ግልገል ጊቤ ሁለት ለሰዓታት በገጠመው ችግር ኃይል ማመንጨት አቋረጠ
‹‹ኮርፖሬሽኑ ስለታሪፍ ጭማሪ ያቀደውም፣ የሚያውቀውም ነገር የለም›› አቶ ምህረት ደበበ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ሚያዝያ 17 ቀን 2003 ዓ.ም. ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል በአብዛኛው የአገሪቱ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው፣ በግልገል ጊቤ ሁለት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ደርሶ በነበረው ድንገተኛ ችግር መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