የደህንነት አባላቶች ስልኮቻቸውን የሚጠቀሙት የተቃዋሚዎችን ዘገባ በማየት እና በማሰራጨት ነው በሚል ተገመገሙ::

Minilik Salsawi – የደህንነት አባላት ግምገማ በጌታቸው አሰፋ ሰብሳቢነት ቀጥሏል::ትላንትና ቀዝቀዝ ብሎ የተጀመረው ግምገማ ዛሬ ላይ ተሟሙቆ የዋለ ሲሆን የደህንነት አባላቱን ከስራ የማፈናቀል ለእስር የመዳረግ እና ከደረጃ ዝቅ የማድረግ ውጤቶችን ግምገማው እንደሚወልድ ይጠበቃል::ትላንትና በሁለት የደህንነት አባላት ሞባይል ላይ የተጀመረው ግምገማ ዛሬ እስከ ምሽት ድረስ ሰፋ ብሎ በስምንት አባላት ላይ ግምገማው ሰፍቶ ታይቷል::ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ እንደገለጹት አራት ሲም ካርድ የሚጎርሰው የወያኔ የደህንነት ሞባይል ቀፎዎች በተቃዋሚዎች ጉዳይ የተጨናነቀ መሆኑ ሲደረስበት የተቃዋሚዎች ዘገባ ምስሎች ጹሁፎች እና ተመሳሳይ ጉዳዮች ሲገኙበት የተጠቀሙት የኢንተርኔት ታሪክ ሲፈተሽ አብዛኛው የሚያሳየው የተቃዋሚዎችን እና የአክቲቭስቶችን ድህረ ገጽ መሆኑ ታውቋል::

ለአንድ ሳምንት ይቆያል የተባለው ይህ ግምገማ ሰራተኞችን በማሳደም የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ በማብዛት ባለስልጣናትን በማማት አለቆቻቸውን በማጓጠጥ በሚል የተገመገሙ ሲሆን ታዳዲስ አባላትን እና የደህንነት ቢሮ ሃላፊዎችን በማጋጨት የተገመገሙ ሲሆኑ አዳዲስ አባላቱ በከፍተኛ የደህንነት አካላት በማስጠንቀቂያ እና በማስፈራሪያ መታለፋቸው ታውቋል::በደህናነት ቢሮ እስጥ የተደራጀ አፍራሽ ሃይል አለ የሚሉት የደህንነቱ ሹም አቶ ጌታቸው ይህን ቡድን ለማፍረስ አልተቻለም ኔትወርኩ አወሳስበስ የዘረጉትን ቀድሞ ማፍረስ ያስፈልጋል ሲሉ በተጠርጣሪ አባሎቻቸው ላይ ዝተዋል::የደህንነት ቢሮው እየታመሰ ሲሆን የሚገመገሙ አባላት ሁሉ ከስራ የሚሰናበቱ ሲሆን በተለያየ የፈጠራ ክስ እስር ቤት እንደሚወረወሩ ታውቋል::
‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