መንግሥትና ዳያስፖራው ከህንዶቹ የሚማሩት ካለ

በአገሪቱ የተካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነትን ሽሽት፣ ከደርግ ግድያና መቅሰፍት ለማምለጥ፣ ለትምህርት እንዲሁም የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ኑሮ ለመቀየር ወይም በሌላ አጋጣሚ፣ ወደ ውጭ ወጥተው እዚያው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሚሊዮኖች እንደሚቆጠሩ ግምታዊ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