መንግስት በርሃብ ለተጠቁት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ታወቀ • በርሃብ የተጠቁት ዜጎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው • ‹‹ሰው በርሃብ እያለቀ ነው›› • ‹‹የሚላስ የሚቀመስ የለም፡፡ ቤተሰባችን ፈርሷል›› • ‹‹እርዳታ ቢሰጥማ ከዚህ ድረስ አንመጣም ነበር፡፡›› መንግስት በርሃብ ለተጎዱት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ …

መንግስት በርሃብ ለተጠቁት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ታወቀ • በርሃብ የተጠቁት ዜጎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው Read more »

  Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተለያዩ አይነት የሙስና ወንጀሎች ሲሰሩ በጉምሩክ እና ገቢዎች መስሪያ ቤትን የሙስና ወንጀል የለም ብሎ ባይካድም ከጥቅማቸው ይልቅ የሕዝብ አደራ አንበላም የሚሉ ሰራተኞች ለሕወሓት ስውር እጆች አንታዘዝም በማለታቸው በሙስና ስም ጥቃት እየደረሰብን …

ለሕወሓት ስውር እጆች ታዛዥ ስላልሆንን እየተጠቃን ነው ሲሉ የጉምሩክ ሰራተኞች ይናገራሉ:: ‪ Read more »

ተወዳጅ የማህበራዊ ሚዲያ የሆነው ፌስቡክ አገልግሎቶቹን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያዘመነ እና አዳዲስ መተግበሪያዎችን እያስተዋወቀ ይገኛል። በቅርቡ አዲስ የቪዲዮ ማጫወቻ አገልግሎት ማስታወቁም ይታወሳል። ታዲያ ፌስቡክ ገፃችን ላይ የሚመጡ እና የወደድናቸውን ቪዲዮዎችን ቀለል ባለ መንገድ እንዴት አውርደን ለራሳችን መያዝ እንችላለን የሚለውን እንመከለታለን። …

ፌስቡክ ገፃችን ላይ የሚመጡ እና የወደድናቸውን ቪዲዮዎችን ቀለል ባለ መንገድ እንዴት አውርደን ለራሳችን መያዝ እንችላለን ? Read more »

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወሳኝነታቸውን ያሳዩበት መድረክ

በኢትዮጵያ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እስከዛሬ ሲደረጉ ከነበሩ ከንግግር ያልዘለሉ የቁርጠኝነት ማሳያዎች አንድ እርከን የዘለለ እንደሆነ የተነገረለት በጥናት ላይ የተመሠረተ ውይይት፣ በቅርቡ በመንግሥት ከፍተኛው አስፈጻሚ አካል ተካሂዷል፡፡

ይህ ለሕዝብ ከወትሮው በተለየ በከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ወቀሳና ተጠያቂነትን ያስነሳው ውይይት፣ መነሻ ምክንያቱ ታች መሬት ተወርዶ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ የዳሰሳ ጥናት መካሄዱ ነው፡፡ የጥናቱ አቅራቢዎች በውይይቱ ወቅት የችግሩን ስፋትና መጠን ሲያስረዱ፣ ለወትሮው የሐሳብ ልዩነቶቻቸውን ከመጋረጃ በስተጀርባ በመጨረስ ለሕዝብ አንድ ሆነው በመቅረብ የሚታወቁት የኢሕአዴግ ቱባ ባለሥልጣናት፣ በአደባባይ ልዩነቶቻቸውን በግልጽ ያወጡበት ውይይት እንደነበር ታይቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአገሪቱ ቁንጮ ባለሥልጣን ሆነው ከመጡበት ጊዜ  ጀምሮ፣ በግልጽ የሥልጣን ባለቤትና የገዥው ፓርቲ አቅጣጫ የመወሰን ሥልጣን እንዳላቸው ያሳዩበትም ነበር፡፡ በተለይ በመሬት፣ በኢንቨስትመንት፣ በፍትሕና በተለያዩ መስኮች በጥናቱ የቀረበው አሳሳቢ ሥጋት ካልተወገደ አደገኛነቱንም በማስጠንቀቅ አውስተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፅንኦት በመስጠት ለአገሪቱም ሆነ ለሕዝቡ አደገኛ የሆነውን የመልካም አስተዳደር ችግር መታገል የሕዝብ አመኔታን እንደሚያስገኝ አስታውቀው፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትም በውስጣቸው መደንገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ከውይይቱ በኋላ ባለሥልጣናት በብሔር፣ በዝምድና፣ በጥቅማ ጥቅምና በመሳሰሉት ከተሳሰሯቸው ኔትወርኮቻቸው እንዲላቀቁም አስጠንቅቀዋል፡፡ ዝርዝሩን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ ወይም በ ፖለቲካ ገጽ ይመልከቱ፡፡

 

ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት መግባባትና መተባበር ሊቀመንበር የሆኑት የአቶ ፈንታሁን ብርሃኑ የ13 አመት ሴት ልጅ በአንድ ወጣት በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ ስትገደል፣ ሌላው የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ አበራ ሃይለማርያምም በዚሁ ወጣት ተገድለዋል። አቶ ፋንታሁን ለኢሳት እንደተናገሩት ጎረቤታቸው የሆኑት አቶ አበራ የተገደሉት ምናልባትም ጩኸት ሰምተው ልጃቸውን ለመታደግ በመሞከራቸው ሳይሆን …

ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታይዋን በሚባለው አካባቢ ይሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች፣ ሆን ተብሎ በተቀሰቀሰ እሳት ድርጅታቸው እስከ ሙሉ ንብረታቸው እንደወደመባቸው ለኢሳት ተናግረዋል። ድርጊቱ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ የተፈጸመ ሲሆን፣ መንግስት በአካባቢው ለሚያሰራው መንገድ ድርጅቶችን በማቃጠል ካሳ እንዳይከፍል ለማድረግ ነው በማለት ነዋሪዎች ተናግረዋል። በቃጠሎው ከ15 በላይ የንግድ ድርጅቶች የወደሙ ሲሆን፣ ፖሊሶች ህዝቡ …

በፌዴሬሽኑ ተልካሻ አሰራር ስህተት የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ታገደ ፌዴሬሽኑ በሚሰራው ተደጋጋሚ ስህተት ትምህርት የሚሰጥ እርምጃ መወሰድ አለበት !!! በፌዴሬሽኑ ተልካሻ አሰራር ምክንያት የኢትዮጵያ ሴቶች ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያውጭ ሆነ በወንዶች ብሄራዊ ብድን ቢጫ ካርድ ትምህርት ያልወሰደው የኢትዮጵያ የእግር …

በፌዴሬሽኑ ተልካሻ አሰራር ስህተት የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ታገደ Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

የጀርመኑ ኮሜርስ፤የዩናይትድ ስቴትሱ ሲቲ እና የኬንያው ንግድ ባንኮች በአዲስ አበባ ቢሮ የመክፈት እቅድ ሰንቀዋል። በኢትዮጵያ ቢሮዎቻቸውን የከፈቱት የውጭ ኩባንያዎች ግን በዘርፉ ያለምንም ገደብ የመስራት ፈቃድ የላቸውም።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከህገ መንግስቱ ጀምሮ አዋጅና በሌሎችም የዜጎችን መብት የሚደነግጉ በርካታ መሰረቶች ቢኖሩም ለይስሙላ ህጋዊ ሥርዓት እንዳለ ከማስመሰልም አልፎ ለአገዛዙ ማጥቂያና መግዢያ ከመሆን ባለፈ የዜጎችን መብት እያስከበሩ አይደለም፡፡ ባለፉት 6 ወራት እንኳን ህግ እንደተቀበረች፣ በዚሁ አገዛዙ ውስጥ ተፅዕኖ ያለው የፍርድ …

ከነካባው የተቀበረውን የፍትህ ሥርዓት ነፃ ለማውጣት ትግላችን አጠናክረን እንቀጥላለን! (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ) Read more »

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የእጅ ስልክ ባልታወቁ ሰዎች እጅ የገባ ሲሆን ኢንጂነር ይልቃል በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሃገር ላሉ አባሎቻቸው እና ደጋፊዎቻቸው የሚቀጥለውን ማሳሰቢያ አስተላልፈዋል:: ማሳሰቢያ :- የእጅ ስልክ (ሞባይሌ) ባልታወቁ ሰዎች እጅ ስለገባ ከዛሬ ጥቅምት 24/2008 …

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል የእጅ ስልክ ባልታወቁ ሰዎች እጅ ገባ:: Read more »

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት የነበሩት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ፣ በማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ ክሱ ቀደም ብሎ በ1998 ዓ.ም. ተመሥርቶባቸው የነበረ ቢሆንም፣ እንዲቋረጥ ተደርጎ ከቆየ በኋላ የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ በነበሩት አቶ ልዑል ወልዱ (አሁን የትግራይ  ክልል ፍትሕ ቢሮ …

የቀድሞ የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ‹‹አርበኛ ሳይሆኑ አርበኛ ነኝ›› በማለት በማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ተከሰሱ Read more »

ወያኔ ምክረ ሃሳብ ይበለው እንጂ የፖሊሲ ማሻሻያ የቀለበው ቀጥታ መሆኑ ታውቋል:: -በግል ባንኮች ላይ የተጣለው የቦንድ ግዥ እንዲነሳ ጠይቋል -የታክስ ነፃ መብቶች እንዳይሰጡ ብሏል -የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አለበት ብሏል የዓለም ገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ፣ …

የዓለም ገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለወያኔ አዲስ የፖሊሲ ማሻሻያ አቀረበ:: Read more »

  Minilik Salsawi – ስካቢስ የተሰኘ ወረርሽኝ በምሥራቅ ጎጃም፣ በሰሜን ጎንደር፣ በደቡብ ወሎና በዋግ ህምራ ዞኖች በሚገኙ 20 ወረዳዎች ላይ መከሰቱን የተባበርት መንግስታት ድርጅት ያስታወቀ ሲሆን ከፍተኛ የሰብኣዊ ቀውስ ያስከተለውን የድርቁን ሁኔታ ሽላ በማለት አጣብቂኞቻቸውን ለማላላት ደፋ ቀና የሚሉት ባለስልጣናት …

ወገን በወረርሽኝ በሽታ እያለቀ ነው:: የድርቁ ሁኔታ ከመባባሱ አልፎ ከንጽህና ጋር የተያያዙ እና ውሃ ወለድ በሽታዎች ተስፋፍተዋል:: ‪ Read more »

