ሞቃዲሾ ሁለት የቦምብ ፍንዳታዎች አስተናገደች::
#SahafiHotelAttack #Mogadishu – በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በአንድ ሆቴል ደጃፍ ላይ በመኪና ላይ የተጠመደ ፈንጂ ፈንድቶ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል::ይህንን ተከትሎ ወደ ሆቴሉ ሕንጻ ለመንባት በሞከሩ ታጣቂዎች እና በመንግስት ሃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኮስ ልውውጥ በርካታ አደጋዎች የተከሰቱ ሲሆን በድጋሚ …
#SahafiHotelAttack #Mogadishu – በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በአንድ ሆቴል ደጃፍ ላይ በመኪና ላይ የተጠመደ ፈንጂ ፈንድቶ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል::ይህንን ተከትሎ ወደ ሆቴሉ ሕንጻ ለመንባት በሞከሩ ታጣቂዎች እና በመንግስት ሃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኮስ ልውውጥ በርካታ አደጋዎች የተከሰቱ ሲሆን በድጋሚ …
[youtube http://www.youtube.com/watch?v=iOlP2Itf6Oc]
የህገ-ወጡ የመጅሊስ አመራሮች በዘንድሮው ሃጅ የፈጸሙት የሙስናና የዝርፊያ ወንጀል ተጋለጠ ቢቢኤን የእያንዳንዱን የመጅሊስ አመራር በዘመዶቻቸው ስም የፈጸሙትን የሙስናና ዘረፋ ወንጀል በሰነድ ና በፎቶ ግራፍ ማስረጃ አስደግፎ በተከታታይ ለህዝብ ያቀርባል መረጃ ቁጥር አንድ የህገ-ወጡ መጅሊስ ምክትል ፕሬዝዳንት ኡመር ይማም የሃጅ የዘረፋ …
የህገ-ወጡ የመጅሊስ አመራሮች በዘንድሮው ሃጅ የፈጸሙት የሙስናና የዝርፊያ ወንጀል ተጋለጠ Read more »

በማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ጥቅምት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት መምህር (አጥማቂ) ግርማ ወንድሙ፣ አያት የሚገኘው መኖርያ ቤታቸው በፖሊስ መበርበሩ ታወቀ፡፡
ፖሊስ ቤታቸውን ሲበረብር ያገኘው ነገር ባይገለጽም፣ ለተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት ማስረጃ የሚሆነውና ሌሎች ተጨማሪ ነገሮች ፍለጋ ሳይሆን እንዳልቀረ ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
መምህር ግርማ ከሁለት ወራት በፊት የእስር ትዕዛዝ ተሰጥቶባቸው እንደነበር ተጠቁሞ፣ አንድ ቀን ፖሊስ ጣቢያ አድረው ጥቅምት 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡ በወቅቱም ፖሊስ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቆባቸው ነበር፡፡ የፖሊስን ጥያቄ በመቃወም የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲፈቱ በጠበቃቸውና በራሳቸው የጠየቁ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ አልተቀበላቸውም፡፡
መምህር ግርማ የተጠረጠሩበትን የማታለል ወንጀል የፈጸሙት፣ በመስከረም ወር 2006 ዓ.ም. እንደሆነና በየካ ክፍለ ከተማ ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ ነዋሪ መሆናቸው ከተጠቆመው አቶ በላይነህ ከበደ መኖርያ ቤት ጋር የተገናኘ መሆኑ በምርመራው ተገልጿል፡፡
ፖሊስ በምርመራው እንዳረጋገጠው አቶ በላይነህ ከትዳር አጋራቸው ጋር የሚኖሩበት በ400 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ መኖርያ ቤት ነበራቸው፡፡ አቶ በላይነህ ቤታቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ካልሸጡ ሊሞቱ እንደሚችሉ መምህር ግርማ ሲነግሯቸው፣ ከፍተኛ ዋጋ ያወጣላቸው የነበረ ቤታቸውን በ800 ሺሕ ብር ለመሸጥ መገደዳቸውን የፖሊስ ምርመራ ይጠቁማል፡፡
መምህር ግርማ ቤቱን ማሸጥ ብቻ ሳይበቃቸው፣ ገንዘቡ እንዲበረክትላቸው እንዲፀለይበት እንዲሰጧቸው የተጠየቁት አቶ በላይነህ፣ ገንዘቡን መስጠታቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡ ሊፀለይበት ወደ መምህር ግርማ ቤት ተወስዷል የተባለው ገንዘብ ውሎ በማደሩ፣ አቶ በላይነህ ወደ መምህር ግርማ ቤት ስልክ ሲደውሉ ስልኩ አልሠራ እንዳላቸውና ወደ ውጭ አገር መሄዳቸውን እንደሰሙ መግለጻቸው በፖሊስ ተጠቅሷል፡፡
ተጠርጣሪው መምህር ግርማ ለፍርድ ቤቱ ከሳሻቸውን ቀይ ይሁኑ ጥቁር እንደማያውቋቸውና ሆን ተብሎ የተሸረበባቸው ሴራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የማያስከለክል መሆኑን በመግለጽ በዋስ እንዲለቀቁ ቢጠይቁም፣ ፍርድ ቤቱ አልተቀበላቸውም፡፡ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ባለመቀበል ሰባት ቀናትን በመፍቀድ ለጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

–ተጠርጣሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩና የእንግሊዝ ኤምባሲ እንዲጠየቁ አመለከቱ
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሽብር ድርጊት ወንጀል ተጠርጥረው ለተከሰሱት ለእነ ዘመኑ ካሴ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ያስተላለፈውን ትዕዛዝ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አገደው፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የሥር ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ሐምሌ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. የሰጠውን ብይን ያገደው፣ የፌዴራል ማዕከል ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝ ሲመረምር የሚያስቀርብ ሆኖ በማግኘቱ መሆኑን ባስተላለፈው ትዕዛዝ አስታውቋል፡፡
