ወጣቶችና የአዳዲስ ግኝቶች ውድድር
ሥነ ቴክኒክ እየተስፋፋ በመጣበት ፤ በአሁኑ በ 21ኛው ክፍለ-ዘመን ፣ ሥራ ከመፈለግ ፣ ሥራ መፍጠር ይሻላል የሚል እምነት ያላቸው በኢንዱስትሪ በበለጸጉትና በአዳጊ ሀገራትም የሚገኙ ወጣቶች ቁጥር የመጨመር ምልክት እየታያበት መሆኑ ይነገራል ።
ሥነ ቴክኒክ እየተስፋፋ በመጣበት ፤ በአሁኑ በ 21ኛው ክፍለ-ዘመን ፣ ሥራ ከመፈለግ ፣ ሥራ መፍጠር ይሻላል የሚል እምነት ያላቸው በኢንዱስትሪ በበለጸጉትና በአዳጊ ሀገራትም የሚገኙ ወጣቶች ቁጥር የመጨመር ምልክት እየታያበት መሆኑ ይነገራል ።
የአፍሪቃ ህብረት አባል ሃገራት የመሪዎች ጉባኤ ክፍለ ዓለሙን በሚፈታተኑ ችግሮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚነጋገር ይጠበቃል ። ቦኮሃራም ፣ኤቦላ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ እና ደቡብ ሱዳን ጉባኤው ከሚያተኩርባቸው ርዕሶች ውስጥ ይጠቀሳሉ ።ጉባኤው በአባል ሃገራት መዋጮ የሚሰማራ ፀረ ሽብር ኃይል ማቋቋም የሚቻልበትን መንገድም ይፈልጋል ።
በኤቦላ ወረርሽኝ አስተላላፊ ተኀዋሲ የሚያዘው ሰው ቁጥር በርግጥ እየቀነሰ መጥቶዋል። ይህ ግን ችግሩ በምዕራብ አፍሪቃ ቀንሶዋል ማለት አይደለም። በመሆኑም፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሽታውን በመታገሉ አኳያ ከዚሁ አካባቢ ጋር ትብብሩን ማጠናከር ይጠበቅበታል።
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የልማት ስራዎች በሚያደርገው ድጋፍ የራሱን ህግጋት እና መርሆዎች በተደጋጋሚ መጣሱ ተነገረ።የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ባንክ ያገኘውን የገንዘብ ድጋፍ በጋምቤላ ክልል ለሚያደርገው የግዳጅ የሰፈራ መርሐ-ግብር ሲጠቀምበት ቆይቷል የሚል ወቀሳም ይሰነዘርበታል።
በአዲስ አበባ በጥንታዊነቱ የታወቀው የመጀመሪያው ዘመናዊ ሆቴል ፤ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል፣ ጥር 3 ቀን ጧት ተቃጠሎ ከባድ ጉዳይ እንደደረሰበት ይታወቃል።
ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚበቅለዉ የጫካ ቡና ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ማደጉ በዓለም ቡና ጠጭዎች ዘንድ ተወዳጅነት ማትረፉ ይነገርለታል።
በኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልል 100 ሺ ሄክታር መሬት ለእርሻ ስራ የተኮናተረዉ የህንዱ ካራቱሪ ኩባንያ መክሠሩን የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ። ኩባንያው ከተረከበዉ መሬት ያለማው 1,340 ሄክታር ብቻ ነው።
በዕሁዱ የግሪክ አጠቃላይ ምርጫ ያሸነፈው ግራ ዘመሙ ሲሪዛ የግሪክ ፓርቲ ፣ነፃ የግሪኮች ፓርቲ ከተባለው የቀኝ ክንፍ ብሔረተኛ ፓርቲ ጋር ጥምር መንግሥት መስርቷል ።በግሪክ ላይ የተጫኑትን የቁጠባ እርምጃዎች የሚቃወሙት እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ሥልጣን መያዛቸው ትኩረት ስቧል ።
