፡ መገርሳን ሐሮማያ ከተማ ተደብድቧል፡፡ ድብደባው እርቃን ነበር፡፡ እጆቹ በገመድ ተጠፍረው ጉልበቱን ያቅፍና በእጆቹ መታጠፊያ እና በቋንጃው መካከል እንጨት ያልፍና ይሰቀላል – ወፌ ይላላ፡፡ ከዚያ ይደበደባል፡፡ መገርሳ ይህንን ይነግረኝ የነበረው፣ እግሮቹ መታጠፊያ ላይ የቀረውን ሰምበር የመሰለ ነገር እያሳየኝ ነው፡፡ ‹ተንጠልጥዬ እየተሰቃየሁ ብልቴን ይጎትቱታል› ብሎኛል ሲነግረኝ፡፡ በመሐሉ ራሱን ይስታል፡፡ ‹ከዚያ ቅዝቅዝ ሲለኝ እነቃለሁ፤ ስነቃ አውርደውኝ አገኛለሁ፡፡ አሁንስ ታምናለህ አታምንም ይሉኛል፡፡ የማምነው ነገር እንደሌለ ሲያውቁ መልሰው ይሰቅሉኛል፡፡› አለ፡፡ በመጨረሻ ግን መገርሳ ተረታ፡፡
‹ሳስበው ከምሞት፣ ዕድሜ ልክ ተፈርዶብኝ በሕይወት ብኖር ይሻለኛል ብዬ አሰብኩ› አለ፡፡ ‹አዎ፣ እኔ ነኝ ቦንቡን የወረወርኩት› አላቸው፡፡ መርማሪዎቹ ተደሰቱ፡፡ ራቁቱን የሆነ ክፍል ውስጥ መሬት ላይ አጋድመውት ሄዱ፡፡ ከዚያ ‹በሕይወቴ የማይዘነጋኝ ዘግናኝ ነገር ተከሰተ› ብሎ የሚከተለውን አጫወተኝ፡፡ ቤቱ ውስጥ የዶሮ ጫጩቶች ነበሩ (የአንዱ የደህንነት ሰራተኛ መኖሪያ ቤት ውስጥ ይመስለዋል ያለው)፡፡ ጫጩቶቹ መጥተው እየተራመዱ እላዩ ላይ ይወጡበታል፡፡ መገርሳ እነርሱን “እሽ” ብሎ የሚያባርርበት አቅም አልነበረውም፡፡ እግራቸው ይበላዋል፡፡ ሲነግረኝ ‹ጫጩቶቹን ጠላኋቸው› ነበር ያለኝ፡፡ ግን ምንም ሊያደርጋቸው አልቻለም፡፡

በማግስቱ በካሜራ ፊት ሐረማያ ዩንቨርስቲ ግቢ ውስጥ የፈነዳውን ቦምብ ያፈነዳው እሱ እንደሆነ አመነ፡፡ እሱ በወቅቱ ዩንቨርስቲው ግቢ ውስጥ አልነበረም፡፡ እንዲያውም የታቀደ ረብሻ እንዳለ መረጃው ቀድሞ ደርሶት ለዩንቨርስቲ ግቢው የኦሕዴድ ጽ/ቤት ደውሎ ማስጠንቀቁን ነግሮኛል፡፡ ያ ሁሉ አልፎ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ተላልፎ ተሰጠ፡፡ ነገር ግን፣ እሱ ወደአዲስ አበባ እየመጣ እያለ ፖሊስ የእውነትም ቦንቡን ወርውሮታል ብሎ ያመነበትን ሰው ያዝኩኝ አለ፡፡ ነገር ግን ካፈርኩ አይመልሰኝ ባይ መንግሥት መገርሳን ከመክሰስ አልተመለሰም፡፡ ጽፈኸዋል በተባለው ግጥም ክስ ተመስርቶበት ‹ተከላከል› ተብሎ፣ መከላከያ ምስክሮቹን አስደምጦ ‹የነጻ› ወይም ‹ጥፋተኛ› ብይን እየተጠባበቀ ነው፡፡ አዱኛ ኬሶም በተመሳሳይ መዝገብ ‹በቄሮ አባልነት› ተከላከል ተብሎ መከላከያ ምስክሮቹን እያስደመጠ ነው፡፡

