በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ሃይልአ ቅርቦት እጥረትና የመጠጥ ውሃ ችግር እየተባባሰ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ ቀደም ብሎ የነበረው የውሃና የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር እንደተባባሰና በአንዳንድ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች በውሃ እጥረት ምክንያት ህብረተሰቡ አሁንም እየተጉላላ መሆኑን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ዘገባ ገለጸ:: እንደ ዘጋቢያችን ሪፖርት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በተከሰተው የውሃ እጥረት ምክንያት ነዋሪዎች ውሃ ፍለጋ ረጂም መንገድ ለመጉአዝ እየተገደዱ እንደሆነ አክሎ ገልፁአል::  ከዚሁ ጋር በተያያዘም በከተማይቱ አሁንም የኤሌክትሪክ አቅርቦት እጥረቱ እንደቀጠለና ይህም ችግር በርካታ ክፍለ ከተሞች ላይ እየተከሰተ መሆኑን ገልጹአል::

በአዲስ አበባ ከተማ ያለው የመብራት ሃይል አቅርቦት ችግር በዚህ መልኩ ባለበት ሁኔታ ለዘረኛው አምባገነን አገዛዝ ቅርበት እንዳለው የሚታወቀው ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ ከበለስ የኃይል ማመንጫ ወደ አዲስ አበባ የተዘረጋውና ከ1.9 ቢሊዮን ብር በላይ የወጣበት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርና የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታቸው ተጠናቁአል፡፡ የኤሌክትሪክ ሃይል ችግር ከንግዲህ አይኖርም ብሉአል::

የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን ችግር አስመልክቶ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ በሰጡት አስተያየት መቼም ወያኔ ይቺን ሃገር እስከገዛ ድረስ ህዝቡ ከችግር ነጻ ይሆናል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው:: የጊቤ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግንብታ ተጀምሮና እስከተጠናቀቀበት ጊዜ ድረስ ወያኔ እየተከሰተ ላለው የመብራት ሃይል እጥረት የማይቀባጥረው ነገርና የማይሰጠው ምክንያት አልነበረም። እነሆ ጊቤም ሆነ ተኬዜ ተመርቆ አገልግሎት እየሰጠ ነው ብንባልም እንደሚታየው ችግራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት እንጂ እየተሻለው ሲሄድ አይታይም ብለዋል፣ በመጨረሻም ችግራችንና የችግሮቻችን ምንጭ ወያኔና ወያኔ በመሆኑ ዛሬ ነገ ሳንል ባንድነት ተነስተን ከትከሻችን ላይ አሽቀንጥረንን መጣል ይኖርብናል በማለት አስተያየታቸውን አጠቃለዋል::