ዓለም አቀፍ የስካውት አውደ ጥናት በመቀሌ ተካሄደ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የስካውት ማህበር ተመስርቷል።
የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የስካውት ስብሰባ በመቀሌ ከተማ ተካሂዷል። በዩኒቨርስቲ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የተማሪዎች ስካውት ቅዳሜ ዕለት ተቋቁሟል።በኢትዮጵያ ስካውት እንቅስቃሴ ከአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግሥት እንደተጀመረ ይታወቃል። ይሁንና በትምህርት ቤቶች ከሁለተኛ ደረጃ በላይ አላለፈም ነበር።
በአሁኑ ወቅት እንቅስቃሴውን ወደዩኒቨርስቲዎች ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው። እናም ሰሞኑን የትግራይ ስካውት ማህበር ከዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ጋር በመሆን ባዘጋጁት ዓለም አቀፍ የስካውት አውደ ጥናት የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የስካውት ማህበር ተመስርቷል።