ታስሮ መፈታት ቅጣት ነው፡፡ ሰቅጣጭ በደል በሚፈፀምባት ከተማ፣ አገር ሠላም ብሎ ከሚኖር ሰው ጋር ምንም እንዳላየ፣ ምንም እንዳልሰሙ መስለው የመኖር ቅጣት፡፡

ማዕከላዊ ምርመራ ወጥቼ ስገባ፣ መታሸት ሲያስፈልገኝ ሲያሸኝ፣ ጨዋታ ሲያመምረኝ ሲያጫውተኝ የነበረው ረደላ ሸፋ እና አባሪው ሀሰን ሁለቱም ‹ነጻ ለመውጣት ወይም ጥፋተኛ ለመባል ተከላከሉ› ተብለው መከላከያ ምስክሮቻቸውን ለማስደመጥ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ የቤንሻንጉሉ አጄላ አራት ዓመት ተፈርዶበት ሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ተወስዷል፡፡ አቦይ ገብረሚካኤል ‹ተከላከሉ› ተብለው መከላከያ ምስክር እያስደመጡ ነው፡፡ ኡማን እና ኡጁሉም ‹ጥፋተኛ› ተብለው ፍርዳቸውን ለመመቀበል ቀጠሮ ተይዞላቸዋል፡፡

እስረኞች ይመጣሉ፣ ከሰሜን ይመጣሉ፣ ከደቡብ ይመጣሉ፣ ከምሥራቅ ይመጣሉ፣ ከምዕራብ ይመጣሉ፡፡ በሕዝብ ጥቅም ሥም ጦር መዝዞ ሥልጣን የተቆጣጠረው መንግሥት ዛሬም የፖለቲካ እስረኞች የሉኝም ይላል፡፡

ከአራት መቶ በላይ የሚሆኑ አሶሳ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች በፌደራል ትምሕርት ሚኒስቴርና በቤንሻጉል ክልል ምክር ቤት ላይ የፍትሐቤር ክስ መመስረታቸው ታወቀ። ለክክልሉ ምክር ቤት መጥሪያ ሊሰጡ የሄዱት የአርሶ አደሮቹ ተወካይ ተይዘው መታሰራቸውም ይሰማል። የክልሉን ምክትል አስተዳዳሪ እና የቤንሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች …

ከ400 በላይ የሚሆኑ አሶሳ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ክስ መመስረታቸው ታወቀ – VOA Read more »

