ለዓባይ ቃል ወይስ ተግባር?

ረቡዕ፣ ሚያዝያ አሥራ ዘጠኝ ቀን ሁለት ሺሕ ሦስት ዓመተ ምሕረት፣ ንጋት አስር ሰዓት ተኩል መስቀል አደባባይ ስንደርስ፣ ‹‹ማን ነው የቀረው?›› በሚያስብል ሁኔታ በርካታ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች በቦታው ላይ ተገኝተው ነበር፡፡ ብዙዎቹ ከተደረደሩት አውቶቡሶች ውስጥ ገብተው ቦታቸውን በመያዝ የጉዞውን መጀመር በጉጉት ይጠባበቃሉ፡፡