ጥቅምት 20 ለ21 አጥቢያ 2008 ዓ.ም. የልጃቸውን ጓደኛ በሽጉጥ ተኩሰው በመግደል የተጠረጠሩ ሐኪም፣ ከነመሣሪያቸው በቁጥጥር ሥር ውለው እየተመረመሩ መሆኑ ታወቀ፡፡በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 13/14 ልዩ ሥፍራው ማጂክ ካርፔት በሚባለው ትምህር ቤት አካባቢ የተገደለው ወጣት ቴዎድሮስ ሲሳይ ይባላል፡፡ ቴዎድሮስ ከጓደኞቹ ጋር …

የልጃቸውን ጓደኛ በመግደል የተጠረጠሩት በሰላም ከፍተኛ የጥርስ ክሊኒክ የጥርስ ሐኪም ታሰሩ Read more »

አቃቢ ሕጎች ሆን ብለው ተገበዉን ሕግ ጠቅሰው አይከሱም :: ምስክሮች ማስጠናት፣ በግድ “ይሄን መስከር ተብሎ ማስፈራራት፣ ካልመሰከርክ እዚህ ትከርማታለህ፣ አንተም ትታሰራልህ” የማለት ነገር አለ:: ከፍተኛ አመራር ጣልቃ ገብነት አለ። ይሄን ፋይል ዝጋ፣ ምርመራም ከተጀመረ አቁም፤ እንባላለን፣ የሚል ራሳቸው ባለሞያዎቹ የሚያነሱት …

VIDEO : አቃቢ ሕጎች ሕግ ጠቅሰው አይከሱም ምስክሮች ማስጠናት፣ በግድ “ይሄን መስከር ተብሎ ማስፈራራት፣ ካልመሰከርክ እዚህ ትከርማታለህ፣ አንተም ትታሰራልህ” የማለት ነገር አለ: Read more »

የ54 አመቱ አሪክ የተባለ እስራኤላዊ መንገደኛ ከቻድ ወደ አዲስ አበባ በሚሄደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ላይ እያለ በአንድ ሱዳናዊ ተሳፋሪ የግድያ ሙከራ ተደረገበት። ሱዳናዊ አህመድ መሃመድ የተባለው አጥቂ በቁጥጥር ስር ውሎ ዛሬ በአዲስ አበባ ለፍርድ ቀርቧል:: [youtube http://www.youtube.com/watch?v=4CT4hOXtlpk]   An …

እስራኤላዊ መንገደኛ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ላይ እያለ በሱዳናዊ ተሳፋሪ የግድያ ሙከራ ተደረገበት ። Read more »

የኦፌኮ/መድረክ ከፍተኛ አመራር ዶክተር ሞጋ ፉሪሳ ስለኢትዮጵያዊነት ስለጎሳ ፖለቲካ እና ወቅታዊ ሁኔታዎች ይናገራሉ:: http://www.1ethiopia.net/v/esat-yesamintu-engida-interview-with-dr-moga-frissa-about-current-and-ethnic-politics  

በአማራ ክልላዊ መንግሥት በድርቅ በተጠቁ በተለያዩ ዞኖች የተከለሉ ውኃ ምንጮች ውስንነት፣ ከንፅህና ጋር ለተያያዙ በሽታዎች መፈጠር ምክንያት መሆኑ ተገለጸ፡፡ 

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በዚህ ሳምንት በወጣው ሪፖርት፣ ‹‹ስካቢስ›› የተሰኘ ወረርሽኝ በምሥራቅ ጎጃም፣ በሰሜን ጎንደር፣ በደቡብ ወሎና በዋግ ህምራ ዞኖች በሚገኙ 20 ወረዳዎች መከሰቱን አስታውቋል፡፡ በዋግ ህምራ ዞን ብቻ 88,905 ግለሰቦች በወረርሽኙ መያዛቸው ታውቋል፡፡ የጤና ጥበቃ  ሚኒስቴር በበሽታው ለተጠቁ ሥፍራዎች መድኃኒቶችን በመላክ ላይ መሆኑን የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ የችግሩ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ የተለያዩ ዘርፎችን ትብብር የሚጠይቅ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡ 

በሽታው ተዛማች በመሆኑ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተጀመረው ጥረት በአፋጣኝ ተስፋፍቶ መቀጠል እንደሚኖርበት የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ ወረርሽኙ የተከሰተው ከድርቁ ጋር ተያይዞ እንደሆነ በሪፖርቱ አስፍሯል፡፡ 

ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ በምግብ እጥረት የተጎዱ ሕፃናት ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ የምግብ ፕሮግራም የሚያስፈልጋቸው ሕፃናት ቁጥር ከሌላው ጊዜ በ20 በመቶ መጨመሩን፣ የተጎጂዎቹ ቁጥር በየወሩ እየጨመረ መሄዱን ጽሕፈት ቤቱ በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

በመስከረም ወር የተመዘገቡ በምግብ ዕጦት የተጎዱ ሕፃናት ቁጥር 35,216 የነበረ ሲሆን፣ በነሐሴ ወር ከተመዘገቡት 43,391 ሕፃናት የ19 በመቶ ቅናሽ ያሳየ ቢሆንም፣ በአገር አቀፍ ደረጃ በመስከረም ወር የተመዘገበው በምግብ ዕጦት የተጎዱ ሕፃናት ቁጥር ከሌላው ማንኛውም ዓመት የ20 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ 

ከፍተኛው ቁጥር የተመዘገበው በአማራ ክልል እንደሆነ የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ በየወሩ በክልሉ 6,489 በምግብ ዕጦት የተጎዱ ሕፃናት ወደ ምግብ ፕሮግራም እንደሚገቡ ጠቁሟል፡፡ 

