‹‹አዲስ አበባ ውስጥ ትልቅ ወንጀል ፈጽሞ ማምለጥ የማይቻል ነገር ነው›› ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሣ፣

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ሊባል በሚያስችል ደረጃ የቅሚያ፣ አንቆ (ሀንግ) ትንፋሽ በማሳጣትና በመደብደብ ዝርፊያ እየተፈጸመ ነው፡፡ የከተማው ነዋሪዎች ከጧቱ 12 ሰዓት ተነስተው ወደፈለጉበት ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይችሉም እየተናገሩ ነው፡፡