የዩናይትድ ስቴትስን ሰሜን ምሥራቃዊ ግዛቶች ጠንካራ የበረዶ ዉሽንፍር እንደመታ ዘገባዎች ያመለክታሉ። እስከ60 ሴንቲ ሜትር እንደሚደርስ የተነገረዉ እጥጥ ባዘቶ ብናኝ ወርዶ የሚከመረዉ በረዶ በተለይ የኒዮርክ ግዛትን ከነፋስ ጋ ተዳምሮ ነዉ የገረፈዉ።
ፔጊዳ የተሠኘውን እሥልምናን የሚጠላውን የጀርመን ቡድን የሚያወግዝ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባና የሙዚቃ ድግስ ቡድኑ ንቅናቄውን በጀመረበት በድሬስደን ከተማ ትናንት ምሽት ተካሂዷል ። ታዋቂው ጀርመናዊ የዘመናዊ ሙዚቃ አቀንቃኝ ኽርበርት ግሮነማየር ባስተባበረውና በርካታ ሙዚቀኞች በተካፈሉበት የአደባባይ ትርዒት ላይ ከ35 ሺህ በላይ ሕዝብተገኝቷል ።
ራሱን የሱዳን ሰፊ ብሔራዊ አገር አቀፍ ግንባር ያለው በዛያሉ ፓርቲዎችን የወጣቶችድርጅቶችን እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦችንያቀፈው የሰብስቦች ግንባር(ንቅናቄ) ፕሬዚዳንት አሊሐሰን አሕመድ ሐሰኔይ በተለያዩ የምዕራብ አውሮፓ መዲናዎች በመዘዋወር
ኢትዮጵያውያን በዱባይ ማራቶን ከ1ኛ እስከ 10ኛ በመግባት እጅግ አመርቂ ድል አስመዝግዋል፣ የብር ሽልማትም አግኝተዋል። በዓለም አቀፍ የቢስክሌት ውድድር ኢትዮጵያዊው አበረታች ውጤት አምጥቷል። የዓለማችን ኮከብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። በኤፍ ኤ ካፕ ውድድር ቸልሲና ማንቸስተር ሲቲን ጨምሮ ኃያላኑ በትንንሾቹ ጉድ ሆነዋል።
የአሜሪካ ሕዝብን ደሕንነት ለመጠበቅ ዋሽግተኖች ሰሞኑን ያደረጉት አብዛኛ ዜጎቻቸዉን ከየመን ማስወጣት ነዉ።የመኖች የት ይሒዱ?አደባባይ ወጡ።ሁቲን በመቃወምና በመደገፍ።የመን ቀይ ባሕርን፤የአደን ባሕረ-ሰላጤና አረቢያ ባሕር ይገናኙባታል።ከሁለት ሺሕ ኪሎ ሜትር የሚበልጥ የባሕር ጠረፍ አላት።ጥንታዊናት ሰፊ ።ግን ከአረብ ሐገራት ሁሉ ደሐ
በሰሜን ፈረንሳይ የወደብ ከተማ ካሌ የሠፈሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ተገን ጠያቂ ስደተኞች የኑሮ ሁኔታ ኢሰብዓዊ ነው ሲል የመብት ተሟጋቹ ድርጅት «ሂውመን ራይትስ ዎች» ወቀሰ። ድርጅቱ ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ እንዳስታወቀው፣
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ትናንት በአዲስ አበባ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቶ የነበረ ሲሆን፣ የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች ሰልፍ ለመዉጣት በዝግጅት ላይ እንደነበሩ በፌዴራል ፖሊስ የኃይል ተግባር
ብሪታንያዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ዶክተር ማርቲን ሂል በ71 ዓመታቸው አረፉ፣ ባለፈው ዓርብ በለንደን ሥርዓት ቀብራቸው የተፈፀመው ማርቲን ሂል በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ፣ አምነስቲ
የዓለም ዜና፤ ጥር 17 ቀን 2007 ዓም
በተለያዩ መንገዶች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት ለሥራ የሚሄዱ ኢትዮጵያውን ልዩ ልዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈፀምባቸው ተደጋግሞ ሲነሳ ቆይቷል ።