አቶ አንዳርጋቸው በመከላከያ ምስክርነት በቆጠሯቸው በእነ ዘመኑ ካሴ የክስ መዝገብ (አሥር ሰዎች) የተካተቱት አቶ አሸናፊ አካሉ፣ አቶ ደህናሁን ቤዛ፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁንና አቶ አንሙት የኔዋስ ሲሆኑ እንዲመሰክሩላቸው የፈለጉትም፣ ተከሳሾቹ ኤርትራ ሄደው ከአቶ አንዳርጋቸው ትዕዛዝና መመርያ እንደተቀበሉ ዓቃቤ ሕግ የጠቀሰባቸውን ክስ እንዲያስረዱላቸው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በወቅቱ ከሳሸ ዓቃቤ ሕግ፣ ‹‹አቶ አንዳርጋቸው በተለያዩ ጊዜያት በተመሠረቱባቸው የወንጀል ክሶች በአንዱ ዕድሜ ልክ ሲፈረድባቸው በሌላኛው ሞት ተፈርዶባቸዋል፡፡ በመሆኑም ለምስክርነት ስለማይበቁና ሕግም ስለሚከለክላቸው ቀርበው ሊመሰክሩ አይገባም፤›› ብሎ ተቃውሞ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ግን የዓቃቤ ሕግን ክርክር ውድቅ በማድረግ አቶ አንዳርጋቸው ቀርበው እንዲመሰክሩ ሦስት ጊዜያት ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፣ ማረሚያ ቤቱ የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት ሳያቀርባቸው ቀርቷል፡፡ በአራተኛው ቀጠሮ ‹‹አቶ አንዳርጋቸው ማረሚያ ቤት የሉም›› ብሎ ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በደብዳቤ ገልጿል፡፡
ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤቱ ምላሽ ተማረው የተወሰኑት ‹‹ብይን ይሰጠን›› ሲሉ፣ አቶ ደህናሁን ቤዛና አቶ ሞንዳዬ ጥላሁን ቀርበው መመስከር እንዳለባቸው በመግለጽ፣ ፍርድ ቤቱ ከውጭ አገር (የመን ሰንዓ) ይዞ ያመጣቸው ፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉና ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲጠየቁ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀው ነበር፡፡
ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በችሎት ያመለከቱትን አቤቱታ በማጠናከር፣ ጥቅምት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ጉዳያቸውን እያየው ለሚገኘው ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ጽፈዋል፡፡ ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤቱ በጻፉት ደብዳቤ እንደገለጹት፣ አቶ አንዳርጋቸው በትውልድ ኢትዮጵያዊ ቢሆኑም በዜግነት እንግሊዛዊ በመሆናቸው፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ጉዳያቸውን እንደሚከታተሉ ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉና ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲጠየቁ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው አመልክተዋል፡፡
የሥር ፍርድ ቤት በተከሳሾቹ ደብዳቤ ላይ ብይን ከመስጠቱ በፊት ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝ የመረመረው ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የሥር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳይፈጸም በማገድ፣ ያስቀርባል ባለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለኅዳር 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ነገሩ፣ ለዘመናት ከምናውቀው እውቀት የተለየ በመሆኑ ግራ ማጋባቱ አይቀርም፡፡ እስካሁን ለሕፃናት ዕድገትና ጥንካሬ ጥሩ ነው በማለት ሕፃናትን ስንመግብ የኖርነው ወተት፤ በተቃራኒው ለሕፃናት ዕድገት ጥሩ አይደለም፤ ያቀጭጫቸዋል ቢባሉ ምን ይላሉ? የሚገርም ነው!ሰሞኑን በሂልተን ሆቴል ሲካሄድ በቆየው 4ኛ የአፍሪካ የምግብና የኑትሪሽን ፎረም ላይ አንድ ተመራማሪ፤ በመርዛማ ኬሚካሎች (አልፋ ቶክሲን) ላይ ያደረጉትን የምርምር ውጤት ሲያቀርቡ፤ እግረ መንገዳቸውን የአዲስ አበባና አካባቢዋ ወተት ከመጠን በላይ መርዛማ ኬሚካል (አልፋ ቶክሲን) እንዳለው ገልፀዋል፡፡ ተመራማሪው ዶ/ር አሻግረ ዘውዱ፤ ዓለም አቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት (ILRI) ባወጣው ሪፖርት፤ በ2016 በአዲስ አበባና አካባቢዋ ባደረገው ጥናት፣ ከተሰበሰቡት 140 ናሙና ከ90 በመቶ በላይ ዓለምአቀፍ ሕግ ከሚፈቅደው በላይ መርዛማ ኬሚካል (አፍላቶክሲን M1) እንዳለው ማስታወቁን ተናግረዋል፡፡
አልፋ ቶክሲን በሻጋታ ምክንያት የሚፈጠር መርዛማ ኬሚካል ነው ያሉት ተመራማሪው፤ መርዛማ ኬሚካሉ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ቢጐዳም በሕፃናት ላይ የበለጠ ጉዳት ያደርሳል፣ መቀጨጭና መጫጫት ያስከትላል፡፡ በዕድሜያቸው ልክ ቁመታቸው አያድግም፡፡ በኢትዮጵያ 40 በመቶ ሕፃናት ቀጫጫ ናቸው፡፡ መርዛማ ኬሚካሉ ከማጫጨት በተጨማሪ ረዥም ዕድሜ ሲቆይ የጉበት ካንሰር ያስከትላል ብለዋል፡፡
