የተገታተሩ ደም ሥሮች/ሔሞሮይድስ
ኪንታሮት በተለያዩ የሰዉነት ክፍሎቻች ላይ የሚወጣ ከቆዳ በሽታዎች አንዱ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ። መነሻ ምክንያቱ ደግሞ ቫይረስ ወይም ተሐዋሲ ነዉ።
ኪንታሮት በተለያዩ የሰዉነት ክፍሎቻች ላይ የሚወጣ ከቆዳ በሽታዎች አንዱ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ። መነሻ ምክንያቱ ደግሞ ቫይረስ ወይም ተሐዋሲ ነዉ።
የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙ 6 የኦሮሞ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በድሎናል ሲሉ አማረሩ ። የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ግን ያልተፈታ ችግር እንደሌለና በተለይ በአባላት ላይ ይደርሳል ስለተባለው እንግልት ቦርዱ እንዳልሰማ ተናግረዋል ።
ቦነር ነታንያሁን የጋበዙት እኛን ሳያማክሩ ነው ከሚሉት የዴሞክራት ፓርቲ እንደራሴዎች ወደ 40 ያህሉ ንግግሩን ላይ እንደማይገኙ አስታውቀዋል ።
የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን በምዕራብ አፍሪቃ የተከሰተውን የኤቦላ ስርጭት ለማብቃት ያደረገውን ጥረት ውጤት ለመመልከት ዛሬ በብራስልስ ጉባዔ አካሄደ።
የሞ ኢብራሂም ድርጅት የመልካም አስተዳደር ሽልማቱን ትናንት እንደገና ለአንድ አፍሪቃዊ መሪ ሰጠ። የድርጅቱ ሽልማት ሰጪ ኮሚቴ እንዳስታወቀው፣ ዘንድሮ ለዚሁ ሽልማት የበቁት ተሰናባቹ የናሚቢያ ፕሬዚደንት ሂፊኬፑንዬ ፖሀምባ ናቸው።
እጎአ በ2022 በረሃማዋ ቓታር ውስጥ ሊከናወን ዕቅድ የተያዘለት የዓለም ዋንጫ ውድድር ከወዲሁ ውዝግብ አስነስቷል። የአውሮጳ ቀዳሚ ሊጎች ያከናወኑዋቸውን ጨዋታዎች ከእንግሊዝ ተነስተን ጀርመን፣ ብሎም ስፔን እና ጣሊያን ደርሰን እንቃኛለን።
የኢራቅ ጦር በ«እስላማዊ መንግሥት፣ አይ ኤስ» አንፃር ግዙፍ ዘመቻ ጀመረ። ጦሩ በዚሁ ዘመቻው በ«አይ ኤስ » ቁጥጥር ስር የምትገኘዋን የቲክሪት ከተማ ነፃ የማውጣት ዓላማ አለው።
የሁቲ አማፂዎች ርዕሰ-ከተማ ሰነዓ የዶለዉ ግን ከኢራን ርዳታ ይልቅ በዩናይትድ ስቴትስና በአረብ ተባባሪዎችዋ የሚረዱት የየመን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ግራ አጋቢ ግን ተመሳሳይ የጅል ስልት ነዉ።የፕሬዝዳንት አብድ ረቦ መንሱር ሐዲ፤ የዓሊአብደላ ሳላሕና የጄኔራል አሊማ ሑሴይን ተቃራኒ ግን ተመሳሰይ ሴራ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ፤ በአፄ ዳግማዊ ምንይልክ መሪነት ፣ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ ም ፤ ቅኝ ግዛት ለማስፋፋት ዘምቶ በነበረው የኢጣልያ ጦር ላይ ድል የተቀዳጀበት 119ኛው የአድዋ ድል በዓል፤ ዛሬ በሀገሪቱ በመላ ተክብሮአል ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ ም ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው አገር አቀፍ ምርጫ ፤ የምርጫ ዘመቻውና የገጽ-ለገጽ ክርክሩም ከትናንት በስቲያ ተጀምሮአል።
ባለፉት 5 ዓመታት ኢትዮጵያ በህገ ወጥ የገንዘብ ፍሰት ያጣችው ገንዘብ መጠን 10 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል ። ኢትዮጵያም አጣች የተባለው ገንዘብ በሃገሪቱ ድህነትን ለመቀነስ የተወሰዱትን እርምጃዎች ሊያፋጥን ይችል እንደነበርም ነው የተገለፀው ።
70 ሽህ የሚሆን የሞስኮ ነዋሪ በክሬምሊኑ ቤተ-መንግሥት ላይ የሰላ ትችት በማቅረባቸዉ የሚታወቁት የሩስያ መንግሥት ዋንኛ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቦሪስ ኔምትሶፍ ግድያን በተመለከተ ሐዘኑን በሰልፍ ገለፀ። የሩስያዋ ሁለተኛ ሰፊ ከተማ በሆነችዉ በሳንክት ፒተርስበርግም ቢያንስ 2500 ተቃዋሚ ሰልፈኞች አደባባይ በመዉጣት ሐዘናቸዉን ገልፀዋል።
