ሌ/ኮ መንግስቱ ኃይለማሪያም በ‹‹ኑዛዜያቸው›› በርካቶችን ለኢትዮጵያ ውድቀት ተጠያቂ አደረጉ::
ጌታቸው ሽፈራው
• ‹‹ስለ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ መናገር ቀርቶ ስሙንም ማንሳት በጣም ያሳፍረኛል››

• ‹‹ጀኔራል መርዕድ ንጉሴ የውጊያ መሰናዶዎቼን ለጠላት አሳልገው ሰጥተዋል
• የሀገር ደህንነት መስሪያ ቤት ፈላሻዎችን በህገ ወጥ መንገድ ሲያስተላልፍ ነበር
• ፕሮፌሰር መስፍንና ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ ተጠያቂ ከተደረጉት ታላላቅ ሰዎች መካከል ናቸው
• እነ ፍስሃ ደስታ፣ እነ ኮሎኔል ተስፋዬ፣ እነ ጀኔራል ስዩም ሊያስገድሏቸው እንደነበር አውስተዋል
ኢትዮ-ምህዳር ጥቅምት 20/2008 (አ.አ)፡- የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም ‹‹ኑዛዜ›› ብለው ለህዝብ እንዲደርስላቸው በካሴት ካሰራጩት ድምፅ ተዘጋጅቶ ለንባብ በበቃ ‹‹ከኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም አንደበት›› የተሰኘ መፅሃፍ በርካታ ምሁራንንና የቀድሞ ባልደረቦቻውን በኢትዮጵያ ላይ በማሴርና ለውድቀቱም ተጠያቂ ናቸው ማለታቸውን አስነብቧል፡፡ ኮ/ል መንግስቱ አብዛኛውን ይሸረብባቸው የነበረውን ሴራ የተረዱት ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ እንደሆነ በቁጭት ተናግረዋል፡፡ በተለይ በመፈንቅለ መንግስቱ ወቅት የተገደሉት ጀኔራሎች ለውድቀቱ ዋነኛዎቹ ተጠያቂ ተደርገዋል፡፡ ከጀኔራሎቹ መካከል እነ መርዕድ ንጉሴ፣ ፋንታ በላይ በስፋት የተጠቀሱ ሲሆን የጀኔራል መርዕድ ንጉሴ ሁለተኛዋ ሚስት ለሻዕቢያ ትሰራ እንደነበር ተግልፆአል፡፡ በተጨማሪም ጀነራል መርዕድ ንጉሴ የውጊያ ስትራቴጅ መሰናዶዎችን ለጠላት አሰልፎ ሰጥቷል ሲሉ ተጠያቂ አድርገዋቸዋል፡፡
በመፅሃፉ እነ ፍስሃ ደስታ፣ እነ ኮሎኔል ተስፋዬ፣ እነ ጁኔራል ስዩም ኮ/ል መንግስቱን ጦርነት ውስጥ በማጋፈጥ በህይወታቸው ላይ አደጋ እንዲደርስባቸው ለማድረግ ሙከራ ማድረጋቸው ገልፀው በጓዶቻቸው ሴራ ይሸረብባቸው እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ በተቋም ደረጃም የኢትዮጵያ ሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ፈላሻዎችን ወደ እስራኤል በመላክ ሴራ ውስጥ መሳተፉን፣ በዚህ ንግድም በርካታ ግለሰቦች ትርፋማ መሆናቸውን በቁጭት ገልፀዋል፡፡ ኮሎኔሉ በስፋት ከተቿቸው ግለሰቦች መካከል ዳዊት ወልደጊወርጊስ ግንባር ቀደሙ ሲሆኑ ‹‹ስለ ዳዊት ገ/ጊዮርጊስ መናገር ቀርቶ ስሙንም ማንሳት በጣም ያሳፍረኛል፡፡›› ብለዋል፡፡
ኮ/ል መንግስቱ በተለያዩ የጦር አውድማዎች የተደረጉት ፍልሚያዎችና የ17 አመቱ ጉዞ ለምን እንደተሰናከለ፣ መንግስታቸው ለምን ችግር ውስጥ እንደገባ፣ የውጭና የሀገር ውስጥ ሴራዎችን፣ ኢትዮጵያውያን ሰሩት ያሉትን ስህተት በስፋት ዘርዝረዋል፡፡ በተጨማሪም ለምን እንደወጡና እንዳይመለሱ የተሸረበባቻን ሴራ፣ ቤተሰባቸው የገጠመውን ችግርና ለወደፊት መፍትሄ ያሉትንም በመጽሃፉ ሰፍሯል፡፡ ኮ/ል መንግስቱ ከሀገር ከወጡ በኋላ በኑዛዜ መልክ ለህዝብ እንዲደርስ በሲዲ ከቀረፁፁትን ድምፅ በሶስት ግለሰቦች የተዘጋጀው ‹‹ከኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም አንደበት›› የተሰኘው መፅሃፍ ለንባብ የበቃው ከሳምንት በፊት ነው፡፡
ጉጅሌዎች እሥኪ ተጠየቁ
መንግስቱ ኃይለማሪያም ደሣለኝ
Vs
ኃይለማሪያም ደሣለኝ
ሌላውን ትተን የሀገር ፍቅሩና እንድነታችን በማናችሁ ላይ ይበረታል?