አልፋ ቶክሲኖች የተለያዩ ናቸው፡፡ እህል ላይ የሚገኙትና በይበልጥ የሚታወቁት 4 ናቸው፡፡ እነሱም B1 B2 G1 G2 ይባላሉ ያሉት ዶ/ር አሻግሬ፤ እህሉ ላይ የሚገኘውን B1 አልፋ ቶክሲን የበላ ከብት በሰውነቱ ውስጥ በሚካሄደው ሜታቦሊዝም፣ B1 መርዛማ ኬሚካል ወደ M1 ይቀየራል፡፡ ኤች አይ ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንደምታስተላልፍ እናት ለልጇ ጡት ስታጠባ መርዛማውን ኬሚካል ወደ ሕፃኑ ታስተላልፋለች፡፡ ከብትም እንደዚሁ፡፡ ሕፃኑ በአልፋ ቶክሲን የሚጠቃው፣ ጡት መጥባት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ነው በማለት አስረድተዋል፡፡ ወተት ለሕፃናት ዕድገት ጥንካሬና ውፍረት ጥሩ ነው ስለሚባል ወተት እየጠጡ ያድጋሉ፤ ለአልፋ ቶክሲን እየተጋለጡ ናቸው ያሉት ተመራማሪው፤ “በወሎ ድርቅ ጊዜ የእርጐ ፈንገስ የሚባል ነገር ተፈጥሮ ነበር፡፡ የሚበላ ነገር ሲጠፋ ፈንገስ የተቀላቀለበት ምግብ በልተው፤ ጋንግሪን ተፈጥሮባቸው እግራቸው የተቆረጠ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡” ብለዋል፡፡ ዓለምአቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ያወጣውን መረጃ በተመለከተ፤ መንግስት ከኢትዮጵያ ፐብሊክ ኢንስቲትዩት፣ የደረጃዎች ምዘናና ተስማሚነት፣ የምግብ ሳይንስና ኑትሪሽን ማዕከል እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ ባለሙያዎች ጥናት እንዲያደርጉበት ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡ ውጤቱ ልክ እንደተባለው ከሆነ ምን እናድርግ? በማለት ምክክር ይደረጋል ያሉት ዶ/ር አሻግሬ፤ ልክ ካልሆነ ደግሞ ኅብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ባካበተው ሀብት ቁንጮ በመባል የሚታወቀው የደቡብ አፍሪካው ስታንዳርድ ባንክ፣ የኢኮኖሚና የባንክ ባለሙያዋን ወይዘሪት ጣይቱ ወንድወሰንን የኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤቱ ተጠሪ አድርጎ ሾመ፡፡
ወይዘሪት ጣይቱ የግዙፉ ባንክ ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን የኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ከተሾሙ ቢቆዩም፣ የጽሕፈት ቤቱ በይፋ ሥራ መጀመር በተበሰረበት ጥቅምት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ወቅት ሹመታቸው ታውቋል፡፡ ስታንዳርድ ባንክ የጽሕፈት ቤቱን አድርሻ ቦሌ አካባቢ፣ ከሞናርክ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ፕላኔት ሌን ታወር ሕንፃ ላይ አድርጓል፡፡
የስታንዳርድ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቤን ክሩገር የጽሕፈት ቤቱን መከፈት በማስመልከት እንደተናገሩት፣ ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ደንበኞቹ ድልድይ ሆኖ ይሚሠራል፡፡ ከደቡብ አፍሪካ በሚሰጠው መመርያ መሠረት ጽሕፈት ቤቱ እንደሚመራ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ የኢነርጂ እምብርት በመሆን ላይ እንደምትገኝ ያስታወቁት ክሩገር፣ ወደፊት የኃይል ኤክስፖርት የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ገቢ አስገኝ እንደሚሆንም አክለዋል፡፡
ወይዘሪት ጣይቱ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳብራሩት፣ ባንኩ ትኩረት ከሚያደርግባቸው መስኮች መካከል የኢነርጂ፣ የመሠረተ ልማት፣ የአግሪ ቢዝነስና የፍጆታ ሸቀጦች ትልቁን ቦታ ይይዛሉ፡፡ የጽሕፈት ቤቱ መከፈት ከደንበኞች እየመጣ ያለውን ጥያቄ ለማስተናገድ ስለሆነ ለጥያቄያቸው ምላሽ እንደሚሰጥ አብራርተዋል፡፡ ‹‹እዚህ የመጣነው ሰዎች እንዲያውቁን፣ ገበያውን ለመረዳት፣ የጥናት አቅማችንን ለማሳደግ፣ ነገሮች እንዴት እንደሚጓዙ ለማየትና ኢኮኖሚው እንዴት እንደሚንቀሳቀስ ለመረዳት ነው፤›› ያሉት ኃላፊዋ፣ የባንኩ ደንበኞች በዚህ አገር ለመሠማራት ቢፈልጉም ድጋፍ ለመስጠት ባንኩ ጽሕፈት ቤት ከፍቷል ብለዋል፡፡ ባንኩ ከአፍሪካ በተጨማሪ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በእስያ፣ በደቡብ አሜሪካና በሌሎችም አገሮች ደንበኞች እንዳፈራ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ተወልደው ያደጉት ወይዘሪት ጣይቱ በአሜሪካ የኢኮኖሚክስና የፋይናንስ ትምህርቶችን ተከታትለዋል፡፡ በአሜሪካ ታዋቂና ግዙፍ ከሆኑት መካከል በኒው ዮርክ ፌደራል ሪዘርፍ ባንክ፣ እንዲሁም በጂፒ ሞርጋን ባንክ በኮርፖሬት ባንክ ዘርፍ በማገልገል የካበተ ልምድ አላቸው፡፡ በኒው ዮርክ ሪዘርቭ ባንክ በነበራቸው ቆይታ ወቅት የአሜሪካ ባንኮችን ጨምሮ የዓለም የፋይናንስ ተቋማትን ቀውስ ውስጥ የከተተውን አጋጣሚ አስተናግደዋል፡፡
ከስምንት ዓመት በፊት የተከሰተው ቀውስ ሌህማን ብራዘርስ የተባለውን የአሜሪካ ባንክ የውኃ ሽታ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ የኒው ዮርክ ሪዘርቭ ባንክ በወቅቱ የተከሰተውን ቀውስ የማጣራት ተግባር እንዲያከናውን በተደረገበት ወቅት ወይዘሪት ጣይቱ የባንኩ ባልደረባ ነበሩ፡፡
ስታንዳርድ ባንክን ጨምሮ የናይጄሪያው ኤኮ ባንክ፣ የእንግሊዙ ኤችኤስቢሲ፣ የህንዱ ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ ኦፍ ኢንዲያ ጽሕፈት ቤቶቻቸውን በአዲስ አበባ ከከፈቱት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
