በሊቢያ የግብጽ ተወላጆች የሆኑ 21 ክርስቲያኖች በአሠቃቂ ሁኔታ ከተገደሉና የግብፅ ፕሬዚዳንትም ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ርምጃ እንዲወስድ ካሳሰቡ ወዲህ ፣ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤት ጉዳዩ ን አንስቶ መወያያቱ ተገለጠ። ግብፅ በሀገር

በምሥራቅ ዩክሬይን የአውራ ጎዳናና ባቡር ሐዲድ መገናኛ መሥመር ላይ በምትገኘው ዴባልትሴቭ በተሰኘችው ከተማ ፤ የተከበበው የኪቭ መንግሥት ጦር ሠራዊትና የምሥራቅ ዩክሬይን አማጽያን ለሳምንታት ብርቱ ውጊያ ሲያካሄዱ ከቆዩ በኋላ ከተማይቱ በአማጽያኑ ቁጥጥር ሥር መዋሏ ተረጋገጠ።

ባለፈው ሳምንት ማለቂያ ላይ ፤ የኬንያ መንግሥት የመገናኛ ብዙኀን የሥርጭት አገልግሎትን፣ ከቆየው «አናሎግ» ወደ ዘመናዊው ሥነ ቴክኒክ አያያዝ «ዲጂታል »ማሸጋገሩ ፤ NTV KTN «ሲቲዘን TV» እና QTV በሚሉ ምሕጻረ ቃላት የታወቁትን ዐራት

የካቲት 11፣ 1967 ዓም የተመሠረተው የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ 40ኛ የምሥረታ ዓውዳመት በመቀሌ ከተማ ተከበረ። የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ 40ኛ የምሥረታ ዓመት በተለያዩ ቦታዎች እና ዝግጅቶች ሲከበር ነው የሰነበተው።

በሜዴትራንያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት ሲሞክሩ በጉዞ ላይ ህይወታቸው የሚያልፍ ስደተኞች ቁጥር ባለፈው ዓመት በመጠኑ ቀንሶ ነበር ። ሆኖም ባለፈው ሳምንት ቁጥራቸው ከ300 በላይ የተገመተ ስደተኞች የሜዲቴራንያን ባህር ሲሳይ ሆነዋል ። የቀጠለው የባህር ስደተኞች እልቂትና መላው የዛሬው ትኩረት ነው ።

አፍሪቃ ዉስጥ በየዓመቱ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ልጃገረዶች በዘልማዳዊዉ የአኗኗር ይትበሃል መሠረት የመዋለጃ አካላቸዉ ይተለተላል ወይም ለዚህ ችግር የተጋለጡ መሆናቸዉን የዓለም የጤና ድርጅት ይገልፃል።

የዩሮ ቀውስን ተከትሎ ባለፉት ዓመታት በግሪክ ላይ የተጣለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም እና የቁጠባ ርምጃ በቅርቡ ወደ ስልጣን የመጣው አዲሱ የግሪክ መንግሥት እንደማይቀበል አስታዉቋል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የጀርመን ትምህርት ቤት ትናንት የተመሰረተበትን 60 ዓመት አከበረ። በነዚህ ዓመታት ውስጥ በርካታ ኢትዮጵያውያንን እና ጀርመናውያንን አስተምሮ ለከፍተኛ የሥራ ደረጃ እንዳበቃ ተነግሮለታል።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ሃዲድ በተሽከርካሪዎች ጉዳት እየደረሰበት ነው። መንገደኞችም የባቡር መከለያ አጥሮችን በመዝለል መሻገር መጀመራቸው ለተሽከርካሪ እና ባቡር ትራንስፖርቱ ስጋት ሆኗል። በአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የመንገድ ደህንነት ባለሙያ ሁኔታው ትኩረት እንደሚያሻው ተናግረዋል።

ሊዮኔል ሜሲ ዳግም ሐትሪክ ሠርቷል፤ ቡድኑ ባርሴሎና ላቫንቴን 5 ለዜሮ በመርታት ከመሪው ሪያል ማድሪድ ጋር ትንቅንቁን አጠናቅሮታል። በቡንደስሊጋው ባየር ሙይንሽን ሐምቡርግን 8 ለባዶ አንኮታኩቷል። አርሰናል በእንግሊዝ FA Cup ድል ቀንቶታል። በጣሊያን ሴሪኣ ዝቅተኛ ነጥብ ያላቸው ኹለት ቡድኖች ኃያላኑን ቡድኖች ተፈታትነው ነጥብ አስጥለዋል።

