የእስልምና እምነት ተከታዮች በጂማ ክርስትያኖች ላይ እያደረሱ ባሉት ወንጀሎች የወያኔ እጅ እንዳለበት ታወቀ
ህዝብን በዘር በሃይማኖትና በጎሳ በመከፋፈል የስልጣን እድሜውን ማራዘም ስራየ ብሎ የተያያዘው ዘረኛው የወያኔ አምባገነን አገዛዝ፡ በቱኒዚያ የተነሳው ህዝባዊ አብዮት በኢትዮጵያችን ሊነሳ ይችላል ከሚል ስጋት ለዘመናት ተፋቅሮ እና ተከባብሮ በሚኖረው የሙስሊሙና ክርስቲያኑ ህብረተሰብ መካከል ሆን ብሎ ግጭቶችን እየቀሰቀሰ መሆኑን ለሥር ዓቱ ቅርበት ያላቸው የግንቦት 7 ታማኝ ምንጮች ገለጹ።
ቀደም ሲል በአገዛዙ ሥር ባሉ ሚዲያዎችና ታላላቅ ስብሰባዎች ሳይቀር በወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ይነዛ የነበረው ጸረ አማራ ቀሳቀሳ እንደታሰበው አማራውንና የተቀረውን ህዝብ ሆድና ጀርባ ሊያደርግ እንዳልቻለ ወያኔ በምርጫ 97 ከደረሰበት ሽንፈት ልምድ ካገኘ ወዲህ ፡ የብሄረሰብን ልዩነትን ማራገቡን ለወጥ አድርጎ በሃይማኖቶች መካከል ውጥረት መፍጠር እንደቀጠል ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል። በአዲስ አበባ እና ሌሎች ትላልቅ ከተሞች የመስጊድ ወይም የቤቴክርስቲያን መስሪያ ቦታ ሁለቱን ሃይማኖቶች ሊያራኩት በሚችል ሥፍራ እያስቀመጠ የተለያዩ ግጭቶችን ሲቀሰቅስ የቆየው ዘረኛው የመለስ ዜናዊ ቡድን የአንዱ ሃይማኖት አስተማሪ የሌላውን ዕምነት በአደባባይ እንዲያጥላላ ወይም እንዲያንቋሽሽ ሲያደርግ እንደነበረ የተለያዩ አገር ውስጥ የሚታተሙ ጋዜጦች አጋልጠዋል።
ህዝብ በወያኔ የ20 አመት አገዛዝ ክፉኛ በመማረሩ እና ለካድረዎችና ለወያኔ ጄሌዎች አልታዘዝም ማለት በመጀመሩ ሰሞኑን በሰሜን አፍርካ የታየው አይነት ህዝባዊ አብዮት ይነሳብኛል ከሚል ስጋት በህዝብ መካከል መተማመንና የአላማ አንድነት እንዳይኖር ለጂማ ከተማ ቅርብ በሆነቺው አሰንዳቦ ከተማ ሙስሊሞች ተነስተው ቤቴክርስቲያን በእሳት እንዲያጋዩና ክርስቲያኖችን አካባቢውን ለቀው እንዲጠፉ የወያኔ አጋር በሆኑት የክልሉ ባለሥልጣናት አማካይነት እየተሰራ መሆኑን መረጃ ምንጮቻችን አጋልጠዋል።
ይህ በጂማ እና አካባቢው እየተባባሰ ያለውን የሃይማኖት ግጭት ለማስቆም ወያኔ አስከ ዛሬ የወሰደው ምንም እርምጃ እንደሌለ የሚናገሩ ምንጮቻችን በአስንዳቦ ወረዳ ብቻ ከ7 ሺህ በላይ ክርስቲያኖች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል። የግንቦት7 ዘጋቢ በግጭቱ የተፈናቀሉትን የጥቃቱን ሰለባዎች አጝኝቶ ያነጋገረ ሲሆን ግጭቱ በህይማኖት ምክንያት የተነሳ ይሁን እንጂ ወያኔ ህዝብን በመከፋፈል ለመግዛት ያለውን አጀንዳ ለመተግበር ሆን ብሎ እርስ በርስ እንደሚያጋጫቸው ከረጅም ጊዜ ጀምሮ እንደሚያውቁ እንደነገሩት አስታውቆአል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና የአራት ኪሎ ነዋሪዎች ከወያኔው ሆድ አደር ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ጋር መጋጨታቸው የተገለጸ ሲሆን የአለም ገና ነዋሪዎች ደግሞ የከተማው ከንቲባ ጋዝ ተርከፍክፎበት ካልተቃጠለ አንረካም ማለታቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቲለኢቪዥን ኢሳት በዘጋብው ላይ አሳይቱአል::
ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡን ያናገርናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ የፖለቲካ ፓርቲ አባል በስልክ በሰጡን አስተያየት በጋሞጎፋ፣ አዋሳና፣ ጂማ እየተከሰቱ ያሉ ግጪቶጭና ህዝባዊ አመጾች ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ለከት ያጣ ግፍ መለያ ናቸው ብለዋል:: አያይዘውም ዘረኛና ከፋፋዩ አጋዛዝ እንዲህ አይነት ግጪቶችን ራሱ እንደሚያስነሳና ኢትዮጵያዊያን በነኝህ አነስተኛ ችግሮች ትኩረት በማድረግ ስርአቱ እያደረሰ ያለውን መረን የለቀቀ በደል እንዲረሳ፣ እርስ በርሱ በማጋጨት እንዲከፋፈል እንደሚያደርግ ገልጸው፣ በውጪ ሃገራትም ሆነ በሃገር ውስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን አሁን የተገኝውን አጋጣሚ በአግባቡ ልንጠቀምና ዘረኛውን አገዛዝ ከትከሻችን አሽቀንጥረን ለመጣል በአንድነት የመቆሚያ ጊዚያችን ነው ብለዋል።