የሩሲያ A-321 የመንደኞች አዉሮፕላን ሲና በረሃ ግብፅ ዉስጥ ዛሬ ተከሰከሰ። 217 መንገደኞች እና 7 ሠራተኞችን የጫነዉ አዉሮፕላን በደረሰበት አደጋ ተሳፋሪዎቹ እንዳልተረፉ በግብፅ የሩሲያ ኤምባሲ በፌስቡክ ገጹ ላይ መግለፁን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።
UTC 16:00 የዓለም ዜና 01.11.201500
• ወጣቶቹ ሉሲዎች ለዓለም ዋንጫ ቢያልፉም ባያልፉም መነቃቃት ፈጥረዋል • ሎዛ አበራ በዱራሜ ብዙ መሰሎችን አነቃቅታለች • ዋልያዎቹ ቻን በመግባት ታሪክ ደግመዋል ግሩም ሠይፉ በዓለም U-20 የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ለመሳተፍ 1 ጨዋታ የቀራቸው ወጣቶቹ ሉሲዎች ቢያልፉም …
ወጣቶቹ ሉሲዎች ለዓለም ዋንጫ ቢያልፉም ባያልፉም መነቃቃት ፈጥረዋል::ብሄራዊ ቡድኖቹ ከፌደሬሽኑ ውጭ በሽልማት መበረታታት አለባቸው:: Read more »
ነገሩ፣ ለዘመናት ከምናውቀው እውቀት የተለየ በመሆኑ ግራ ማጋባቱ አይቀርም፡፡ እስካሁን ለሕፃናት ዕድገትና ጥንካሬ ጥሩ ነው በማለት ሕፃናትን ስንመግብ የኖርነው ወተት፤ በተቃራኒው ለሕፃናት ዕድገት ጥሩ አይደለም፤ ያቀጭጫቸዋል ቢባሉ ምን ይላሉ? የሚገርም ነው!ሰሞኑን በሂልተን ሆቴል ሲካሄድ በቆየው 4ኛ የአፍሪካ የምግብና የኑትሪሽን ፎረም …
ከ200 በላይ ተሳፋሪዎችን ይዞ በሲናይ በረሃ ሲጓዝ የነበረው የሩሲያ አውሮፕላን መከስከሱን የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል።ኤር ባስ ኤ-321 የተሰኘው ይህ አውሮፕላን ከቀይ ባህሩ የሻርማል ሼክ ሪሶርት በመነሳት ወደ ሩሲያ እያቀና ነበር ። የአውሮፕላኑን መሰወር አስመልክቶ የተለያዩ መላምቶች ሲሰጡ ቆይተው፥ ቢቢሲ በሰበር …
ከ200 በላይ ተሳፋሪዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረው የሩሲያ አውሮፕላን መከስከሱ ተነገረ። Read more »
በባቲ ከተማ የሚገኝ አንድ የአእምሮ በሽተኛ የሆነ ልጅ ከወራት በፊት “አርዳችሃለሁ እገድላችሃለሁ” እያለ ይናገራል። በፌስቡክም ላይ ይፅፋል። እንኳን ዘንቦብሽ እንዲሉ ከፌድራል ቀጥታ ባቲ ድረስ የሄዱ ፖሊሶች ና ደህንነቶች ይህን ልጅ ለመያዝ ባቲ ከተማ ላይ ይደርሳሉ። የአካባቢው ነዋሪዎችም ልጁ የአእምሮ ችግር …
የወያኔ ዳኞች የአእምሮ በሽተኛ የሆነውን ልጅ የአይሲስ ወታደር ነኝ ብሏል ብለው ሊፈርዱበት ነው Read more »
በባህርዳር የባጃጅ ሾፌሮች አድማ መቱ የባህርዳር ከተማ የባጃጅ ሾፌሮች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በከተማው ባጃጆች ከአንድ መስመር ውጭ እንዳይሰሩ ከመከልከላቸው ባሻገር ኮንትራት ጭናችኋል በሚልና በሌሎችም ሰበቦች በየቀኑ ከፍተኛ ቅጣት ስለሚጣልባቸውና ቅጣቱ ከሚያገኙት ገቢ በላይ በመሆኑ የስራ ማቆም …
የሳተላይት ሥርጭቱ መካከለኛው ምሥራቅን፣ ደቡብ አውሮፓንና ሰሜን አፍሪቃን ያካልላል (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፳፬፤ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ አገልጋዮችዋ እና ምእመናንዋ ድምፅዋን የምታሰማበትና መረጃ የምትሰጥበት የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት እንድትጀምር ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡ ከጥቅምት 12 ጀምሮ የዓመቱን የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በማካሔድ …![]()
ግድያ ለመፈፀም ዝቷል- አቃቤ ህግ
በፌስቡክ፤ “አይኤስ ነኝ” ከሚል መልእክት ጋር የግድያ ዛቻ በማስተላለፍ የሽብር ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ የተከሰሰው ወጣት ላይ፤ የአቃቤ ህግ ከትናንት በስቲያ ምስክሮችን አቀረበ፡፡ አቃቤ ህግ ያቀረበው ክስ፣ ሰይድ መሃመድ፣ በሚያዚያ ወር 2007 ዓ.ም፤ “አይኤስ ነኝ” በማለት በፌስቡክ እንደጻፈ ይገልጻል፡፡ የአይኤስ ወታደር ነኝ … በቅርቡ በረመዳን ወር የሚታረዱትን ለመያዝ ወደ ባቲ እመጣለሁ” የሚል የዛቻ መልዕክት በግል በፌስቡክ ገፁ ላይ ለጥፏል ብሏል – አቃቤ ህግ፡፡
1ኛ የአቃቤ ህግ ምስክር፤ ከላይ የተጠቀሰው መልዕክት ላይ ሰዎች አስተያየት በሰጡበት ወቅት ይህንን መልዕክት በፌስቡክ መመልከቱን የገለፀ የአቃቤ ህግ ምስክር፤ ከአካባቢዬ ወጣቶች ጋር በመመካከር ለፖሊስ ጠቁሜያለሁ ብሏል፡፡
የባቲ ከተማ ፖሊስ መሆናቸውን የገልፁ ሌላ የአቃቤ ህግ ምስክር በበኩላቸው፣ ጥቆማ ከደረሰን በኋላ ተጠራጣሪውን በቁጥጥር ስር አውለናል ብለዋል፡፡ በተጠርጣሪው የፌስቡክ ገፅ ላይም፤ “አይኤስ ማለት እንደኔ አይነት ነው፡፡ በረመዳን ወር ለእርድ ወደ ባቲ እመጣለሁ” የሚል መልዕክት አይቻለሁ ብለዋል፡፡
በወቅቱ “ለምን ይሄን አደረግህ” ብዬ ጠይቄዋለሁ፤ እሱም፤ “እኔ ጓደኞቼን ለማስፈራራት ነው እንጂ አይኤስ አይደለሁም” ሲል መልሶልኛል ብለዋል – እኚሁ የአቃቤ ህግ ምስክር፡፡ በሚያዚያ ወር፤ አይኤስ የተሰኘው አሸባሪ ቡድን፣ በሊቢያ በርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን በሚያዝያ ወር፣ አይ ኤስ የተሰኘው አሸባሪ ቡድን በሊቢያ በርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለማውገዝ፤ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ለመሄድ እየተዘጋጀሁ እንደነበር አስታውሳለሁ፤ ተጠርጣሪው የተያዘውም በዚያኑ እለት ነው በማለት ምስክሩ ተናግረዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ነው፤ ተጠርጣሪው ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ የመጣው ተብሏል፡፡