በናትናኤል ፈለቀ

ሚያዝያ 17 ቀን 2006 ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ ከቤት የሸከፍኩትን ጋቢ እና ቅያሪ ልብስ እንደያዝኩ ማዕከላዊ በተለምዶ ሳይቤሪያ በመባል የሚታወቀው የእስረኞች ማጎሪያ ሕንፃ 7 ቁጥር ገባሁ፡፡ ውስጥ 7 ሰዎች ነበሩ፡፡ እኔ 8ኛ ሆኜ ነው የተቀላቀልኳቸው፡፡ ምንም ሳልናገር ቆሜ ክፍሉን አየሁት፡፡ ሰዎቹን አየኋቸው፡፡
አንድም ቃል ሳንለዋወጥ አንደኛው “ኢትዮጵያ” ብሎ በሀዘኔታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ፡፡
ኦቻን ኦፕዮ የአኝዋክ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በ1996 በጋምቤላ የተቀሰቀሰውን ግጭት ሸሽተው ወደአሁኗ ደቡብ ሱዳን ከተሰደዱት ኢትዮጵያውያን መካከል ነበር፡፡ በወቅቱ የተከሰተውን ችግር ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ይፈፅም የነበረውን ግድያ በመሸሽ ለቀናት ጫካ ውስጥ ተደብቆ ከቆየ በኋላ ነበር ቀናትን የፈጀ የእግር ጉዞ አድርጎ ደቡብ ሱዳን የገባው፡፡ ከጁባ አቅራቢያ የአለ የስደተኞች ጣቢያ ውስጥ ከ8 ዓመት በላይ የቆየው ኦቻን ቤተሰብ መሥርቶ፣ ሁለት ልጆችን ወልዶ በጁባ የተረጋጋ ሕይወት መኖር ጀምሮ ነበር፡፡
የ1996ቱ የጋምቤላ ቀውስ በተቀሰቀሰበት ወቅት ክልሉን በርዕሰ ብሔርነት ይመሩ የነበሩት አቶ ኦኬሎ ኦኳይ በደቡብ ሱዳን መንግሥት ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው ሲሰጡ ከጁባ አብረዋቸው የታሰሩት የአኝዋክ ተወላጆች መካከል ኦቻን ኦፕዮ ነበር፡፡
ወደደቡብ ሱዳን ሲሸሽ ጫካ ውስጥ እሾሃማ የዛፍ ቅርንጫፍ የቀኝ ዓይኑን መቶት የማየት ችሎታውን ቢጋርድበትም የቀረችውን የማየት ችሎታውን በአኝዋክኛ የተተረጎመውን መጽሐፍ ቅዱስ እያነበበ የእስር ግዜውን ያሳልፋል፡፡ (በነገራችን ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደአኝዋ የተረጎሙት ኡመድ አግዋ በአሁኑ ወቅት በሽብር ወንጀል ተከሰው ቂሊንጦ ይገኛሉ፡፡)
ኦቻን ሲበዛ ሠላማዊ ሰው ነው፡፡ የሁለት ልጆቹ ነገር አብዝቶ ያሳሰበው ቀን ግን ከሰው ጋር መነጋገር አይፈልግም፡፡ አንድ ቀን ድንገት ብቻውን ስቅስቅ ብሎ ያለቅስ ጀመር፡፡ ሰባት ቁጥር በግዜው የቀረነው እሱ፣ እኔና ዘግየት ብሎ የተቀላቀለን ቢልሱማ የሚባል የሐሮማያ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነበርን፡፡ ሁለታችን በጣም ተደናግጠን ምን እንደሆነ ጠይቀነው ሊነግረን ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ቆይቶ ሲረጋጋ ልጆቹ እንደናፈቁት እና ምን አጥፍቶ እንዲህ ያለ ፈተና እንደገጠመው እንዳልገባው እያማረረ አጫወተኝ፡፡
በነኦኬሎ ኦኳይ መዝገብ 3ኛ ተከሳሽ ሆኖ ቀድሞ ቂሊንጦ የወረደው ኦቻን ነበር፡፡ ከጥቂት ግዜያት በኋላ እኔም በነሶልያና ሽመልስ መዝገብ 3ኛ ተከሳሽ ሆኜ ቂሊንጦ ስወርድ ኦቻንን ዞን3 አገኘሁት፡፡ እንደመጀመሪያው ሁሉ ተንከባክቦ ግቢውን አላመደኝ፡፡
ኦቻን የአኝዋ አስተማሪዬም ነበር፡፡ ለቤት የመጀመሪያ ልጅ መሆኔን ስለሚያውቅ በአኝዋ ባሕል እንደሚደረገው ኡመድ እያለ ነው የሚጠራኝ፡፡ ትንሽ የማይባሉ የአኝዋ ቃላትንም አስተምሮኛል፡፡
የአኙዋኩ ጓደኛዬ የተከፈተበት የሽብር ክስ የአገር ግዛት አንድነትን ለማፍረስ ሞክሯል በሚል ተቀይሮለት ጥፋተኛ ተብሎ ቂሊንጦ ፍርዱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ እስር ስገባ ያስተዋልኩት በሐዘን ተሞልቶ “ኢትዮጵያ!” ሲል ያማረረው ፊቱ እስከ ሕይወቴ ፍፃሜ አብሮኝ ይዘልቃል፡፡ ይህችን አጭር ጦማር ያለህበት ድረስ መንፈስ ይዞት ይመጣ እንደሆን ይነ ፑዋ! ኦሎ ቦንጎ! ብዬሃለሁ፣ ኦቻን ኦፒዮ፡፡

«የሽምብራው ጥርጥር የዛፎቹ ፍሬ የትም የትም ዞሬ ትዝ አለኝ ሀገሬ» የዛሬ ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩን «የመሰንቆው ሊቅ» ጌታመሳይ አበበ ዘመን ተሻጋሪ ከሆኑ የባህል ሙዚቃ ጨዋታዎች በግንባር ቀደምትነቱ የሚታወቀዉ ነዉ። ሁለ ገቡ ከያኒ ጌታመሳይ አበበ «የጥበብ ገበሪም » በመባል ይታወቃሉ። …

«የመሰንቆው ሊቅ» ጌታመሳይ አበበ – ዶይቸ ቬለ Read more »