የሱዳን መንግሥት ጦር ባለፈው ጥቅምት በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍለ ሃገር በዳርፉር ከተማ በርካታ ሴቶችና ህፃናትን ደፍሯል ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩመን ራይትስ ዋች ባለፈው ሳምንት አጋልጧል ።

የዩክሬን መንግስት እና አማጽያን በሳምንቱ መጨረሻ የተፈራረሙት ስምምነት በአንድ ቀን ተጣሰ። የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጄኔፈር ፓሳኪ ሩሲያ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በምስራቅ ዩክሬን አሰማርታለች ሲሉ ከስሰዋል።

ኮፕንሐግን በሚገኝ አንድ የአይሁዳዊያን ፀሎት ቤት ፊት ለፊት ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ቆሰሉ። የዴንማርክ ፖሊስ እንዳስታወቀው ከቁስለኞቹ መካከል ሁለቱ ፖሊሶች ናቸው። ይህ ከሆነ ከሰዓታት በኋላ ፖሊስ በእግሩ እንደሸሸ የተነገረውን ተጠርጣሪ ማግኘቱን እና መግደሉን ይፋ አድርጓል።

ዩጋንዳ በሀገሯ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ዓማፅያን ሀገሯን ለቀው እንዲወጡ ከጥቂት ቀናት በፊት ትዕዛዝ አስተላልፋለች። ይኸው የዩጋንዳ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ የወሰዱት ውሳኔ ከዓማፅያኑ ብርቱ ወቀሳ ተፈራርቆበታል።

ሴራሊዮን መዲና ፍሪታውን ውስጥ 6 ግለሰቦች ላይ እንደ አዲስ የኢቦላ ተሐዋሲ ምልክት በመታየቱ በመዲናዋ የሚገኙ 700 ቤቶች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች መግባት መውጣት መከልከላቸው ተዘገበ።

የብሪታኒያና የዩናይትድ ስቴትስ የጦር አውሮፕላኖች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ የምስራቅ ጀርመንዋን የድሬስደን ከተማ እንዳልነበረች ያደረጉበት የቦምብ ድብደባ ልክ ዛሬ 70 ዓመት ደፍኗል ።በአየር ድብደባው 25 ሺህ ሰዎች እንደሞቱ ሲገመት አብዛኛዎቹ የከተማዋ ውብ ህንፃዎችና የስነ ጥበብ ቅርሶችም ወድመዋል ።

እጎአ የካቲት 14 ቀን ማለትም ነገ በየአመቱ የፍቅረኛሞች ቀን ወይም «ቫለንታይንስ ደይ» ይከበራል። ይህ ቀን በምዕራቡ ሀገራት ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ዘንድም በደማቅ መከበር ከጀመረ ሰነበተ።

ደቡብ አፍሪቃ ከዘር መድሎ ሥርዓት ነፃ ከወጣች ወዲሕ ከ1,6 ሚሊዮን የሚበልጥ ስደተኞች ይኖሩባታል ተብሎ ይገመታል።የነጭ ዘረኞቹ ሥራዓት «ሐገር አልባ» አድርጓቸዉ የነበሩት የቀድሞዎቹ ስደተኞች ግን የዛሬዉቹን ለማስታናገድ የፈቀዱ አልመሰሉም።

መሪዎቹ ከዚሕም በተጨማሪ ሥለግሪክ የምጣኔ ሐብት ቀዉስ፤ በተጠርጣሪ አሸባሪዎች ላይ መንግሥታቱ ሥለሚያደርጉት ቁጥጥርም ተነጋግረዉ።አዉሮጳ መድረሻ ሜድትራንያን ባሕር ዉስጥ የሚረግፉት የአፍሪቃዉያን ስደተኞች እልቂት ግን በሕብረቱ መሪዎች ዘንድ ከቁብ አልተቆጠረም