በኤልኒኖ ምክንያት በተፈጠረው አየር መዛባት የተከሰተው ድርቅ እየተባባሰ መምጣቱን ጠቅሶ፣ እየጨመረ የመጣውን የምግብ ዕርዳታ ፍላጎት መጠን ለማሟላት የኢትዮጵያ መንግሥት ተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም አጥጋቢ ምላሽ አለመገኘቱን አስታውቋል፡፡ እ.ኤ.አ. የ2015 እና የ2016 የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ፍላጎት ማሟላት የሚያስችል የገንዘብ ምንጭ አለመኖሩ አሳሳቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ እ.ኤ.አ. ለ2016 የሚያስፈልገው ዕርዳታ በአስቸኳይ መገኘት እንዳለበት የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ ዕርዳታውን አጓጉዞ ከሚፈለገው ሥፍራ ለማድረስ ከሦስት እስከ አምስት ወራት ቀድሞ መዘጋጀት እንደሚኖርበት ጠቁሟል፡፡ 

መንግሥት ከለጋሾች የሚፈለገውን ያህል የገንዘብ ድጋፍ ባለማግኘቱ ሁኔታዎች በከፉበት አካባቢ በራሱ ወጪ ዕለታዊ ዕርዳታዎች በማድረግ ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ 

ከመንግሥት የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት 50,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴና 300 ሜትሪክ ቶን የምግብ ዘይት በመከፋፈል ላይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ የከብቶች መኖ በመታደል ላይ መሆኑን፣ የውኃ ጉድጓዶች ጥገና ሥራ እየተከናወነ እንደሆነና የውኃ ማጣሪያ ኬሚካሎች በመሠራጨት ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት በተፈጠረው ድርቅ ምክንያት 8.2 ሚሊዮን ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፣ የዕርዳታ አቅርቦቱ ካልተፋጠነና የአየር ፀባዩ ካልተለወጠ የተረጂዎች ቁጥር በሁለት ወራት ውስጥ 15 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ 

 

በሽብር ድርጊት ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው ዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ካቀረበባቸው በኋላ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ የተሰናበቱት የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣

ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸው ይግባኝ ተመርምሮ እንደሚያስቀርብና እንደማያስቀርብ ለመንገር በድጋሚ ተቀጠሩ

የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን በመቃወም የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝ ተከትሎ ውሳኔው እንዳይፈጸም ዕግድ የሰጠው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ጥቅምት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. የውሳኔ መዝገቡን መርምሮ ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ‹‹ያስቀርባል ወይም አያስቀርብም›› ብሎ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፣ ዓቃቤ ሕግ የተቃወመው የሥር ፍርድ ቤት የውሳኔ መዝገብ እንዳልቀረበለት ገልጿል፡፡ በመሆኑም ውሳኔውና ዝርዝር ማስረጃዎቹ ተያይዘው እንዲቀርቡለት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ 

በዕለቱ ይግባኝ የተጠየቀባቸው የአንድነት አመራር የነበሩት አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር የነበሩት አቶ አብረሃ ደስታና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበሩት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ እንዲሁም አብረዋቸው ይግባኝ የተባለባቸው አቶ አብረሃም ሰለሞን በችሎት አልተገኙም፡፡ ፍርድ ቤቱ በችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

 

አፌን መረረኝ፤ ጠረን አመጣብኝ፤ የተለያዩ ሰዎች ሲናገሩት የሚደመጥ ችግር ነዉ። የአፍ ምሬት ከምን ይመጣል? ዉስጥ ደዌ ከፍተኛ ሃኪም ዶክተር ቶሌራ ወልደየስ፤ አፍን ሊያመርሩ የሚችሉ የተለያዩ ምክንያቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ነዉ በዝርዝር ያብራሩት። ዶክተር ቶሌራ የተለያዩ በሽታዎችም አፍ ላይ ምሬት እንዲሰማን ሊያደርጉ …

የአፍ ምሬትና ጠረን መንስኤዎቹ Read more »

ጥቅምት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋቢያችን ነዋሪዎችን በማነጋገር እንደገለጸው፣ በአድማው የተሳተፉትን ሹፌሮችን ወደ እስር ቤት የወሰዱ ሲሆን፣ ከፖሊስ የሚደርስባቸውን ጫና በመፍራት ስራ እንጀምራለን ያሉት ደግሞ 500 ብር ቅጣት ካልከፈሉ እንደማይጀምሩ ተነግሯቸዋል። ከፖሊስ የሚደርሰውን ወከባ በመፍራት ብዙ ሹፈሮች አሁንም ራሳቸውን ደብቀዋል። አንድ የባጃጅ ባለሃብት መንግስት ለምን አድማ አደረጋችሁ በሚል እየተበቀለ ነው ብለዋል።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

መንግሥት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ከሚያወጣው ወጪ ባነሰ ታሪፍ አገልግሎት እንደሚሰጥ በመግለጽ፣ ወጪውን ለማካካስ 50 በመቶና ከዚያም በላይ ሊደርስ የሚችል ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል መባሉን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል አስተባበለ።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሃይለማርያም ደሳለኝ “በብሔር በአብሮ አደግነትና በተለያየ ጥቅም ተሳስረን፣ የምንከላከል ከሆነ ይሄ አይሰራም;እንደዚህ ዓይነት ነገሮች መቆራረጥ ኣለባቸው።” አለ እየተባለ ሃይለኛ ልማታዊ ወቀጣ እየተደረገ ነው::ወያኔን ለማያውቅሽ ታጠኙ በሏት;;በኢኮኖሚ በድርቅ እና በተለያዩ ጫናዎች አጣብቂኝ ውስጥ ከውስጥ እና ከውጪ …