ራሱን ፔጊዳ ማለትም «በምዕራባውያን ሃገራት የእስልምና መስፋፋት ተቃዋሚ የአውሮጳ አርበኞች» ብሎ የሚጠራው ቡድንን በመቃወም ዛሬ በጀርመን ፍራንክፉርት ከተማ ትዕይንተ-ሕዝብ ተካሂዷል።
የደቡብ ሱዳን ገዢ ፓርቲ ፣ የሱዳን ሕዝብ ነፃ አውጪ ንቅናቄ፣ «ኤስ ፒ ኤል ኤም» ተቀናቃኝ አንጃዎች ባለፈው ረቡዕ የሥልጣን መጋራት ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል። ይኸው በገዢ ፓርቲ ውስጥ የተፈጠረውን ልዩነት ለማብቃት እንደሚረዳ የሀገሪቱ ሕዝብ ተስፋ አድርጓል።
የኤርትራ መንግሥት 6 ዓመት ገደማ በእሥር ላይ ያቆያቸውን ጋዜጠኞች መፍታቱን ፤ ዋና ጽ/ቤቱ በፓሪስ፤ ፈረንሳይ የሚገኘው ድንበር አያግዴው የጋዜጠኞች ድርጅት (RSF) አስታውቋል። የተፈቱት ለራዲዮ ባና ይሠሩ እንደነበሩ የተነገረላቸው፤ በረኸት
ኢትዮጵያ ዉስጥ በመጪዉ ግንቦት ወር ለሚካሄደዉ አጠቃላይ ምርጫ ድምፁን ለመስጠት 33 ሚሊዮን መራጭ ሊመዘገብ እንደሚችል የምርጫዉ አስተባባሪ ባለስልጣናት ይገምታሉ። ወጣቱ በሚያመዝንባት ኢትዮጵያ፤ የወጣቱ የምርጫ ተሳትፎ ምን ይመስላል? የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ርዕሳችን ነው።
ብዙዉን ሰዉ እዚህ ያነጋገረዉ ጉዳይ ተጣርቶ መልስ ያገኘ ይመስላል ይላል የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤን በላከልን ዘገባ። ጋዜጣዎች ጽፈዋል፤ ሰዎች ሰልፍ ወጥተዋል እኛም ይላል ይልማ የኤርትራዊዉን ስደተኛ የወጣት ካሊድን ጉዳይ አንስተን ዘግበናል።
ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትየስዑድ አረቢያ ንጉሥ አብደላቢንአብድአዚዝአልስዑድ የቀብር ሥርዓት ዛሬ ተፈጸመ። በዘጠና ዓመታቸዉ ያረፉት የሳዉዲ ንጉሥ ታናሽ ወንድማቸዉን በአልጋወራሽነት ቀደም ብለዉ ሰይመዉ ነበር።
በያዝነዉ የጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ,ም የመጀመርያ የሙዚቃ ድግሳችን የኢትዮጵያን የአዝማሪ ሙዚቃን በቀጥታ ለማስደመጥ ቀርበናል፤ ሲል ነበር WDR የተሰኘዉ የጀርመኑ የራድዮ ጣብያ ሲያስደምጥ የነበረዉ ዝግጅት።
ሁለቱ መሪዎች በጋራ ለሁለቱ ሐገራት የኩባንያ ባለቤቶች፤ የድርጅት ተጠሪዎችና ነጋዴዎች ገለፃና ማብራሪያ ሰጥተዋልም
ጦርነት የገጠሙት የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች ትናንት አሩሻ ታንዛኒያ ላይ የእርስ በርስ ጦርነቱን ሊያስቆም የሚችል አዲስ ስምምነት መፈራረማቸዉ ተሰማ።
የኢትዮጵያ መንግሥት በመጪዉ ግንቦት ለሚካሄደዉ ምርጫ ነፃ ሃሳብን ለማገድ ሆኖ ብሎ የግል መገናኛ ብዙሃንን እየተጫነ ነዉ ሲል ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት ሂዉማን ራይትስ ዎች አመለከተ።
የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት(WHO) ዘመናዊ ሥልጣኔ ያጎናጸፈው ምቾት እስከምን ድረስ ለቅሥፈት እንደሚዳርግ ሲያስጠነቅቅም ሆነ ሲያሳስብ፤ «የሥልጣኔ በሽታዎች» ባላቸው የበሽታ ዓይነቶች ሳቢያ በያመቱ ምን ያህል ሰዎች እንደሚሞቱ በሚያወጣው መዘርዝር ጥናት ላይ ያሳያል።
