የአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ በአዲስ አበባ
የአይቮሪ ኮስትና የሊብያ ጉዳዮች ናቸው የአፍሪካ ሕብረቱ የአዲስ አበባ የከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ ምክንያቶች፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ከባድ ውሣኔዎችን እንዲያሣልፉ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የአፍሪካ ሕብረት ተአማኒነት ጉዳይና የገንዘብም ጉዳይ ሌሎቹ ጠረጴዛ ላይ ያሉ መነጋገሪያዎች ናቸው፡፡ በኅዳሩ ምርጫ አሸናፊነታቸውን ዓለም በስፋት ያረጋገጠላቸውና ዕውቅና የሰጣቸው …