ከጅምሩ ኋላፊነት የጎደለው አገዛዝ ስለተጠያቂነት ሞራሉ የለውም::ከአጣብቂኝ ለመውጣት የሚደረግ ልማታዊ ሽወዳ ይቁም::‪(ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

አልጀዚራ በታሊባን የግዛት አከባቢዎች ባሉ ካምፖች ውስጥ አሸባሪው አይሲል/አይሲስ ሕጻናት አጥፍቶ ጠፊዎችን እያሰለጠነ መሆኑ ቦታው ድረስ በመሄድ በቭድዮ እና በፎቶ የተደገፈ ፕሮግራም አቅርቧል::አልጀዚራ ቦታው ድረስ በመሄድ ያቀረበው ዘገባ እንደሚያመለክተው ራሱን አይሲል ብሎ የሚጠራው ድርጅት በአፍጋኒስታን ፓኪስታን እና ጎረቤት አገሮች ውስጥ …

አፍጋኒስታን ውስጥ በሚገኙ የታሊባን ካምፖች አሸባሪው አይሲል ሕጻናት አጥፍቶ ጠፊዎችን እያሰለጠነ ነው:: Read more »

የኑሮ ውድነት ግሽበቱ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው፡፡ ጂሀዳውያን ናችሁ የተባሉ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ከምዕተ ዓመቱ ግቦች ብዙዎቹ በስራ ላይ አልዋሉም ተባለ [youtube http://www.youtube.com/watch?v=XDeNxYzJYpw]

ምርጫ 1997 ዓ.ምን ተከትሎ ጥቅምት 22/1998 ዓ.ም በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቀጥታ ትዕዛዝ በ‹‹ፀጥታ ሀይሎች›› በጭቃኔ ለተገደሉት ሰማዕታት እና ለቆሰሉት ኢትዮጵያውያን በሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት መታሰቢያ ተደረገ፡፡ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ጥቅምት 22/1998 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የገጠማቸውን በተለይም ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ ያዩትንና …

ምርጫ 1997 ዓ.ምን ተከትሎ ጥቅምት 22/1998 በጭቃኔ ለተገደሉት ሰማዕታት የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሄደ Read more »

ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያዋ የድንበር ከተማ ሜሩ ኢዞሎ አቅራቢያ በቦረና እና ሜሩ ጎሳዎች መሃከል በተቀሰቀሰ ግጭት አስር የአካባቢው ነዋሪዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ከ2 ሺ በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። የከተማው አሽከርካሪዎች ግጭቱ እጅግ አስፈሪ እንደነበርና ሁኔታዎቹ አሳሳቢ መሆናቸውን ገልጸው የሜሩ ብሔር አባላት ወደ ከተማቸው የሸሹ ሲሆን የቦረና ጎሳ አባላትም …

ፍሪደም ሃውስ የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት በዓለማችን ላይ የኢንተርኔት አፈና እየጨመረ መሄዱን በ2015ቱ የኢንተርኔት ነጻነት ሪፖርቱ ላይ ገለጸ። ድርጅቱ በጥናቱ ካካተታቸው 65 ሃገራት መካከል 32ቱ የኢንተርኔት ሳንሱርና አፈናን አጠናክረዋል ብሏል።

Minilik Salsawi – በኢትዮጵያ በሃይማኖታዊ የመንፈስ ጥኡም ሰበካና ዜማ ጋር በማጣፈጥ የጨቋኞችን የበላይነት በመስበክ ሕዝብን ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ የጳጳሳት እና የሼህዎች አብይ ተግባር ነው።ዜጎችን መታደግ የማይችሉ በአስቸኳይ ቆባቸውን አውልቀው ከተራው ሕዝብ የመቀላቀል ግዴታ አለባቸው።ቤተክርስቲያን እና መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅና ጓንት …

አሁንም እደግመዋለሁ :- ዜጎችን መታደግ የማይችሉ የሃይማኖት መሪዎች ቆባቸውን ያውልቁ:: (ምንሊክ ሳልሳዊ‬) Read more »

ደቡብ ሱዳን ራሷን የቻለች ሉዓላዊ አገር ሆና ብቅ ያለችው እ.ኤ.አ. በሐምሌ 2011 ነበር፡፡ ደቡብ ሱዳናውያን ይህን ነፃነት ለመቀዳጀት እ.ኤ.አ. ከ1956 ጀምሮ ከሰሜን ሱዳናውያን ጋር ጦርነት ውስጥ ቆይተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1977 በደቡብ ምዕራብ ሱዳን ነዳጅ መገኘቱ ከተረጋገጠ በኋላ፣የእርስ በርስ ጦርነቱ ይበልጥ ተጧጡፎ …

አስደንጋጩ የአፍሪካ ኅብረት የደቡብ ሱዳን ግምገማ Read more »