የናይጀሪያው ፅንፈኛ ቡድን ቦኮ ሀራም የሽብር ተግባሩን ከሰሜናዊ ናይጀሪያ አልፎ አሁን ወደ ጎረቤት ሀገራት ማስፋፋት መጀመሩ ባካባቢው ትልቅ ስጋት ፈጠረ። በናይጀሪያ ስለቀጠለው የቡድኑ ጥቃት ትናንት የመከረው የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ቡድኑ ለጠቅላላ ምዕራብ እና ማዕከላይ አፍሪቃ ትልቅ አደጋ መደቀኑን አስታውቋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ዖባማ፤ በምዕተ ዓመቱ 15ኛ ዓመት መግቢያ ወር ላይ ትናንት ለህዝባቸው ባሰሙት ንግግር ፣ ዐበይት ያሏቸውን አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች አንስተዋል። በሀገር ውስጥ ለኤኮኖሚው ዐቢይ ግምት ሲሰጡ፤
የኪየቭ ሞስኮዎች መወነጃጀል፤ የሞስኮ ዋሽግተን-ብራስልሶች መወጋገዝ፤ መበቃቀልም እንደናረ ነዉ።፤ በዚሕ መሐል የፈረሰዉ የሠላም ዉል ገቢር ይሆናል ብሎ ማሰብ አንዳዶች እንደሚሉት የዋሕነት ነዉ።ዩንግ ግን ሌላ ምርጫ የለም ባይ ናቸዉ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠላም ማጣትዋ «አሳሰበኝ» ይልላታል።ዩናይትድ ስቴትስ የአል ቃኢዳ «አባላት» የምትላቸዉን ትገድልባታለች።ሳዑዲ አረቢያና ኢራን ይሻኮቱባታል ይባላል።አሸባሪዎች በቦምብ ያተራምሷታል፤የጎሳ ታጣቂዎች፤አማፂያን፤ እና ወታደሮች ይዋጉባታል።ደቡብ አረቢያዊቱ ሐገር እዉነት ዓለም ሊያተራምስ ይችላል እንደ ዩሱፍ ያሲን።
የኮንጎ ዴሚሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ ዘመነ-ሥልጣናቸዉን ለማራዘም ማቀዳቸዉን በሚቃወሙ ሠልፈኞችና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል ትናንት የተጀመረዉ ግጭት ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።
ከአየር ንብረት ለዉጡ ጋ ተገናኝቶ ይሁን ግልፅ ባይሆንም በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ሃገራት የክረምቱ የቅዝቃዜ ደረጃ መለዋወጥ ከጀመረባቸዉ ዓመታት ወዲህ ያልተጠበቁ ክስተቶች እየታዩ እንደሆነ ይነገራል። ከለዉጦቹ አንዱ ካለፉት ስምንት ዓመታት ወዲህ በመላዉ ዓለም የታየዉ ማር የሚሠሩት ንቦች ቁጥር እያነሰ የመሄዱ ጉዳይ ነዉ።
የኢትዮጵያን ቡና ወደ አዉሮጳ በብዛት በማስገባት ጀርመን ቀዳሚነቱን ይዛ ብትገኝም ፈረንሳይ ከዓመታዊ የቡና ፍጆታዋ ስድስት በመቶዉን የምታስገባዉ ከኢትዮጵያ መሆኑ ተሰምቷል። ሰሞኑን በፓሪስ ፈረንሳይ የኢትዮጵያን ቡና ፤ የኢትዮጵያን ባህልና የጥበብ ሥራዎችን የሚያስተዋዉቅ ዝግጅት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ካሜሩን አሸባሪው ቡድን ቦኮ ሀራም በናይጀሪያ አጠናክሮ የቀጠለው ጥቃት ዒላማ ከሆነች ሰንበት ብሏል። ቡድኑ ያን ያህል ጥበቃ የማይደረግበትን ሁለቱን ሀገራት የሚያዋስነውን ድንበር እየተሻገረ የእገታ እና የኃይል ተግባሩን አስፋፍቶዋል።
ከአስር ቀናት በፊት በፓሪስ ፈረንሳይ አክራሪ እስላማዊ አሸባሪዎች ጥቃት ፈፅመዉ 17 ሰዎችን ከገደሉ ወዲህ የአዉሮጳ መንግሥታት በሽብርተኝነትና አሸባሪዎች ላይ ጠንካራ ርምጃ ለመዉሰድ የሚያስችላቸዉን ስልት መንደፋቸዉን እያስታወቁ ነዉ።
