በሙስና ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በሌለበት በ20 ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ
በከባድ የእምነት ማጉደልና መንግሥታዊ ሰነዶችን አስመስሎ በማዘጋጀትና ወደ ሀሰት በመለወጥ የሙስና ወንጀል ክስ የተመሠረተበት ተከሳሽ በሌለበት 20 ዓመት ጽኑ እስራትና በሃምሳ ሺሕ ብር መቀጮ እንዲቀጣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ግንቦት 2 ቀን 2003 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ውሳኔ ማስተላለፉን የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