በዘውዲቱ ሆስፒታል የእንቅርት ታካሚዋ ለሃሞት ጠጠር ህክምና ሆዷ ተከፈተ

– የህክምና ስህተቱን የፈፀሙት ሃኪም ከሥራ ተባረዋል
– “የሃሞት ጠጠሩ በነፃ ስለወጣልሽ ዕድለኛ ነሽ” ሲሉ ዋሽተዋታል

   በዘውዲቱ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ በተፈፀመ የህክምና ስህተት ሣቢያ እንቅርት ለማስወጣት የሄደችው ታካሚ በስመ ሞክሼ በተፈጠረ ስህተት ለሃሞት ጠጠር ህክምና ሆዷ ተከፈተ። ታካሚዋ ከሁለት ዓመታት ወረፋ ጥበቃ በኋላ ተራዋ ደርሶ በአንገቷ ላይ የወጣውን እንቅርት ለማስወጣት ነበር ወደ ሆስፒታሉ የሄደችው፡፡
ሠላም ደሞዜ የተባለችው ታካሚ በአንገቷ ላይ የወጣውን እንቅርት ለማስወጣት አስፈላጊውን ምርመራ አድርጋ በሆስፒታሉ አልጋ ትይዛለች። በሌላ በኩል ሰላም ኪሮስ የተባለች ታካሚ ደግሞ ለሃሞት ከረጢት ጠጠር ህክምና ወረፋ ጠብቃ ቀጠሮዋ በመድረሱ ነበር ወደ ሆስፒታሉ ያመራችው፡፡ ወጣቷ በቀዶ ህክምና ከህመሟ ለመፈወስ አስፈላጊውን ምርመራ አከናውና በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ እንድተኛ ይደረጋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ ሁለቱም ህሙማን የቀዶ ህክምና ሊደረግላቸው ቀጠሮ ተይዞላቸው ሲጠባበቁ ከቆዩ በኋላ ለእንቅርት ህክምና ወደ ሆስፒታሉ ያመራችው ሰላም ደሞዜ በቅድሚያ ወደ ቀዶ ህክምናው ክፍል ትገባለች። የእንቅርት ታካሚዋ በቀዶ ህክምናው ክፍል ከገባች በኋላ ለሃሞት ከረጢት ጠጠር ህክምና ሆዷ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ በታካሚዋ ሃሞት ውስጥ ለቀዶ ህክምና የሚያበቃ ችግር አለመኖሩን ያስተዋሉት የቀዶ ህክምና ባለሙያው፤ ሆዷን መልሰው በመዝጋት የእንቅርት ማውጣት ህክምናውን ያደርጉላታል፡፡
ጉዳዩ ከፍተኛ መደናገጥ የፈጠረባቸው ሃኪሙ፤ በወቅቱ ስለተፈፀመው ሁኔታ አንዳችም ነገር ሳይናገሩ የቀዶ ህክምና ክፍሉን ለቀው ይወጣሉ። ከስፍራው ያገኘናቸው ምንጮች እንደገለፁልን፤ የሀኪሙ ረዳቶችና በስፍራው የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች ችግሩን ለመሸፈንና የተፈጠረውን ስህተት ለመደበቅ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ሲሆን፤ ታማሚዋ ለእንቅርት ቀዶ ህክምና ወደ ሆስፒታሉ ቢመጡም የሃሞት ከረጢት ጠጠር ችግር ስለተገኘባቸው ህክምናው በነፃ እንደተደረገላቸውና በዚህም ዕድለኛ እንደሆኑ በመንገር ቤተሰቦቻቸውን ለማሳመን ጥረት አድርገዋል ተብሏል፡፡ ሁኔታው ያልተዋጠላቸው የታማሚዋ ቤተሰቦች ቀደም ሲል ምንም ዓይነት የህመም ምልክት ባልታየበት፣ ምርመራና ቅድመ ህክምና ባልተደረገበት ሁኔታ በድንገት ለሃሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና የሚያበቃ ችግር ሊፈጠር አይችልም በሚል ከሆስፒታሉ አስተዳደርና ከህክምና ባለሙያዎቹ ጋር ውዝግብ ይፈጥራሉ፡፡ ጉዳዩ የሆስፒታሉ አስተዳደር  ኃላፊዎች ጋር ደርሶም እንዲጣራ ከተደረገ በኋላ ትልቅ የህክምና ስህተት መፈጠሩ ታምኖበት፣ የህክምና ባለሙያዎቹና አስተዳደሩ ቤተሰቦቿን ይቅርታ በመጠየቅ ለታካሚዋ የቅርብ የህክምና ክትትል እንዲደረግላት የተወሰነ ሲሆን የቀዶ ህክምና ባለሙያውና ረዳቶቹ ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የዘውዲቱ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ተረፈ አሰፋ፤ የህክምና ስህተቱ መፈፀሙን አምነው ስህተቱ የተፈፀመው በወቅቱ የቀዶ ህክምናውን ያደረጉት ሃኪምና ረዳቶቻቸው ታካሚዋ በትክክል የመጣችው ምን ዓይነት ህክምና ልትፈጽም መሆኑንና ሌሎች ሁኔታዎችን በአግባቡ ሳያረጋግጡ ህክምናውን በመጀመራቸው ነው ብለዋል፡፡
አንድ ሰው የቀዶ ህክምና ከማድረጉ በፊት በአግባቡ ሊደረግ የሚገባው “ሰርጂካል ሴፍቲ ቼክ ሊስት” መኖሩን የጠቆሙት ዶ/ር ተረፈ፤ በዚህች ወጣት ታካሚ ላይ ይህ ጥንቃቄ ሳይደረግ በመቅረቱ ስህተቱ መከሰቱን አስረድተዋል፡፡
የስህተቱ መፈፀም ሳያንስ በወቅቱ ስህተቱ አምኖና ስለ ሁኔታው ለቤተሰቦቿ ትክክለኛ መረጃ ሰጥቶ ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ የነበረ ቢሆንም ይህም አለመደረጉን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
“አሁን ታካሚዋ ለህይወቷ የሚያሰጋት ምንም አይነት ችግር የሌለባት መሆኑ በህክምና ባለሙያዎች በሚገባ ስለተረጋገጠ ስለጉዳዩ ለቤተሰቦቿ በቂ መረጃ በመስጠት ይቅርታ ጠይቀናቸዋል፡፡ ታማሚዋ ግን ከሆስፒታሉ እንድትወጣ በሃኪሞቿ ቢፈቀድላትም ሁለት ቀዶ ህክምና በማድረጓ በቅርብ ሆና የጤናዋን ሁኔታ እንድንከታተላት ስለፈለግን አሁንም በሆስፒታሉ ውስጥ ትገኛለች፡፡ የጤናዋ ሁኔታ ግን በጣም ጥሩ ነው” ብለዋል – ዶ/ር ተረፈ አሰፋ፡፡ ስህተቱን የፈፀሙት የቀዶ ጥገና ሃኪም በኮንትራት የተቀጠሩ መሆናቸውን ያመለከቱት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ፤ ከሥራና ከደመወዝ እንዲታገዱ በማድረግ የዲሲፕሊን እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል፡፡
ትልቁ ስህተት የቀዶ ሃኪሙ ቢሆንም ሥራው ላይ የተሳተፉት የሀኪሙ ረዳቶችም ከተጠያቂነት ሊያመልጡ እንደማይችሉ ጠቁመው እነሱም የዲሲፕሊን እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል – ዶ/ር ተረፈ፡፡  