ትናንት በምስራቅ ጀርመንዋ በድሬስደን ከተማ ፔጌዳ በተባለው ቡድን የተጠራው ና የፔጊዳ ተቃዋሚዎች ሊያካሂዱ ያቀዷቸው ሰልፎች መታገዳቸው እዚህ ጀርመን ማነጋገሩ ቀጥሏል ።እገዳው በጀርመን ሃሳብን በነፃ መግለፅን ተጋፍቷል የሚል ወቀሳ ተሰንዝሮበታል ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአምባገነንነት ወደዴሞክራሲ ለሚደረገዉ ሽግግር እንዲረዳዉ በነቂስ ወጥቶ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ ዘጠኙ ተጣማሪ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረቡ።
በኢትዮጵያ በክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ የጥምቀት በዓል በደማቅ ተከብሮአል። የጥምቀት በዓል ከጊዜ ወደ ጊዜ የዓለም አቀፉን ሕብረተሰብ ቀልብ እየሳበ በመምጣቱ የአከባበር ሥነ-ስርዓቱን በተመ የትምሕርት፤የሳይንስና የባሕል ድርጅት «UNESCO» ጥበቃ ስር በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተመልክቶአል።
በምጸታዊ ካርቱኖቹ የሚታወቀው የፈረንሳዩ ሻርሊ ኤብዶ ጋዜጣ ከተፈጸመበት ጥቃት ማግስት ለህትመት የበቃው እትም በዓለም ዙሪያ ቁጣን ቀስቅሷል። በድጋሚ በነብዩ መሐመድ ላይ የሚሳለቅ ምስል ይዞ ብቅ ያለው የፈረንሳይ ጋዜጣ በእስያ፤መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪቃ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።
ፖሊስ ደርሶኛል ባለው መረጃ ምክንያት የድሬስደኑ ሰልፍ ቢገፋም በሌሎች የጀርመን ከተሞች ግን ፔጊዳ የጠራቸው ሰልፎች ይካሄዳሉ ።
የአይቮሪኮስቱ አጥቂ ዊልፍሬድ ቦኒ በ32,3 ሚሊዮን ዩሮ ከስዋንሲ ሲቲ ወደ ማንቸስተር ሲቲ ተዛውሯል። የክሮሺያው ግብ አዳኝ ወጣት አንድሬ ክራማሪችም የእንግሊዙ ሌስተር ሲቲን ተቀላቅሏል። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ውጤቶች የሚንደረደረው የዛሬው የስፖርት ጥንቅራችን ዝውውርን የሚመለከቱ እና ሌሎች ስፖርት ነክ ዜናዎችን አካቷል።
ከ30በላይ የዓለም ቋንቋዎች ዝግጅቶችን የሚያሰራጨዉ ዶይቼ ቬለ ራድዮ እና የጀርመን የባህል ተቋም በመተባበር ባዘጋጁት መድረክ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሦስት ትምህርት ቤቶች ለተዉጣጡ ተማሪዎች በሙዚቃ የተደገፈ የጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርት ተሰጠ።
ኩሊባሊ የኮሸር የገበያ አዳራሽ ሺያጭ-ሸማቾችን አግቶ ጥያቄዉ ካልተሟላለት ታጋቾቹን እንደሚገድል ሲዝት፤ ሲፎክር፤ ባቲሌይ እቅርቡ ያሉትን ገበያተኞች ይዞ-ከምድር በታች ወደሚገኘዉ ሸቀጥ ማከማቻ ክፍል ወረደ።
ከጀርመን ከተሞች፤ እንደ ድሬስድን እስልምና እንዳይስፋፋ የሚታገል ከተማ የለም። ባለፉት የሰኞ ሳምንታት ድሬስድን ውስጥ እስልምና እንዳይስፋፋ የሚታገሉ የፔጊዳ ደጋፊዎች ድሬስድን ከተማ ሰልፍ ሲወጡ ሰንብተዋል። የነገው ሰልፍ ግን የሽብር ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል በሚል ፍራቻ ፖሊስ በከተማዋ ማንኛውም አይነት የአደባባይ ሠልፍ እንዳይደረግ አገደ።