የቀረንን ስላለማስነጠቅ፤ እሴታችንን ስለመጠበቅ!
ልጅ ተክሌ (ኦታዋ – ካናዳ)
መጀመሪያ አገራችንን፣ ቀጥሎ ደግሞ ባህላችንን፣ ከዚያ ማንነታችንን
1 – ሰዉ ሁሉ፡ የሚተነፍሰው ሊቢያን ነው። ግብጽን ነው። ቱኒሲያን ነው። የመንን ነው። ጅቡቲንም ሳይቀር። ስለዚህ ያኛው ጉዳይ ብዙ ሰዎች ስለበዙበትና የተጣበበ ስለመሰለኝ፡ “እንቁላላችንን ሁሉ ባንድ ቅርጫት” እንዳናደርግ በማሰብ፡ ደግሞም ትግሉ ፈርጀ ብዙ ስለሆነ እነሆ ፊቴን ወደ ባህልና ውርስ አዞርኩ። ለነገሩ የፖለቲካ ሩጫችንስ ቢሆን የባህልና የባህርይ ለውጥ ለማምጣት፡ ማንነታችንንና እኛነታችንን ለማስጠበቅ አይደል?