እስከአሁን ባደረግነው ክትትል በትናንትናው ዕለት 14 ኢትዮጵያውያን በደቡብ ሱዳን ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውንና አስከሬኖቻቸው ተለይተው ዛሬ ለዘመድ አዝማድ መላካቸውን ለሆስፒታል ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል። አስክሬን ፍለጋው መቀጠሉ ተነግሯል። ዝርዝሩን ያዳምጡ → listen

የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰብ ላይ እያካሄደ ነው ያሉትን አፈና እንደሚያወግዙ አሥራ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ለምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ አቅርበዋል። የውሣኔ ሃሣቡን የያዘው ሰነድ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ሲቪሎችን መግደላቸው በተገለፀበት በአሁኑ ሁኔታ የአሜሪካው …

የአሜሪካ ሴናተሮች “ኢትዮጵያ ውስጥ አለ” ያሉትን አፈና አወገዙ – VOA Read more »


ጥር 9/2008 ዓ.ም. ማለዳ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ አዲስ በተገነባው የፍጥነት መንገድ ላይ ይጓዝ የነበረ አሽከርካሪ መኪናውን መቆጣጠር ተስኖታል። የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪው በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ ነው። ከተቃራኒ አቅጣጫ አንድ መለስተኛ አዉቶቡስ አስራ ስድስት ሰዎች ጭኖ ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዘ ነው። የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪው የሚጓዝበትን መንገድ ስቶ

በታንዛኒያ በሕገወጥ ስደተኝነት ተፈርዶባቸው በእስር የቆዩ 74 ኢትዮጵያዊያን በኬንያ ድንበር ከተማ ታቬታ ተጥለዋል። ድርጊቱ ያስቆጣት ኬንያ “በዓለምአቀፍ ሕግ የታንዛኒያን ሸክም የምቀበልበት እዳ የለብኝም” በማለት አውግዛ ባሳለፍነው ማክሰኞ ከእስር የተፈቱትን ኢትዮጵያዊያን ወደ ታንዛኒያ እንደምትመልስ ገልጻለች። ታንዛንያ እስረኞቹን ወደሀገራቸው ኢትዮጵያ ከመመለስ ይልቅ ወደ ኬንያ ወስዳ የመልቀቋ ምክንያት የታወቀ ነገር የለም (ምንጭ:- ኒውስ24) Filed under: NEWS

ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ የተመለሰው የብራና መጽሐፍ እያወዛገበ ነው

• ከዩኒቨርስቲው ጋር የተፈራረሙት የደብረ ሊባኖስ ገዳም አስተዳዳሪ ከሥራቸው ታግደው ነበር
• ሐዋርድ ያዘጋጀው ውል የባለቤትነት መብትን ይነፍጋል
• ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትቀበለው ውል እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ተሰጥቷል