ሰሜን አዉሮጳዉቱ ሐገር ፊንላንድ- የመጀመሪያዉን ሥፍራ ይዛለች።ምሥራቅ አፍሪቃዊቱ ኤርትራ ደግሞ አምናም እንደ ሐቻምናዉ ኡራ ወጥታለች።ከአንድ መቶ ሰማንያ ሐገራት አንድ መቶ ሰማንያኛ።አጠቃላዩ የፕረስ ነፃነት ይዞታ ግን ድርጅቱ እንደሚለዉ በአምስቱም ክፍለ-ዓለማት አምና ክፉኛ እሽቆልቁሏል::

ካለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ በእስራት የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመሥገን ደሳለኝ እናት ወይዘሮ ፋናዬ እርዳቸው ልጃቸውን መጠየቅ እንዲችሉ በመጠየቅ ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት እና ለፌዴራል የሕዝብ እንባ ጠባቂ ኮሚሽን፣ እንዲሁም ለውጭ ሀገር ኤምባሲዎች ደብዳቤ መላካቸውን አስታወቁ።

አዳም ረታ፤በውቀቱ ስዩም ፤እንዳለጌታ ከበደ፤ስንቅነህ እሸቱ ፤አለማየሁ ገላጋይ ፤ግርማ ተስፋው ፤ እንዬ ሺበሺ ባለፉት አስር አመታት ረጅም ልብ ወለድ ለህትመት ካበቁ የኢትዮጵያ ደራስያን መካከል ይገኙበታል።

አዲስ አበባ እና የጀርመን የላይፕሲኽ ከተሞች የመሠረቱ የእህትማማችነት ግንኙነት እና ትብብር አሥረኛ ዓመት ሆነው። ይህንኑ ምክንያት በማድረግ ወደ አንድ መቶ ሰው ያጠቃለለ አንድ የላይፕሲኽ ከተማ የልዑካን ቡድን በአሁኑ

የየመን የፀጥታ ይዞታ እየተባባሰ መሄዱ እየተነገረ ነዉ። የሀገሪቱ የታጠቁ ኃይሎች እንቅስቃሴ ያሰጋቸዉ የዉጭ ዲፕሎማትና ኤምባሲዎችም መዘጋታቸዉ ተዘግቧል። እንደዘገባዎቹ ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያና ፈረንሳይ ኤምባሲዎች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዉ ሠራተኞቻቸዉም ከየመን ወጥተዋል።

በላስ ቬጋስ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ፣ በባርሴሎና ፤ እስፓኝና በሃኖፈር ፣ ጀርመን በያመቱ ከጥር አንስቶ እስከ ሚያዝያ በየተራ ስለሚካሄድ የኤሌክትሮኒክስ ዐውደ ርእይ፣ ባለፈው ዝግጅታችን ስናወሳ ፣ ከሞላ ጎደል ስለ «ናኖ ቴክኖሎጂ» ጭምር መግለጻችን

ቪዥን ኢትዮጵያን ኮንግረስ ፎር ዴሞክራሲ የተባለ አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ከመጪዉ ምርጫ ጋ በተያያዘ ዴሞክራሲና የሕዝብ ተሳትፎን በሚመለከት የአንድ ቀን አዉደጥናት አካሄደ።

አንድ ለውሁዳን ጎሳዎች የሚሟገት የጀርመናውያን ድርጅት የስዊትዘርላንድ መንግሥት የተገን ማመልከቻቸው ተቀባይነት ያላገኘላቸውን ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ወስዶት የነበረውን ውሳኔ ሰሞኑን የሻረበትን ድርጊት አሞገሰ።

ባለፈው ሰኞ በሜዲትራንያን ባህር በኩል ወደ ኢጣልያ በጀልባ በመጓዝ ላያ የነበሩ የ27 አፍሪቃውያን ስደተኞች አሳዛኝ እሟሟት አነጋግሮ ሳያበቃ ዛሬ ደግሞ ከ300 በላይ ስደተኞች የተሳፈሩባቸው ጀልባዎች ሰጥመው እዚያው ሜዲትራንያን ባህር ውስጥ ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተዘግቧል ።