በደቡባዊ አፍሪቃ በምትገኘው ንዑሷ ሀገር ሌሶቶ ወይም በሌላ አጠራሯ ባሶቶ ውስጥ በዛሬው ዕለት ምክር ቤታዊ ምርጫ ተካሄደ። ከታቀደለት ጊዜ አስቀድሞ የተካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ ቀደም ሲል የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የተደረገባትን ሀገር ያረጋጋል ተብሎ ታስቧል።
ስለየተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች አናኗኗር እና ባህል ዘግቧል። ወጣቱ ጋዜጠኛ በኢትዮጵያ ተዘዋውሮ ስላየው ከመዘገብ ባለፈ ፤ከፊል ጉዞውን የሚገልፅ አንድ መፅሀፍም አሳትሟል።
የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሃይሎች ድርድር በምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ-መንግስታት አማካኝነት አዲስ አበባ ላይ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ድርድሩን በጥሞና የሚከታተሉ የፖለቲካ ተንታኞች ድርድሩ ፋይዳ ቢስ ነው ሲሉ ይተቻሉ።
ዛሬ ያስቻለዉ የአዉሮጳ ሕብረት ፍርድ ቤት ግን የሺፕሐርድን የጥገኝነት ጥያቄ አልደገፈዉም።ጨርሶም ዉድቅ አላደረገዉም።በፍርድ ቤቱ ዉሳኔ መሠረት ሺፕሐርድ አልዘምትም ለማለቱ ወይም የነበረበትን የጦር ክፍል ለመክዳቱ ያቀረበዉን ምክንያት በመረጃ ማስደገፍ አለበት።
በአዲስ አበባ የደቡብ አፍሪቃ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች፤ ሠላዮች፤ ከኢትዮጵያ የመረጃ ሰዎች ጋር ይራኮቱ-ገቡ።ቢያንስ አራት ጠባቂዎች-እሕል ዉሐ ሳይቀምሱ የአፍሪቃ ሕብረት ፅሕፈት ቤትን ሙጥኝ አንዳሉ አራት ቀን ዉለዉ አደሩ።ሴትዮዋም ከግድያ ሴራዉ አመለጡ።
«እኛ ሃገር ባህላዊ ሆነዉ እየተከበሩ ያሉት በዓላት የሐይማኖት በዓላት ናቸዉ። የሐይማኖት በዓላት እድሜ ለአባቶቻችን እና ለእናቶቻችን ከባህላችን ጋር በደንብ አድርገዉ እንደ ጥሩ ስፊት እንደ ጥሩ ስንደዶ ማንም በማያላቅቀዉ ሁኔታ ሰፍተዋቸዋል። የካቲት 12 እኮ ዳቦ አይቆረስለት፤ ቡና አይፈላለት፤ በግ አይታደርለት ጠላ፤ አይጠመቅለት።
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲ እጩዎና አንዳንድ የግል ተወዳዳሪዎች በመጪዉ ምርጫ እንዳይሳተፉ በእጣ መገለላቸዉ እየተነገረ ነዉ።
በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ሶማሊያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሰዉ ከአልቃይዳ ጋ ትስስር እንዳለዉ የሚነገርለት ፅንፈኛ እስላማዊ ታጣቂ ቡድን አሸባብ በዩናይትድ ስቴትስ፣ ካናዳ፤ ብሪታኒያ እንዲሁም በሌሎች የምዕራብ ሃገራት በሚገኙ የገበያ ማዕከላት ላይ ጥቃት እንደሚያደርስ መዛቱ ተሰምቷል።
የዐባይ ወንዝ ተፋሰስ ሀገራት ፣ ወንዙን በጋራ ለልማት የመጠቀም መብታቸውን የሚያስከብር የውል ሰነድ አብዛኞቹ ከፈረሙ ወዲህ የዋናይቱ አፈንጋጭ ግብፅ ወሳኝ አቋም ምን እንደሚሆን ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኖ መቆየቱ የሚታበል አይደለም። «ግብጻውያን አንዲት
«ተመልሰናል» በሚል ርዕሥ ዛሬ ለገበያ የቀረበዉ ጋዜጣ የሐይማኖት መሪዎችን፤ የፈረንሳይ ቀኝ አክራሪ ፖለቲከኞንና የጂሐዲስት ተዋጊ ምሥልን ይዞ ነዉ የወጣዉ።
የኬንያ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ከአከራካሪዉ የሀገሪቱ ብሄራዊ የደህንነት ሕግ ላይ የተወሰኑ አንቀጾችን አወጣ። መንግሥት የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ በደስታ ተቀብሏል።
ከ2 ዓመት ገደማ በፊት የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት ያከበረው የቀድሞው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ፤ ያሁኑ የአፍሪቃ ሕብረት ፣ በቀጣይ 50 ዓመታት ፣ ማለትም እ ጎ አ እስከ 2063 ፣ ክፍለ ዓለሙ አንድነቱን አጠናክሮ ፣ በኤኮኖሚ ዳብሮ ፤