ትውልዱ ከቀደምት መሪዎቹ ጠንካራ ተመኩሮዎችን ይፈትሻል ለግሉ ግብአት ያውላል ወያኔን ይዋጋል።
**********************************************
I can not white to read it, all what he did was good so fare but being merciless from the starting point made his journey so difficult, It wasn’t difficult for his power only, but also difficult for the country leaded by him. Off course he loved his country Ethiopia on other hand he missed a lot of apportunity and strategies to put the country at least on the right truck resources and materials wested wrong way and wrong direction. Yes! it is not only one single preson to be blamed for all mistakes have don douring his time. All of them responsible for wrong leadership performance, We must not pointing out finger only with him offcourse his the part of the problem but all the problems are not created by himself only. Over all it is a historic phenomena past is already passed.
ኮ/ል መንግስቱ ሀ/ማርያም አገራችን የባህር በር እንዳታጣ ለአደረጉት ተጋድሎ እናመሰግናለ። መሀይምነትን ለማጥፋት የማያነብ አይኖች አይኖሩም የማይጽፉ እጆች አይኖሩም ብለው የኢትዮጵያን ህዝብ ስላስተማሩ እናመሰግናልን። የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ተከባብረው እንዲኖሩ አንዲት አገር አንድ ባንዴራ ብለው ሁሉንም ብሄረሰቦች እኩል ስለአስተዳደሩ እናመሰግናለን። ኢሰፓ ስልጣን እስከለቀቀበት ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት የተጠበቀ ነበር። አገራችንም የባህር ባለቤት ነበረች። ልጅዎትንም አንድነት ብለው ሲጠሩት የሚያሳየው አገር ወዳድነትዎን ነው። እናመሰግናለን መንጌ መልካም የእረፍት ጊዜ።
Tamrat molla, antem kemola asgedom atishalim.please dont talk about ports anymore, those r not yours. Use tana hayk.
kolonel mengestu gena ke 25 amet bohala ke enkelf mebanenu new ?, abyot lejuan tebelalech bemel felsefena sent mehuranen cherese? hageretuan le tigre wenbedewoch asrekebo be guaro ber sheshto weto ahun sekebater, mehayemenetun adebabay eyaweta new.
hulum eko yekedut tesfa qortew new .beyaut beyaut seltanun ye mutegn belo aleqem ale.negusun telo negus hone.menalbat mister adergot kalhone mistum telaw lethed aseba neber new yemibalew .17 amet mulu 1.7 melion hezb chereseyetemarewen hulu.