የአቃቤ ህግ 3ኛ ምስክር የአዲስ አበባ ነዋሪ እንደሆኑ ጠቅሰው፤ ተጠርጣሪው የፌስቡክ ገፁ የራሱ መሆኑን አምኖ ሲፈርም እኔ በታዛቢነት ፈርሜያለሁ ብለዋል፡፡ በፌስቡክ አካውንቱ ላይ የተፃፈውንም መልዕክት እንደተመለከቱ ተናግረዋል፡፡
ፍ/ቤቱም የምስክሮቹን ቃል ካደመጠ በኋላ በመቅረፀ ድምፅ የተቀረፀው ምስክርነት ወደ ፅሁፍ ተገልብጦ የመዝገቡ አካል እንዲሆን ትዕዛዝ ያስተላለፈ ሲሆን ምስክርነቱን መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለህዳር 30 ቀን 2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ተከሳሹ ወጣት፤ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ እስከማገኝ ድረስ በንፁህነት የመታየት መብቴን እንዳላጣ፣ የፍርድ ሂደቱ፤ ተመልካችና ጋዜጠኛ ሳይኖር፤ በዝግ ይታይልኝ ሲል ጠይቋል በጠበቃው አማካኝነት፡
፡ ፍ/ቤቱ ግን፤ ክሱ መታየት የጀመረውና የተነበበው ተመልካቾች ባሉበት በግልፅ ችሎት መሆኑን በመጥቀስ፣ አቤቱታውን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ በተከሳሹ የፌስቡክ ገፅ ላይ የተለጠፈው መልእክት፤ “እኔ አይኤስ አይኤስ ነኝ፣ የስራ ድርሻዬም ሰውን እጅና እግሩን አንጋልዬ መያዝ ነው፤ ደሞዝ የሚከፈለኝ በያዝኩት ሰው ልክ ነው፣ የአይኤስ ወታደር ነኝ፤ በቅርቡ ወደ ባቲ ለእርድ እመጣለሁ” የሚል ነው ብሏል – አቃቤ ህግ፡፡ ተከሳሹ በበኩሉ፤ “የፃፍኩት ለቀልድ ነው” ማለቱ ተገልጿል፡፡

ታዋቂው መምህር ግርማ ወንድሙ የታሰሩት እምነትን መነሻ በማድረግ፣ በተፅዕኖ መኖሪያ ቤት በማሸጥና ገንዘብ አታሎ በመውሰድ ወንጀል ተጠርጥረው መሆኑን ፖሊስ ለፍ/ቤት ያስረዳ ሲሆን ተጠርጣሪው ግን አስተባብለዋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ዘንድ በአጥማቂነት የሚታወቁት መምህር ግርማ ወንድሙ፤ በተጠረጠሩበት ወንጀል ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለቱ ፍ/ቤቱ 7 ቀን ሰጥቷል፡፡
በተጠርጣሪው ላይ እየተጣራ ያለው የፖሊስ የምርመራ መዝገብ፤ መስከረም 2006 ዓ.ም አቶ በላይነህ ከበደ የተባሉ ግለሰብን ሃይማኖትና እምነትን መነሻ በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ ወሰን ግሮሰሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ ከሚገኝ መኖሪያ ቤቱ እስከ ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም ሸጦ ካልወጡ አስከሬናቸው መውጣቱ የማይቀር መሆኑን በመንገር ግለሰቡ ቦታውን እንዲሸጡ አድርገዋል ይላል፡፡
ግለሰቡም ከባለቤታቸው ጋር በመሆን እንደተባሉት ቤቱን በ800ሺህ ብር ይሸጣሉ፡፡
ቤቱ በተጠቀሰው ዝቅተኛ ዋጋ እንዲሸጥ ተጠርጣሪው መምህር ግርማ አስተዋጽኦ ነበራቸው ይላል የፖሊስ የምርመራ መዝገብ፡፡ ግለሰቡ ቤታቸውን ከሸጡ በኋላ ተጠርጣሪው “በራዕይ ያየሁት ቦታ “ቦሌ” አለ፤ እሱን ነው መግዛት ያለብህ፣ ቤቱ የተሸጠበትን 800ሺህ ብር አምጣና እንዲበረከትልህ ልፀልይበት” ብለው ወሰዱት፡፡ የግል ተበዳይ ገንዘባቸውን ለማስመለስ ያደረጉት ጥረት እንዳልሠመረላቸውና ከሀገር ወጥተዋል እንደተባሉ የፖሊስ ምርመራ መዝገብ ያብራራል፡፡
የግል ተበዳይ ጉዳዩ ውሎ ሲያድር ማታለል መሆኑን በመረዳታቸው በመጋቢት 2007 ዓ.ም ወር ገደማ ለፖሊስ ያመለከቱ ሲሆን ፖሊስ ከሄዱበት ሀገር እስኪመለሱ የተበዳዩን ቃልና የምስክሮችን ቃል ሲቀበል መቆየቱን ያትታል፡፡
መምህሩ በበኩላቸው፤ ከሣሽ የተባለውን ግለሰብ ጥቁር ይሁን ቀይ አንድም ቀን አይተውት እንደማያውቁ በመግለጽ ከጀርባዬ የተሴረብኝ ሴራ አለ ሲሉ ለፍ/ቤቱ ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩን የያዘው የፖሊስ የምርመራ ቡድን ከትናንት በስቲያ ተጠርጣሪውን በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ወ/ችሎት ያቀረባቸው ሲሆን ግለሰቡ በተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል ቀሪ የምርመራ ስራ ስላለኝ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ብሎ ፍ/ቤቱን ቢጠይቅም ፍ/ቤቱ የ7 ቀን ጊዜ በመፍቀድ ጉዳዩን ለጥቅምት 25 ቀጥሯል፡፡
ተጠርጣሪው ፖሊስ የተጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የተቃወሙና የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው የጠየቁ ቢሆንም ፖሊስ በዋስ ቢለቀቁ መረጃ ያሸሹብኛል በማለቱ ፍ/ቤቱ የመምህር ግርማን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አድርጓል፡፡
ጌታቸው ሽፈራው • ‹‹ስለ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ መናገር ቀርቶ ስሙንም ማንሳት በጣም ያሳፍረኛል›› • ‹‹ጀኔራል መርዕድ ንጉሴ የውጊያ መሰናዶዎቼን ለጠላት አሳልገው ሰጥተዋል • የሀገር ደህንነት መስሪያ ቤት ፈላሻዎችን በህገ ወጥ መንገድ ሲያስተላልፍ ነበር • ፕሮፌሰር መስፍንና ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ ተጠያቂ ከተደረጉት …
ሌ/ኮ መንግስቱ ኃይለማሪያም በ‹‹ኑዛዜያቸው›› በርካቶችን ለኢትዮጵያ ውድቀት ተጠያቂ አደረጉ:: Read more »
የድርቅ ሰለባ ህዝባችን መንግስት ይፋ ካደረገው ኣንድ ሚልዮን ተጠቂ ህዝብ በሁለት እጥፍ የበለጠ ነው። ሰሞኑን ኣቶ ኣባይ ወልዱ በምስራቃዊ ዞን 2 ወረዳዎች( ኣፅቢወንበርታና ክልተኣውላዕሎ)፣ ደቡባዊ ዞን( ራያ ኣላማጣና ራያ ዓዘቦ) ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ህዝቡ በግልፅ የድርቁ ሁኔታና ኣደገኝነቱ ነግሯቸዋል። በሁሉም …