  “እውነት እና አገልግሎት” ተቋማዊ ብሂሉና መፈክሩ ነው፡፡ በተለይ፣ ለጥቁሮች በሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ዕድልና አስተምሮ በሚያወጣቸው ጥቁር ምሁራን ብዛት ይታወቃል – የአሜሪካው ሐዋርድ ዩኒቨርስቲ፡፡
የዘርና የቀለም ልዩነቶች፣ ፖሊቲካዊና ኢኮኖሚያዊ በደሎች ያስከተሏቸውን መድልዎች፤ ለማኅበራዊ ፍትሕ በቆሙና ለሰብአዊ ነፃነት በሚሟገቱ ምሁራን ማስወገድ ዓላማው ያደረገው ዩኒቨርስቲው፤ በአፍሪካ፣ በአሜሪካና በሌላውም ዓለም የተበተኑ ጥቁሮችን የታሪክና የባህል ቅርሶች ያካበተበት የምርምር ማዕከሉም ከዓለም በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት መካከል ያደርገዋል፡፡
በየአጋጣሚው ያሰባሰባቸውን ቅርሶችና ውርሶች፣ ወደ ጥንት ቦታቸውና ትክክለኛ ባለቤቶቻቸው በሕጋዊ መንገድ መመለስ፣ “ታሪካዊና ባህላዊ ሀብቶቹን ማክበር ነው፤” ይላሉ፣ የዩኒቨርስቲው የሥነ መለኰት ት/ቤት የአካዳሚያዊ ጉዳዮች ተባባሪ ዲን ዶ/ር ጌይ ባይረን፡፡ በተለይም ኢትዮጵያዊ ቅርሶችን ለኢትዮጵያ የመመለስ ጉዳይ፣ የት/ቤቱ የቆየ ፍላጎት እንደነበርና ይህም በአሜሪካም ሆነ በሌላው ዓለም ቅርሶቹን በግልና በተቋም ለያዙ ግለሰቦች፣ ሙዝየሞችና ተቋማት አርኣያነት እንዳለውና ተነሣሽነትንም እንደሚፈጥር ዶ/ር ባይረን ያስረዳሉ፡፡
በት/ቤቱ ማኅደረ ቅርስ ከተከማቹት ኢትዮጵያዊ የብራና ሥነ ጽሑፍ ሀብቶች መካከል፣ ገድለ ቅዱስ ሰራባሞንና ገድለ ቅዱስ ጳውሎስ አንዱ ነው፡፡ የብራና መጽሐፉ፣ በ1993 ዓ.ም. ዶ/ር አንድሬ ቲውድ ከተባሉ የዩኒቨርስቲው የቀድሞው ተማሪ በስጦታ የተበረከተ ሲሆን የ4ኛው መ/ክ/ዘመኑን ሰማዕት ቅዱስ ሰራባሞንና የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ገድል በአንድ ጥራዝ የያዘ ነው፡፡ ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከዐረብኛ ወደ ግእዝ የተተረጎመው በዘጠነኛው የደብረ ሊባኖስ ዕጨጌ አባ መርሐ ክርስቶስ አስተዳደር(ከ1456-1490 ዓ.ም.) ነበር፡፡
የጥንተ ክርስትና እና የሐዲስ ኪዳን ምሁር የሆኑት ዶ/ር ባይረን፣ የብራና መጽሐፉን ወደ ዲጅታል በመለወጥ፣ የትመጣውን ለማወቅ ጥናት ካደረጉት የሥነ መለኰት ት/ቤቱ ምሁራን አንዱ እንደነበሩ፣ የዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ ዘግቧል፤ የገድሉ ጥንተ ባለቤት የደብረ ሊባኖስ ገዳም መሆኑ የታወቀውና ወደ ጥንት ቦታው ለመመለስ የተወሰነውም በጥናቱ ሒደት እንደነበር በዘገባው ተገልጧል፡፡ ከገድሉ ይዞታ ጋር በተያያዘ አስተዳደራዊና ሕጋዊ አካሔዶችን ጨምሮ የተለያዩ ዕንቅፋቶች ዩኒቨርስቲውን እንዳጋጠሙት፣ ድረ ገጹ በጥናቱ የተሳተፉ ምሁራንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ዩኒቨርስቲው ገድሉን ወደ ጥንት ቦታው በሕጋዊ መንገድ ለመመለስ በማሰብ፣ በሕግ አማካሪው አርቃቂነት “የስጦታ ውል” የተሰኘና በስምንት ነጥቦች የተዘረዘረ የስምምነት ሰነድ አዘጋጅቷል፡፡ ውሉ በሐዋርድ ዩኒቨርስቲና በደብረ ሊባኖስ ገዳም መካከል የተፈፀመ መሆኑን የሚገልፀው ዘገባው፤ በሥነ መለኰት ት/ቤቱ ዋና ዲን ዶ/ር አልቶን ፖላርድና በገዳሙ ፀባቴ (አስተዳዳሪ) አባ ወልደ ማርያም አድማሱ እንደተፈረመበትም ጠቁሟል፡፡ ይሁንና የውሉ ይዘት  ከባለቤትነት መብትና ከቅርሱ አመላለስ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ሆኖ ተገኝቷል ይላሉ ምንጮች፡፡
ዩኒቨርስቲው÷ “ከማናቸውም ግዴታ ነፃ የሆነ የባለቤትነት መብት በብራና መጽሐፉ ላይ አለው” የሚለው የውሉ መግቢያ፣ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚመልሰውም “በስጦታ ለመስጠት በመፈለጉ” እንደኾነ ይገልፃል፡፡ የብራና መጽሐፉን ለገዳሙ በስጦታ የሚሰጥበት የባለቤትነት መብት እንዳለው ገዳሙ መስማማቱን የሚገልፀው ውሉ፤ ገዳሙም የብራና መጽሐፉን ሲቀበል፣ ዩኒቨርስቲው ሙሉ በሙሉ የሚያስተላልፈው፣ “አካላዊ የባለቤትነት መብት”ን እንደሆነ አስፍሯል፡፡ ገዳሙን በመወከል የፈረሙት ሓላፊም፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውል ስምምነቱን እንድታከብር የሚያደርግ ዋስትና የመስጠት ሥልጣን እንዳላቸው በውል ሰነዱ ላይ ተመልክቷል፡፡