በሀቅ ለታገለዉ እና ለተላላዉ መሪ ጓድ መንግስቱ ሀ/ማሪያም ረጅም እድሜና ጤና
ለሀገራችን ውድቀት መሰረታዊ ምክንያቱ የሃይለ ስላሴ አገዛዝ ሲሆን መንጌ ደግሞ በዚያው ላይ ቤንዝን አርከፍክፊዋል። ህወሃት ደግሞ ክብረቱን ጭሮ በመለኮስ እሳቱ መጥፋት እንዳይችል አድርጎ አያይዞታል። የተቀሩ ፓርቲዎች እሳቱ እንዳይጠፋ የህወሀት የጎሳ ፖለቲካ አራጋቢ መሳሪያ በመሆን ያገለግላሉ። በዚህ መሀል ህዝቡ አበሳውን ይበላል። ጦርንቱ ሁሉ በፌስ ቡክ ብቻ በመሆኑ ህዝቡ መሪ አጥቶ ተስፋ ቆረጠ። መንግስቱ በስልጣን ዘመኑ ሞቴን እንደ ቴዱ ያርገው ብሎ ስንት እንዳልተናገረ ቁርጥ ሲሆን ህዝቡንና ሀገሩን ለቀን ጅብ ሰጥቶ መሄዱ አለም እያወቀው የከሌን ስም ማንሳት ያሳፍራል ይላል። ሰው መሳይ በሸንጎ አሉ። ማፈሪያስ እሱ።
ኮ/ል መንግስቱ አምባገነንነት ባህሪ ሊኖረው ይችላል። አገሩን መውደድንና ለአገሩ ለኢትዮጵያ ሌት ተቀን መስራቱን የሚጠራጠር አለ? መንጌ በአንድ ብሄረሰብ የበላይነት ያምናል? በመንጌ ጊዜ አንተ የዚህ ብሄር አባል ስለሆንክ ወደ ክልልህ ሂድ ተብሎ አማራ ተባሯል? ጀግኖች የኢሰፓ አባላት ለ 17 አመታት አገር እንዳትፈርስ ላደረጉት ተጋድሎ የኢትዮጵያ ባለውለታ ናቸው።
Re: wind of change
እርስዎ ግን ምን ኩኖ ነው፤ቀን ሌላ ማታ ሌላ የሚኮኑ፧
ኣያምርብዎትም ጓድ
ለእርስዎ ሁለት ኣካውንት እና ድብቅ ስም ምን ይሰራዎሎታል
Leken jib asbelun. Narrow minded people are killing our country. Bad ethnic plitics.
HLACHUM WET TETU
HULACHUM WET BETASA TETU WEYANE ABABA RABNE YBLACHU
መንጌ እኮ መቼም የማይረሳ የኢትዮጵያ ባለ ውለታ ነው በአገሩና በህዝቡ የተወደደ ያለብድርና አእርዳታ ኢትዮጵያን ያሳደገ በተግባር እንጅ በፕሮፓጋንዳ ህዝብን ያላታለለ ስራ አጥና ጎዳና ተዳዳሪ ያልነበረባት አገር የራስዋ የጦር መሳሪያ ማምረቻ የነበራት ከሩ ዜጋ ማንኛውም አገር የሚያከብረው ህዝብ ያገሪቱ ገቢ በፍትሐዊነት የሚከፋፈልባት አገር መርተዋል፡፡
መንግስቱ=ወያኔ። አገሩን ሳይሆን እራሱንና ስልጣኑን ብቻ ነበር የሚወድ።
Melkam asteyayet new.
Numersan, the audio was recorded and distributed 25 years ago, it’s the author who paste it t
Just now.:)
ኘሬዝዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ማለት ጀግና መሪ የነበሩና የሆኑ ታላቅ ሰው ናቸዉ ፡፡የኢትዮጵያ ህዘብ የእንቁላል አሰኳሉ ውሰጥ ጫጩቶችን ስለማያይ ነው የተበላው፡፡ እሳቸው እስካሁን ቢኖሩ ኖሮ ………….አንድነት ፡ ኢትዮጵያዊነት ፡ ባልጠፋ ነበር፡፡ እድሜ ከጤና ለኮሎኔል
ኘሬዝዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ማለት ጀግና መሪ የነበሩና የሆኑ ታላቅ ሰው ናቸዉ ፡፡የኢትዮጵያ ህዘብ የእንቁላል አሰኳሉ ውሰጥ ጫጩቶችን ስለማያይ ነው የተበላው፡፡ እሳቸው እስካሁን ቢኖሩ ኖሮ ………….አንድነት ፡ ኢትዮጵያዊነት ፡ ባልጠፋ ነበር፡፡ እድሜ ከጤና ለኮሎኔል
Kolenel Mengistu endenie kehone feri tetratari ena chekagn rihrahe yemibal neger yalfeterebet biltabilt durye mekonen neber.manegnachewum besu amerar gizie yeteseru metfo negerochina sihtoch bemulu beguadochachew yetefetsemu yesera wutietoch nachew. beka esu fitsum yehonena sihtet serto yemayawuk “yezinb hiwot enkua” yalatefa new. Ferina teteratari mehonu ke meles gar yamesaslutal. endih ayenet sewoch degmo tsetset yemibal ayawukum.sintochun aredachew! aye ethiopia! nuzazie ale Mengie. yewudketachin mejemeria man honena new?
How can I get the book anyone?