አዲሱ የሶማሊያ ካቢኔ ሃገሪቱን ከሁከትና አመፅ ነፃ አድርጎ የመምራት ሃላፊነት ተረክቧል ። 25 አባላት ያሉት አዲሱ ካቢኔ ከትናንት በስተያ ነበር በሶማሊያ ፓርላማ የፀደቀው ። የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦማር አብዱረሺድ አሊ ሻርማርኬ ለፓርላማው ያቀረቡት ካቢኔ የጸደቀው ከ3 ሙከራ በኋላ ነው ።

የመኢአድ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ግን ፓርቲያቸዉ ቀደም ሲል በወጣዉ የጊዜ ሰሌዳ ዕጩዎቹን ያላስመዘገበዉ በፓርቲዉ ዉስጥ ለተፈጠረዉ ችግር ራሱ ምርጫ ቦርድ ፈጣን ዉሳኔ ባለመስጠቱ ነዉ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አዲሱን የመኢአድ ጥያቄ አልተቀበለዉም።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ1970-እስከ 2008 በተቆጠረዉ ሐምሳ- ዓመት ግድም ከኢትዮጵያ 16.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ዉጪ መዉጣቱን አንድ ጥናት ጠቆመ።ባለፉት አርባ-ስምት ዓመታት ከመላዉ አፍሪቃ ወደ ዉጪ የወጣዉ የተጭበረበረ ገንዘብ መጠን አንድ ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል።

ግሪክ በብድርና እዳዋ ላይ ለመደራደር ባቀረበችው ሃሳብ ላይ የአውሮፓ ሃገራትን ድጋፍ ለማግኘት እየጣረች ነው ።የግሪክ የገንዘብ ሚኒስትር ያኒስ ቫሩፋኪስ ለችግሩ መፍትሔ የሚሉትን እቅድ ነገ ብራሰልስ ውስጥ ለዩሮ ተጠቃሚ አባል ሃገራት ማህበር ያቀርባሉ ።ይሁንና የግሪክ አዲስ ሐሳብ ተቀባይነት ማግኘቱ አጠራጣሪ እንደሆነ ነው ከወዲሁ የሚነገረው ።

30ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ «ዝሆኖቹ» በመባል የሚታወቁት ኮትዲቯሮች እጅ ገብቷል። እሁድ የካቲት 1 ቀን 2007 ዓም ጋናውያን በእንባ ታጥበዋል። በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ቦሩስያ ዶርትሙንድ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፎ ከወራጅ ቃጣናው ወጥቷል። በስፔን ላሊጋ ሪያል ማድሪድ ከባድ ሽንፈት ገጥሞታል። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ቸልሲ እየገሰገሰ ነው።

ዲፕሎማሲዉን ደጋግሞ ከመሞከር ይልቅ ከተፋላሚ ሐይላት አንዱን ለይቶ መቅጣት፤ሌላዉን ማስታጠቁ መፍትሔ ይሆን ይሆናል።መፍትሔዉ ሠላማዊ ሊሆን ግን አይችልም።ሐያላኑ ልዩነት፤አለመግባባታቸዉን «በጠመንጃ ሐይል» ለመፍታት እያሰቡ ወይም እየሞከሩ ለደካማዉ ዓለም ችግር ፍትሐዊ መፍትሔ አለን ቢሉ ፈርቶ እንጂ ወዶና አምኖ የሚቀበል መኖሩ አጠራጣሪ ነዉ

በማህበራዊ ኑሮ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ የሕፃናት፣ ወጣቶች እና ሴቶች ጉዳዮች ሚንስቴርን እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የምታማክረው ወጣት ናርዶስ ቹታ በከተማ እና በገጠር በመዘዋወር አዳጊ ህፃናት እና ወጣቶች የሚያጋጥማቸውን የተለያዩ ችግሮችን ምክንያት በመመርመር አንድ ጥናት አዘጋጀች።

የፈረንሳይ እና የአፍሪቃ ሀገራት ጉባዔ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በፓሪስ ተካሄደ። በዚሁ « ሁሉን የሚያሳትፍ እድገት » የሚል ርዕስ በተሰጠው ጉባዔ ላይ ከአፍሪቃ ጋር ያላትን የኤኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነት የማጠናከር ፍላጎት ያላት