አሜሪካ ስመጣ ሦስት ቦታ ያለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይማርከኛል፡፡ ላስቬጋስ ኪዳነ ምሕረትና ቅዱስ ሚካኤል፣ ዴንቨር መድኃኔዓለምና ሚነሶታ ቅድስት ሥላሴ፡፡ ሃይማኖታቸውን የተረዱ፣ ለአገልግሎት የተጉና ምራቃቸውን የዋጡ ክርስቲያኖች ያሉበት ቦታ፡፡ ወደነዚህ ቦታዎች ስመጣ ከማስተምረው የምማረው ይበልጣል፡፡ በአስቸጋሪው የአሜሪካ ኑሮና ፈተና ውስጥ የቤተ …
የአዲስ አበባ ፖሊስ መምህር ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ሥር አዋለ ሲል የገዢው መደብ አፈቀላጤ የሆነው ራዲዮ ፋና መምህር ግርማ የተባሉትን የሃይማኖት አባት በማጣጣል ዘገባ አስተላልፏል::ለመሆኑ መምህር ግርማ በሕወሓት ከሚመራው እና በሙስና ከተዘፈቀው የተዋህዶ መሪዎች ቡድን በላይ ሙስና እና ማጭበርበር ፈጽመው ነው …
ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናት ጀምሮ የአርበኞች ግንቦት7 አባሎች በሰገን ዞን ኮንሶ ወረዳ ውስጥ ገብተዋል በሚል የፖሊስ አባላት በከተማው የሚገኙ ወጣቶችን ሲያድኑ ከዋሉ በሁዋላ ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶችን ይዘው አስረዋል። በአካባቢው ሰሞኑን በፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸመ የተባለ ጥቃትና ወጣቱን የሚያነሳሱ በራሪ ወረቀቶች መበተናቸው ለአሰሳው ተጨማሪ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ነዋሪዎች …
የአሜሪካ ባለስልጣናት እንዳሉት የኦባማ አስተዳደር የሶሪያ ለውጥ ፈላጊ አማጽያንን በወታደራዊ ድጋፍ ለማጠናከር እና አይሲስ የተባለን አሸባሪ ለመዋጋት ልዩ ሃይሏን ወደ ሶሪያ መላኳን ተናግረዋል::ወደ50 የሚጠጉ የአሜሪካን ልዩ ሃይል አባላት ወደ ሶሪያ ያቀኑት የአሳድን መንግስት ተቃውመው መሳሪያ ያነሱ አማጽያንን ለማሰልጠን ለማማከር እና …
አሜሪካ ልዩ ወታደራዊ ኋይሏን ወደ ሶሪያ ስታስገባ በሶሪያ ጉዳይ ቬና ላይ ከስምምነት እየተደረሰ ነው:: Read more »
ጥቅምት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ ሰባራ ባቡር አካካቢ ከሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በመከላከያ ምስክርነት ሊቀርቡ ከነበሩት ሦስት እስረኞች መካከል፣ ሁለቱ የማምለጥ ሙከራ ሲያደርጉ አንዱ ሲገደል አንዱ ማምለጡ ተገለጸ፡፡
የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሕዝብ ግንኙነት ተወካይ ምክትል ሰርጀንት ሳህለ ገብርኤል ይትባረክ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እስረኞቹ ያመለጡት ፍርድ ቤት ደርሰው ለመውረድ ሲቃረቡ የመኪና በር በመስበር ነበር፡፡ በተለያዩ የውንብድና ወንጀሎች 31 ዓመት የተፈረደበት አንደኛው እስረኛ ሲያዝ፣ በተመሳሳይ ወንጀል የዘጠኝ ዓመት ከስድስት ወራት ፍርደኛ የሆነውና ተጨማሪ ሦስት ክሶች የነበሩበት ሁለተኛው እስረኛ ለማምለጥ ባደረገው ሙከራ ተገድሏል፡፡
እስረኛውን አሳዶ ለመያዝ ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ቢሆንም መንደር ውስጥ በመግባቱ ሁኔታዎች አስቸጋሪ በመሆናቸው፣ በመጨረሻ መተኮስ ግድ እንደነበር የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው አስረድተዋል፡፡ ‹‹እስረኛውን ረዥም ርቀት ተከታትለነዋል፡፡ ላለመተኮስ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡ ነገር ግን መንደር ውስጥ በመግባቱ የተወሰደው ዕርምጃ የግድ የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል፤›› ብለዋል፡፡
ለማምለጥ ከሞከሩት ሁለት እስረኞች ጋር በአንድ መኪና ውስጥ የነበረው ሌላ እስረኛ ለመንቀሳቀስ ምንም ዓይነት ሙከራ አድርጎ እንዳልነበር የገለጹት ምክትል ሰርጀንት ሳህለ ገብርኤል፣ ያመለጠውን እስረኛ ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ክትትሉ እየተደረገ ያለው ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጋር መሆኑንና የእስረኛው ፎቶግራፎችም መበተናቸውንም አክለዋል፡፡
አልፎ አልፎ እስረኞች ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ሲሉ የማምለጥ ሙከራ እንደሚያጋጥም፣ ነገር ግን እስካሁን አምልጦ ሳይያዝ የቀረ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ሪፖርተር የእስረኞቹን ሙሉ ስም በሚመለከት መረጃ ያለው ቢሆንም የሕዝብ ግንኙነት ተወካዩ እንዳይገለጽ ጠይቀዋል፡፡
1989 ዐም ነው የኤርትራ መንግስት “የቀይ ባህር ኮርፖሬሽን” የሚባል ግዙፍ የንግድ ድርጅተ አቋቁሞ እየሰራ የነበረበት ጊዜ ነው:: በርካሽ ዋጋ ከኢትዮጵያ የተለያዩ የግብርና ምርቶች እየገዛ ለዐለም የሚያቀርብበትና በአጭር ጊዜ በርካታ መቶ ሚልዮኖችን ማንቀሳቀስ የቻለበት ጊዜ ነበር፡፡ ከዚያ አንድ ዐመት ቀደም ብሎ …
71 የኤርትራ መንግስት “የቀይ ባህር ኮርፖሬሽን” ትራከሮች :- በአቶ ስየና በአቶ መለስ ጥልና መቃቃር ትልቁ መነሻ Read more »
ኣመፁ በወረዳው ትምህርት ፅህፈት ቤት ሓላፊዎችና የወረዳው ኣስተዳደር ላይ ያነፃፀረ ሲሆን በወረዳው የሚገኙ ከ53 በላይ ትምህርት ቤቶችያሉ ርእሳነ መምህራንና ኣስተማሪዎች የሚጠይቋቸው የእድገት፣ የዝውውር፣ የእርከን፣ የውጤት ተኮርና የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄዎች በኣግባቡ ለመመለስ ባለመቻላቸው ነው። የወረዳዋ ኣስተማሪዎች ያስነሱት ጥያቄዎች በኣግባቡ ምላሽ ሊያገኙ …