ባለፈው ሰኞ፣ የዩኒቨርስቲው ሓላፊዎችና ምሁራን በፓትርያርኩ ጽ/ቤት ተገኝተው ገድለ ቅዱስ ሰራባሞን ወጳውሎስን ለገዳሙ ባስረከቡበት ወቅት፣ በግልጽ የተነሡት ተቃውሞዎችና ስጋቶች፣ አስተዳዳሪው ከዩኒቨርስቲው ጋር የተፈራረሙት ሰነድ፣ የገድሉን ባለቤትነት ለገዳሙ ሳይሆን ለዩኒቨርስቲው መስጠቱን አረጋግጧል፡፡
ዩኒቨርስቲው ገድሉን ወደ ጥንት ቦታው መመለሱን ቤተ ክርስቲያኒቱ በከፍተኛ አድናቆት እንደምትመለከተውና እንደሚያስደስታት ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ተናግረዋል፡፡ “ጥንታዊው ብራና ቅርሳችን በመሆኑ ብንቀበለውም ስምምነቱ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕጋዊ የባለቤትነት መብት የሚጎዳ፣ በትውልዱም ዘንድ የሚያስነቅፍ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፤” ሲሉ ተቃውመዋል፡፡
የውል ሰነዱም፣ በልዩ ጽ/ቤታቸው፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የውጭ ግንኙነት መምሪያ፣ በሕግ አገልግሎቱና በቅርሳቅርስ ጥበቃ መምሪያ በጋራ እንዲታይና እንዲመረመርም ፓትርያርኩ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
የደብረ ሊባኖስ ገዳም የሚገኝበትን የሰሜን ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሊቀ ጳጳስነት የሚመሩት አቡነ ቀውስጦስ በበኩላቸው፣ የቅርሱ መመለስ የሁላችን ደስታ ቢሆንም የተመለሰበት ሒደት ግን የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓትና መዋቅር እንዲሁም የገዳሙን ክብር እንዳልጠበቀ ገልጸዋል፡፡ ሦስተኛ ወገን በማስገባት በአስተዳዳሪውና በዩኒቨርስቲው የተፈረመውን ስምምነት÷ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት፣ ሊቀ ጳጳሱ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ፣ ቅዱስ ፓትርያርኩና ቅዱስ ሲኖዶሱ ሳያውቁትና ሳይመረምሩት ሕጋዊ የባለቤትነት መብትን በሚያሳጣ መልኩ መፈጸሙን ብፁዕነታቸው አስረድተዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖናና መዋቅር በመጣስ “ለመታየት እና ለመግነን” ሲባል የተፈጸመው ድርጊት አግባብ ያለመሆኑን ሊቀ ጳጳሱ በርክክቡ ወቅት በመናገራቸውም፣ “እዚያች ገዳም ትኖራታለህ፤ እንተያያለን፤ የፈለከውን ሹምበት” በሚል በገዳሙ አስተዳዳሪ መዘለፋቸው ተጠቅሷል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የገዳሙ አስተዳዳሪ ባለፈው ረቡዕ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ÷ ከሥራ፣ ከደመወዝና ከአገልግሎት ታግደው እንደነበር ታውቋል፡፡ ከትላንት በስቲያ የገዳሙን መነኰሳት አስከትለው በመምጣት በፓትርያርኩ ፊት ሊቀ ጳጳሱን ይቅርታ በመጠየቃቸው በመካከላቸው  ዕርቀ ሰላም ወርዷል፤ ተብሏል፡፡  ይኹንና አስተዳዳሪው “ተጠሪነቴ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ነው” በሚል ያለሥልጣናቸው ከዩኒቨርስቲው ጋር ፈጽመውታል የተባለው ስምምነት ያስነሣቸው ስጋቶችና ተቃውሞዎች ግን መቋጫ አላገኙም፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱ የባለቤትነት መብቷን አሳልፋ ሰጥታ መልሳ በስጦታ መልክ የምትቀበልበት አንዳችም ምክንያት እንደሌለና የዩኒቨርስቲውም ፍላጐት እንዳልሆነ ሒደቱን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡  የስጦታ ውሉ ባስነሳው ውዝግብ ሳቢያ ዩኒቨርስቲው የሕግ አማካሪውን ሳያሰናብት እንዳልቀረም እኒሁ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቷ በበኩሏ፤ “የስጦታ ውል” ሰነዱን እንደምትቃወመው ለዩኒቨርስቲው በይፋ በማሳወቅ፣ ተቀባይነት ያለው ስምምነት እንዲዘጋጅ ጥያቄ ማቅረብ እንዳለበት ተወስኗል፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ቤ/ክርስቲያኗ የአሜሪካንና የአውሮፓን ዩኒቨርሲቲዎች፣ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ባደመቁት  ሌሎች ቅርሶቿ አመላለስ ላይ የራሱ አዎንታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ብለዋል፡፡