ወያኔ በያዝነው የበጀት አመት ወደ ውጪ የላከው የቡና ምርት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ መሁኑ ተዘገበ
በያዝነው የበጀት አመት አጋማሸ ከኢትዮጵያ ወደ ውጪ ሃገር ይልካል ተብሎ የታቀደ የቡና ምርት በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ሮይተርስ የተባለው የዜና አውታር ዘገበ። እንደዘገባው ከሆነ በአፍሪካ በቡና አቅራቢነቱዋ የምትታወቀው ሃገራችን ከምርቱ ከፍተኛ ገቢ በማግኘት በዘርፉ ላይ የተሰማሩትን ገበሬዎች ማጠናከር ብሎም ከድህነት አረንቁዋ ማውጣት የምትችልባቸው አጋጣሚዎች ሰፊ ሆነው ሳሉ ወያኔ በተገቢው ማከናወን አለመቻሉ በርካታ ታዛቢዎችን እንዳስገረመም አክሎ ገልጾአል።
መለስና ግብረአበሮቹ በተለያየ ስም ባቋቋሙዋቸው ድርጅቶቻቸው በገሀድ ከሚያደርጉዋቸው የውጭ ንግድ በተጨማሪ በድብቅ ወደውጭ ሀገራት በመላክ የሚሸጡዋቸው ምርቶች ሀገሪቱዋ ከፍተኛ ገቢ እንድታጣ ማድረጋቸውን ገልጹአል:;
ኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች አንዱ ቡና ሲሆን መለስ ዜናዊና ግብረአበሮቹ በፍጠንት ለመክበር ካላቸው ራስ ወዳድነት የተነሳ ሁሉንም የንግድ ዘርፎች በመቆጣጠር ከፍተኛ ትርፍ በማጋበስ ላይ የሚገኙ ብቻ ሳይሆን በዘረፋ የሚገኘውን ገንዘብ ከኢትዮጵያ ህዝብ በማሸሽ በውጪ አገር ባንኮች በማካበት ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። ወደ ጎረቤት አገሮች በመላክ ከፍተኛ ትርፍ የሚያስገኘውን የጫት ንግድ በሽርክና ስም ገብታ የተቆጣጠረቺው የዘረኛው መለስ ዜናዊ ባለቤት አዘብ መስፍን የቡናውንም ንግድ ለመጠቅለል በስውር እየተንቀሳቀሰች እንደሚትገኝ ከአድስ አበባ ነጋዴዎች ምክር ቤት አካባቢ የተገኘ መረጃ አጋልጦአል። አዜብ መስፍንና አብረዋት የዘረፋ ተባባሪ የሆኑ የንግድ ሸሪኮቿ ወደውጪ የሚልኩዋቸውን ምርቶች ከአምራቹ በርካሽ ዋጋ ለመሸመት እንዲያመቻቸው በተለያየ ጊዜ የአለም ገበያ ላይ ይህ ምርት ዋጋው ወድቆአል የሚል የሃሰት መረጃ በማሰራጨት ከድሀው ገበሬ ምርቱን እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ እንደሚሰበስቡ ይታወቃል:: ባለፈው አመት መጨረሻ ገደማ ወደ ውጪ ይላካል ተብሎ ተዘጋጅቶ የነበረ ከ10000 አስር ሺ ቶን በላይ ቡና ከነበረበት መጋዚን ወጥቶ የት እንደደረሰ ሳይታወቅ እንደቀረና በቅርቡ ተመሳሳይ መጠን ያለው ቡና በአዜብ መስፍን ት ዕዛዝ በድብቅ ከአገር ወጥቶ እንደተሸጠ እንደተደረሰበት ይህ መረጃ ያገኙ የፓርላማ አባላት በስብሰባ ላይ ጥያቄ አቅርበው መለስ ዜናዊ ያለፈው አልፉዋል ከንግዲህ እንዲህ አይነት ህገወጥ ተግባር አይደገምም በማለት ተናግሮ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።
ከድሀው ህዝብ ጉሮሮ ላይ እየነጠቁ በውጭ ሀገራት ባንኮች የሚያከማቹትን ሀብት የት ሊበሉት አስበው ነው በማለት አስተያየቱን የሰጠ አንድ ዘጋቢያችን ያናገረው የአዲስ አበባ ወጣት እነመለስ ሰሞኑን እንኩዋን አምባገነን ጉዋደኞቻቸው ላይ እየደረሰ ከለው ውድቀት መማር አለመቻላቸው አስገርሞኛል። እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ግን በዚህ ሁኔታ እንደማይቆዩ በሚገባ የተረዱ መሆኑን ሲሆን ለዚህም ሰሞኑን በየከተማው የሚያደርጉት ግርግር በቂ መረጃ ነው። ጥያቄው መቼ የሚለው ነው እንጂ ፡ ግፉ ዝርፊያውና መከራውማ ከሚገባው በላይ አንገሽግሾናል በማለት አስተያየቱን ገልጾአል።