የ.ተ. መ.ድ. 3ኛ ኮሚቴ በኤርትራ ውስጥ ስለሚገኘው የሰብአዊ መብት ሁኔታ ሪፖርት አድምጧል። ሪፓርቱን በተመለከተ በመንግሥታቱ ድርጅት የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮም መልስ ሰጥተዋል።
Minilik Salsawi – የሃይል ሚዛን በጃችን ነው … ምእራባውያን ለብሄራዊ ጥቅማቸው እስከተባበርናቸው ድረስ ኢትዮጵያውያንን በፈለገው መንገድ ብንረግጥ እና ብንገዛ ተቀባይነት አናጣም … አንድ ወጥ ሃገራዊ ሳይሆን ጎሳዊ መዋቅር ዘርግተን የቀረውን ክፍል ብናሸው ብናሸብረው በራሳችን ስራ ሕዝብን ብንወነጅል ማንም ምንም የሚያመጣው …
የመብት ጥያቄዎችን በሃይል ለማድበስበስ መሞከር ፍርሃት የወለደው ፖለቲካዊ እብደት ነው:: Read more »
የወያኔ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ውስጥ የአይሲስን አራጅ ቡድን አላማ በማስፋፋት የአይሲስ የኢትዮጵያ መቀመጫን ለመመስረት ግዛታቸውን ለመገንባት ሲሉ ደርሼባቸዋለሁ ያለውን 20 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውያለሁ ሲል ተናገረ::ይህ ወያኔ ስለ አይሲስ ሕዋስ እና ግዛት መመስረት ሲናገር ለመጀመሪያ ጊዜው ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ አይሲስ የራሱን …
አይሲስ በኢትዮጵያ የራሱን መሬት ከልሎ ራስ ገዝ አስተዳደር ሲያደራጅ ደረስኩበት ሲል ወያኔ ተናገረ:: Read more »
በኤርትራ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኋላ ሊኖር ስለሚችለው የፖለቲካ ሁኔታ መናገር ለአብዛኞቹ ኤርትራውያንም ሆነ ለውጪ ታዛቢ ቀላል ጉዳይ አይደለም። ፕሬዝዳንቱ 70ኛ የልደት በዓላቸውን ለማክበር እየተሰናዱ ነው። የጤንነታቸው ሁኔታ በሀኪም እጅ ያለ ነው። ያለፉትን በርካታ አመታት በውጪ ሀገር እየተመላለሱ ህክምና አድርገዋል። እንዳውም …
“የኢትዮጵያ የፋሽን ጥበብ ባለሙያዎች ካገር ውስጥ ብርቱ እገዛ ያስፈልጋቸዋል” የቀድሞ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሞዴል አና ጌታነህ።
ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች እንደሚሉት ከድርቁ ጋር ተያይዞ የውሃ ችግሩ በመባባሱ ፣ ህዝቡ ውሃ ለማግኘት በእጅጉ ተቸግሯል። የውሃ ችግሩ በመባባሱና በየአካባቢው የሚታየው የውሃ ጀሪካም ብዛት ” ሳምንቱን ” ቢጫው ሳምንት” አስብሎታል በማለት ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የውሃ ችግሩ ከሰቆጣ በተጨማሪ በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች ይታያል። በሌላ በኩል ደግሞ ክልሉን እመራዋለሁ የሚለው …
ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአርባምንጭ ምንጮች እንደተናገሩት በቅርቡ የአርበኞች ግንቦት 7 ደጋፊዎች ኢህአዴግን የሚያወግዙና ወጣቱ ለመብቱ እንዲነሳ የሚቀሰቅሱ በራሪ ወረቀቶችን ከበተኑ በሁዋላ፣ ድርጊቱን ፈጽመዋል ብለው የጠረጠሩዋቸውን ወጣቶች በጅምላ ለማሰር ከትናንት ጀምሮ አሰሳ አካሂደዋል። አሰሳውን ተከትሎ የ70 አመት አዛውንት እናትን ጨምሮ ሴቶችና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተይዘዋል። ከተያዙት መካከል የሰማያዊ …
Minilik Salsawi – የደህንነት አባላት ግምገማ በጌታቸው አሰፋ ሰብሳቢነት ቀጥሏል::ትላንትና ቀዝቀዝ ብሎ የተጀመረው ግምገማ ዛሬ ላይ ተሟሙቆ የዋለ ሲሆን የደህንነት አባላቱን ከስራ የማፈናቀል ለእስር የመዳረግ እና ከደረጃ ዝቅ የማድረግ ውጤቶችን ግምገማው እንደሚወልድ ይጠበቃል::ትላንትና በሁለት የደህንነት አባላት ሞባይል ላይ የተጀመረው ግምገማ …
የደህንነት አባላቶች ስልኮቻቸውን የሚጠቀሙት የተቃዋሚዎችን ዘገባ በማየት እና በማሰራጨት ነው በሚል ተገመገሙ:: Read more »
የወያኔ ደህንነት ስብሰባና ግምገማ ተጀመረ ፍሪደም ሀውስ (Freedom House) አመታዊ ዘገባውን አወጣ የአምስቱ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተላለፈ የአቮሪ ኮስት ፕሬዚዳንት በድጋሚ መመረጣቸው ተነገረ የናይጄሪያ መንግስት ቦኮሃራም ይዟቸው የነበሩ ዜጎችን አስለቀቀ በመካከለኛው አፍሪካ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች በፈጠሩት ግጭት …
ሚስጥራዊ መረጃው እንደሚያመለክተው ከሆነ በዛሬው እለት የተቋሙ ጀነራል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ጎን በሚገኘው ቢሮአቸው የተቋሙን ከፍተኛ አመራሮችን ትዕዛዝ ለመስጠት መሰብሰባቸውንና በስብሰባውም ዳይሬክተሩ ተቋሙ ከጥቂት ወራቶች በፊት ብዛት ያላቸው አዳዲስ አባላትን መቅጠሩን እና ወደ ስራ ማሰማራቱን …
ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ቢሮ 16 የደህንነት አባላት እና አመራሮችን በስውር በቁጥጥር ስር ሊያውል ዝግጅት መጀመሩን ተጋለጠ። Read more »
ትናንት ጥቅምት 17/2008 ዓ.ም ከሌሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ በርካታ የአርባ ምንጭ ነዋሪዎች በአፈሳ እየታሰሩ መሆኑን የነገረ ኢትተጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከነዋሪዎቹ መካከል የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎችም ታስረዋል፡፡ ከአስተባባሪዎቹ መካከል አቶ ሉሉ መሰለ፣ ባለቤታቸውና ልጃቸው ሌሊት 8 ሰዓት ላይ የታሰሩ ሲሆን …
በአርባምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ የአርባምንጭ አስተባባሪዎችና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በርካታ ዜጎች መታሰራቸው ታወቀ Read more »
ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኑዌር ዞን ዋና ከተማ ከሆነቸው ንያንግ 30 ኪሜ ራቅ ብሎ በሚገኘው የህንዱ ካራቱሪ ኩባንያ አጠገብ በሚገኘው አንዱራ የአነስተኛ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ሲፐርቪዥን ኢንተርፕራይዝ ሰራተኛ የሆኑት ኢንጂር ሙሉጌታ ደሳለኝ እና የጋምቤላ የእርሻ ቢሮ ሰራተኛ የነበሩት ወ/ሮ ሃይማኖት ተገድለዋል። …
ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ በሽብረተኝነት ወንጀል የተከሰሱት አቶ ደህናሁን ቤዛና አቶ ምንዳዬ ጥላሁን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ቀርበው እንዲመሰክሩ ፍርድ ቤቱ ለተለያዩ አካላት ደብዳቤ እንዲጽፍላቸው ለልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት በድጋሜ ደብዳቤ ጽፈዋል። ቃሊቲ እስር ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፣ ቃሊቲ አለመታሰራቸውን ጥቅምት 12 ፣ 2008 ዓም …
ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ገዳሪፍ አቅራቢያ በተቀሰቀሰ ውጊያ 16 ሱዳናዊያን መገደላቸውን፣ 12 መቁሰላቸውን እንዲሁም 7ቱ ታግተው መወሰዳቸውንና የደረሱበት እንደማይታወቅ ከ300 በላይ የቁም ከብቶችም መዘረፉን የቀድሞው የአገሪቱ ጦር አዛዥና የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ለፓርላማ ሪፖርት አቅርበዋል። ኢስማት አብዱረሕማን ” ሽፍቶች” ያሉዋቸው መሬታችንን አሳልፈን አንሰጥም ያሉ የኢትዮጵያ አርሶ …
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ መርማሪ ቡድን ዛሬ ግለሰቡን በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የወንጀል ችሎት አቅርቧቸዋል።ፖሊስ ግለሰቡ በተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል ቀሪ የምርመራ ስራ ስላሉብኝ ተጨማሪ 14 ቀን ይፈቀድልኝ ብሏል።ተጠርጣሪው በራሳቸውና በጠበቃቸው በኩል ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ …
በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር “የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!” የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን “አልሄድም” ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና […]![]()

ፍሪደም ሃውስ (Freedom House) መቀመጫውን እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገና በመናገር ነጻነት ላይ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው፡፡ይህ ተቋም መንግሥታት ለሕዝቦቻቸው የሚሠጡትን የኢንተርኔት ነጻነት አጥንቶ እያንዳንዱ ሀገር ያለበትን ደረጃ ‹‹Freedom on the net 2015 ›› በሚል ርዕስ ስር ሪፖርት አውጥቷል፡፡ በዚህ ሪፖርት ሰንጠረዥ‹‹ኢትዮጵያ ከቻይና፣ከሦሪያ እና ከኢራቅ ቀጥሎ ምንም ዓይነት የኢንተርኔት ነጻነት የሌለባት አገር ተብላለች፡፡ Listen
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር በትጥቅ ትግል መንግስት ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ኃይሎች ውጤት አያመጡም ብለዋል። በአሥመራ የሚገኘውን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጨምሮ የሁለት ድርጅቶች ምላሽ ሰጥተዋል።
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፣ “የአመጹ ወጣቶችን አጋልጡ” በሚል የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግለሰቦች ቤት እየገቡ አዛውንቶችን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን እየደበደቡ ሲያስሩ ከሰነበቱ በሁዋላ ትናንት ከምሽቱ ሶስት ሰአት ጀምሮ፣ ከጫካ በመጡ ወጣቶችና በመከላከያ ፖሊስ አባላት መካከል ለሰአታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። ኢሳት ከተለያዩ ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ከቴፒ 7 ኪሎሜትር …
ለጤንነትዎ ያንብቡ : ካንሰርን የሚከላከሉ ሰባት ምግቦች .. Health – SEVEN FOODS THAT PREVENTS CANCER. አበባ ጎመን :ካሮት : ዓቡካዶ ; ቲማቲም …… http://betinews.com/?p=3825
በስልጤ ዞን በሁልባራግ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የሂጃብ ገፈፋውን በመቃወም በአደባባይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ተገለፀ በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን የሂጃብ ገፈፋው ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በከተማው ህዝበ ሙስሊም እና በመንግስት ሃይሎች መካከል ግጭት እየተፈጠረ መሆኑ ታውቋል፡፡ በስልጤ ዞን የሚገኙ የተለያዩ …
በስልጤ ዞን የሂጃብ ገፈፋውን በመቃወም በአደባባይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ተገለፀ:: Read more »