ለመሪ ዕቅድ ዝግጅትና ትግበራ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቧል የቤተ ክርስቲያንን ኹለንተናዊ ችግር የሚያጠና ዐቢይ ኮሚቴ አቋቁሟል የሙስና እና የመልካም አስተዳደር ዕጦት በኮሚቴው ጥናት ተካተዋል የጥናቱ ግኝትና መፍትሔ ተቋማዊ ህልውናዋንና አቅጣጫዋን ይወስናል

«ወቅቱ ክረምት ነዉ ካፊያ የሚጥልበት፤
መንገዱ ጠባብ ነዉ፤ ኮሮኮንች የበዛዉ ሰዉ የማይሄድበት፤
ላይጨልም ጨልሞ አይን ያጭበረብራል፤
ይህ የሕይወት አረም ወቅትን ተገን አድርጎ፤
ዓይንን ከጋረደ ማ ማንን ይለያ።»

News Ethiopia Wetatoch Dimts 96 02.11.2015 መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ ። [youtube http://www.youtube.com/watch?v=nDI0Kte6iYs]

ወያኔ ዘር ላይ የተመሰረተ የግዳጅ መዋጮ ሊጀምር ነው :: ስልጤ ውስጥ ፖሊስና ተማሪዎች ተጋጩ ተማሪዎች ተጎዱ በታንዛኒያ የገዥው ፓርቲ ተወካይ ምርጫውን አሸነፉ የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም የሚፈለጉ የቦኮ ሃራም አባላትን ፎቶግራፎች አሰራጨ የደቡብ ሱዳን አማጽያን የያዟቸውን የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት …

ወያኔ ዘር ላይ የተመሰረተ የግዳጅ መዋጮ ሊጀምር ነው Read more »

ቢቢኤን የማፍያው ህገ-ወጡ አህባሽ መጅሊስ የሃጅ ዝርፊያ መረጃ ቁጥር 2 በሙስሊም ኮፍያ የተደበቀው የነበረው መንግስት ያስቀመጠው ወንጀለኛው የህገ-ወጡ መጅሊስ ጸሃፊ አራጋው አሊ ሲጋለጥ ለሁለት አመታት ከሀጅ ጉዞ ታግዶ የቆየው በሌብነት የተሰማራ ሙስሊም ያልሆነ ሲሳይ ተስፉ ወልደ ጊዎርጊስ የተባለ ሀጅ እንዲሄድ …

በሙስሊም ኮፍያ የተደበቀው የነበረው መንግስት ያስቀመጠው ወንጀለኛው የህገ-ወጡ መጅሊስ ጸሃፊ አራጋው አሊ ሲጋለጥ Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት «ድሕነትን ታሪክ እናደርጋለን» ባለበት፤ የሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት በድርብ አሐዝ ማደጉ በሚነገርበት ባሁኑ ወቅት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዉያን ዳግም ምፅዋት መማፀናቸዉ በርግጥ ግራ-አጋቢ አነጋጋሪም ሆኗል

 በበፍቃዱ ዘ ኃይሉ
የሰለሞን ስዩምን ‹‹የኦሮሞ ጉዳይ እና የኢትዮጵያ ብያኔ›› የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ (ሁለተኛ እትም) አነበብኩት፡፡ በጥቅሉ ወድጄዋለሁ፡፡ ጥቂት ቅሬታዎች ግን አሉኝ፡፡ ሰለሞን በአማርኛ የኦሮሞ ጉዳይን ከጻፉ (እና እኔ ካነበብኩላቸው) ጸሐፍት ሁሉ በተሻለ ልለው በምደፍረው ደረጃ ምሁራዊ ታማኝነት (intellectual honesty) ተስተውሎበታል፡፡ አልፎ፣ አልፎ ግን ምሁራዊ ታማኝነቱ ከሚጎድላቸው ምሁራን ማጣቀሱ ሚዛን አስቶ ያንገዳገደው ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ የታቦር ዋሚ ‹‹የውገና ድርሰቶችና የታሪክ እውነቶች››ን ማንሳት ይቻላል፡፡ ታቦር ትልቅ ርዕስ ይዞ ትንንሽ ክርክር የተከራከረባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ አንዱ የቋንቋ ተናጋሪዎች ብዛትን በተመለከተ የሚሰጠው ምንጭ አልባ ድምዳሜ ነው፡፡ ሰለሞን ያንን በኦሮሞ ጉዳይ ላይ ያንፀባርቀዋል፡፡ ‹‹. . . መረጃዎች አሉ›› በሚል ብቻ፡፡ በተጨማሪም አጠራጣሪ (አከራካሪ) ሁኔታዎች ላይ እምነቱን ለዘውግ ብሄርተኞቹ ትርክት ወደመስጠቱ አዘንብሎብኛል፡፡

ይህ በእንዲህ አያለ፣ መጽሐፉን አንብቤ ስጨርስ የጎደለ ነገር ያለ-ያለ ተሰማኝ፡፡ ታዲያ የጎደለ የመሰለኝን ምዕራፍ ለምን አልጽፈውም አልኩና ተነሳሁ፡፡ ጽሑፉን የምጽፈው የሰለሞንን ሐሳብ እየተዋስኩ፣ የኔን እየጨመርኩበት ነው፡፡ እሱም ይጭንብኛል፤ እኔም እጭንበታለሁ፡፡ ስለዚህ ከታች የማሰፍረው ጽሑፍ ላይ ‹እኔ›› እኔ አይደለሁም፡፡ ሰለሞን ስዩም ነው፡፡ እኔ ሁን እንዳልኩት፡፡

