ምርት ገበያና ዳሸን ባንክ በመጋዘን ደረሰኝ ብድር ለመስጠት ተሰማሙ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከዳሸን ባንክ ጋር የመጋዘን ደረሰኝን በመያዝ በመጋዘኖች አካባቢ ለሚገኙ አምራቾች ብድር ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት አደረጉ፡፡ ዳሸን ባንክ ይህን መሰሉን የብድር ስምምነት ከምርት ገበያው ጋር ሲፈራረም፣ ከንብ ባንክና ከንግድ ባንክ በመቀጠል ሦስተኛው ነው፡፡