የተጣመመው የብሔርተኝነት ቅርንጫፍ
በኢትዮጵያ ቀኝ ዘመሞች አና ግራ ዘመሞች ሁሌም እርስ በርስ እንደተዋቀሱ ነው፡፡ እነዚህ ‹‹ትምክህተኛ ብሔርተኞች ፍፁም አሀዳዊ አገር ለመፍጠር ሊፍጨረጨሩ አገሪቱን ይበታትኗታል፡፡ ሲሉ፣ እነዚያ ‹‹ጠባብ ብሔርተኞች ሁሉንም ነገር በዘውግ ዓይን እያዩ አገሪቱን ሊበጣጥሷት ነው›› ይላሉ፡፡ መጽሐፉ በኦሮሞ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡ ስለሆነም አሁን ማተኮር የምፈልገው የዘውግ ብሔርተኞች የሚከሰሱባቸው ችግሮች እና መፍትሔዎች ላይ ነው፡፡

አማራ-ሰግነት (Amhara Phobia)
ኦሮሞ ብሔርተኝነት ከገጠሙት ፈተናዎች መካከል አንዱ የኦ&#4654

መንግሥት የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ 50 በመቶ እንደሚጨምር ይፋ አደረገ

ፋብሪካዎች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል

መንግሥት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ከሚያወጣው ወጪ ባነሰ ታሪፍ እየደጎመ ሲያቀርብ መቆየቱን በመግለጽ፣ በአሁኑ ወቅት ቢያንስ ወጪውን የሚሸፍን ታሪፍ ማስከፈል በማስፈለጉ 50 በመቶና ከዚያም በላይ ሊደርስ የሚችል ጭማሪ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ እንዳስታወቁት፣ መንግሥት ለበርካታ ዓመታት በድጎማ ሲያቀርበው የቆየው የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ በጣም ዝቅተኛ ነበር፡፡ ዝቅተኛ ብቻም ሳይሆን በአሁኑ ወቅት ኃይል አምርተው ለመንግሥት ለመሸጥ ፍላጎት ካላቸው ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ፣ የታሪፉ ዝቅተኛነት የድርድር አቅሙን እንዳዳከመበት አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም መንግሥት የታሪፍ ለውጥ የማድረግ አቋም እንዳለው፣ ዘ ኢኮኖሚስት ሰሞኑን በአዲስ አበባ ባካሄደው የኢትዮጵያ ጉባዔ ላይ ለታደሙ ኢንቨስትሮች ገልጸዋል፡፡ 

ኢንጂነር አዜብ እንዳብራሩት፣ መንግሥት በአሁኑ ወቅት አንድ ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ዘጠኝ የአሜሪካ ሳንቲም እያወጣ ይገኛል፡፡ በአንፃሩ አንድ ኪሎ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ለመሸጥ ስድስት የአሜሪካ ሳንቲም እያስከፈለ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የ50 በመቶና ከዚያም በላይ ለውጥ ሊሆን እንደሚችል ይፋ አድርገዋል፡፡ 

ኢንጂነሯ ለሪፖርተር እንዳብራሩት፣ ዝቅተኛ ነው ያሉት ታሪፍ በኃይል ማመንጨት ዘርፍ የሚፈለገውን ያህል የውጭ ኢንቨስትመንት እንዳይመጣ በማድረግ ሲጎዳው ቆይቷል፡፡ በመሆኑም የታሪፍ ለውጥ እንደሚደረግ በመገለጹ 14 ያህል የውጭ ኩባንያዎች ኃይል አመንጭተው ለመንግሥት ለማቅረብ ድርድር ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ ኩባንያዎች መካከል የአራት ቢሊዮን ዶላር የጂኦተርማል ኃይል ፕሮጀክት ይዞ የመጣው ሬይክቪክ ጂኦተርማል፣ ጄነራል ሞተርስና ብላክ ራይኖ የተሰኙት ይጠቀሳሉ፡፡ 

ብላክ ስቶን ለተባለው የአሜሪካ ኩባንያ እህት የሆነው ብላክ ራይኖ፣ በአሁኑ ወቅት ከጂቡቲ እስከ አዋሽ 550 ኪሎ ሜትር የሚዘረጋውን የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ይህ ኩባንያ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት ከኤሌክትሪክ ኃይል ጋር ስምምነት ከመድረሱም በተጨማሪ፣ በመጪዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ወሳኝ ወደሆነው ምዕራፍ እንደሚሸጋገር ኩባንያውን በመወከል የተገኙት ሺሌሽ ሙራሊዳሃ አስታውቀዋል፡፡ እንዲሁም በኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ሥራ ላይ ለመግባት ፍላጎት እንዳለውም ለመንግሥት ማስታወቁን ኢንጂነር አዜብ ጠቁመዋል፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል የታሪፍ ማሻሻያ እንደሚደረግ ይፋ መደረጉ ካስደነገጣቸው መካከል የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ማኅበር ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ጨርቃ ጨርቅና ጥጥ ኢንዱስትሪዎች ፌደሬሽን የቦርድ አባል አቶ ፋሲል ታደሰ አንዱ ናቸው፡፡ ኢንጂነር አዜብ የጠቀሱት የታሪፍ ጭማሪ ኢንዱስትሪዎችን ሳይሆን ኃይል ወደ ውጭ የሚልኩትን ኩባንያዎች የሚመለከት ነው በማለት ለመከራከር ቢሞክሩም፣ ጭማሪው ሁሉንም እንደሚመለከት ኢንጂነር አዜብ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ ‹‹ይኼማ ሙቱ ማለት ነው፤›› ያሉት አቶ ፋሲል፣ የታሪፍ ጭማሪ ከዚህ ቀደም ተነስቶ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እንደማይመለከት ከመንግሥት ጋር ስምምነት ተደርጎ እንደነበር በመግለጽ፣ የመረጃ ችግር እንዳይሆን በማለት ሥጋታቸውን ሲገልጹ ቢደመጡም፣ ኢንጂነሯ በድጋሚ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ ሆኖም የታሪፉ ጭማሪ ሚዛናዊ እንዲሆን መደረጉን ኢንጂነር አዜብ ለማስረዳት ሞክረዋል፡፡

ይሁንና ይጨመራል የተባለው ታሪፍ ከመቼ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ኢንጂነሯ ባይገልጹም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንደሚሆን ግን ተናግረዋል፡፡ 

ከሁለት ዓመት በፊት የአፍሪካ ልማት ባንክ በአፍሪካ በከፍተኛ ወጪ ኃይል የማመንጨት አዝማሚያዎችን የሚያስቃኘው ጽሑፍ ላይ እንዳሰፈረው፣ መንግሥታት ኃይል የማመንጨት አቅማቸው ደካማ እንዲሆን ከሚያደርጉ ፈተናዎች መካከል ከፍተኛ ወጪ አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም መንግሥታት የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎትን ለማሟላት በድጎማ ለማቅረብ መገደዳቸውን ባንኩ አስፍሯል፡፡ 

በሌላ በኩል መንግሥት በኢነርጂው መስክ ማስተካከል ይገባዋል ከተባሉት ችግሮች መካከል የውጭ ምንዛሪ ለውጥና ሊያስከትል የሚችለውን የኪሳራ ሥጋት እንዴት እንደሚመለከተው ተጠይቋል፡፡ የቢሮክራሲ ጣጣዎች፣ በጂኦተርማል መስክ የፋይናንስና የማበረታቻ ፓኬጆችን ማሻሻል እንዳለበት የሬይክቪክ ጂኦተርማልና የብላክ ራይኖ ኃላፊዎች መንግሥትን አሳስበዋል፡፡ 

 

የመግለጫው የፒዲኤፍ ቅጂ ሊንክ፡- http://goo.gl/siwmU6 መግለጫው በድምጽ ቅጂ ቆይቶ የሚለጠፍ ሲሆን ሙሉ ቃሉ በጽሁፍ ደግሞ እንደሚከተለው ይነበባል፡- በስልጤ ዞን ኒቃብ እና ሂጃብ ላይ የታወጀው ዘመቻ የብሔራዊው ጭቆና አካል ነው! ሙስሊሙ መብቱ እስኪከበርለት ድረስ ስልቱን እየቀያየረ ከመታገል ወደኋላ አይልም! እሁድ ጥቅምት …

ሙስሊሙ መብቱ እስኪከበርለት ድረስ ስልቱን እየቀያየረ ከመታገል ወደኋላ አይልም ! ወቅታዊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ Read more »

እሁድ 21 / 02 / 2008 ዓ/ም በመቐለ ከተማ ማይክሮፎን በመያዝ ከ1 ዓመት እስከ 29 ዓመት ዕድሜ ክልል የሚገኝ ማንኛውም ሰው የማጅራት ገትር( ኣንቅፂ) ክትባት መውሰድ እንዳለባቸው በጥብቅ እየታዘዘ ነው። Amdom Gebreslasie በኣሁኑ ሰዓት የትግራይ ክልል ጨምሮ በድርቅ የተጠቁ ኣከባቢዎች …

የማጅራት ገትር ወረርሺኝ( ኣንቅፂ) ድርቅ በመታቸው ኣከባቢዎች ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል። Read more »

የነጭ ሽንኩርት አስሩ ለጤንነት ያለው ጠቀሜታ ነጭ ሽንኩርት ከተለያዩ ምግቦች ውስጥ በመጨመር መመገብ ለጤንነት እጅግ ጠቀሜታ ይሰጣል::በነጭ ሽንኩርት ውስጥ አሊሲን ማለት አንቲባዮቲክ አንቲቭራል አንቲፈንገስ እንዲሁም አንቲኦክሲዳንት የተባሉት ንጥረ ነገሮች የሚገኙ ሲሆን በቫይታሚን እና በተፈጥሮ ማእድናት የበለጸገ ነው ነጭ ሽንኩርት:: በውስጡ …

የነጭ ሽንኩርት አስሩ ለጤንነት ያለው ጠቀሜታ Read more »

  Minilik Salsawi – በሰራዊት ውስጥ ያለውን የአንድ ዘር የበላይነት የፖለቲካ ነጻነት አለመኖር የጥቅማጥቅም ጉዳዮች የደረጃ እና የማእረግ እድገት ማጣት በሶማሊያ ስለዘመቱት ወታደሮች ጉዳይ ከየክፍላቸው እየታፈኑ ስለሚታሰሩ እና ስለሚሰወሩ የሰራዊት አባላት ጉዳይ ከፍተኛ ተቃውሞ ከሚያሰሙት ከመከላከያ እዞች አንዱ የሆነው በጄኔራል …

በደቡብ ምስራቅ እዝ ያለው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጥለው መኮብለላቸውን ቀጥለዋል:: Read more »