የዶቸ ቨለ የዘንድሮው ሐሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ሽልማት ፤ በእሥራት ላይ ለሚገኘው ለስዑዲ ዐረቢያው የድረ ገጽ ዐምደኛ ለራይፍ ባዳዊ ተሰጠ።
የዶቸ ቨለ የዘንድሮው ሐሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ሽልማት ፤ በእሥራት ላይ ለሚገኘው ለስዑዲ ዐረቢያው የድረ ገጽ ዐምደኛ ለራይፍ ባዳዊ ተሰጠ።
በየዓመቱ እጅግ በርካታ የፕላስቲክ ቆሻሻ ባህር ላይ ይጣላል። በጎርጎሪዮሳዊዉ 2010ዓ,ም ብቻ ከ4,8 እስከ 12,7 ሚሊዮን ቶን ፕላስቲክ ዉቅያኖስ ዉስጥ ተጥሎ መገኘቱን የአዉስትራሊያና ዩናይትድ ስቴትስ ተመራማሪዎች መዝግበዉ ይፋ አድርገዋል።
ከCNN እስከ FOX የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ትላልቅ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሰሞኑን እየተቀባበሉ ያራገቡት አዲሱ የአሸባብ ዛቻ-ሚኒሶታን ናይሮቢ-ሞል ኦፍ አሜሪካን-ዌስት ጌት ያደርጋቸዋል የሚል ሥጋት አሳዳሯል።የሥልታዊ እና የዓለም አቀፍ ጥናት ማዕከል ተመራማሪ ሪቻርድ ዶዉኔ ግን ዛቻዉ አያሰጋቸዉም
ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ አመት የሜድትራኒያን ባህርን በጀልባ ለማቋረጥ ከሞከሩ 218,000 ሰዎች መካከል 3,500 መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን አስታውቋል። በዚህ በተመሳሳይ መንገድ ወደ አውሮጳ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃ በመጨመር ላይ ነው።
ካለፉት 14 ወራት ወዲህ የርስበርስ ጦርነት የቀጠለባት የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ትናንት አዲስ አበባ ላይ እንደገና ተጀመረ።
በዩክሬን ዋና ከተማ ክየቭ በሜይደን የነፃነት አደባባይ ከ1 ዓመት በፊት ለተቃውሞ ሰልፍ ወጥተው የተገደሉት ሰዎች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ታስበዋል ።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አባ ብርሃነ የሱስ ፤ ከሁለት ወራት ገደማ በፊት ከሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንስስ ፣ የካርዲናልነት ማዕረግ ማግኘታቸው የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያውያን ድል እየተደጋገመ ነው። በወንድም በሴትም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ በመሆን በጃፓን የተኪያሄደውን የቶኪዮ ማራቶን ተቆጣጥረውታል። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ የእግር ኳስ ፍልሚያ ትናንት ሊቨርፑል ሳውዝሐምፕተን ላይ ድል በመቀዳጀት ወደ ዋነኞቹ ተፎካካሪዎች ተርታ ተጠግቷል።
ከጊዜ ወደጊዜ ዕድገት እያሳየ እንደመጣ የሚነገርለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ፣ ሁለት አዳዲስ የአይሮፕላን ጭነት (ካርጎ) ማከማቻ ሕንጻዎችን መገንባት መጀመሩ ተገለጠ።
የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በምስራቅ አፍሪቃ ለአራት ቀናት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀቁ። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ጀርመናውያን ስለ አፍሪቃ ያላቸው አመለካከት መለወጥ አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
የሕዝቧን መሠረታዊ ፍላጎት አሟልታ በማኖር ከአፍሪቃ አቻ ያልነበራት ሐገር ዛሬ የአሸባሪዎች፤የጎጠኞች፤ የሽፍቶች፤የስደተኛ አስተላላፊዎች፤ የዘራፊዎች መናኸሪያ ሆናለች።ከአራት ዓመት በፊት አንድ መሪ ነበራት።ዛሬ አስራ-ሰባት ሺሕ መሪዎች የሚያዙት አስራ-ሰባት ሺሕ ታጣቂ ቡድናት ይርመሰመሱባታል።
አዲስ አበባ ውስጥ ፣ በአዲስ ከተማ ፤ ወረዳ 5 ፣ መርካቶ አካባቢ ለመወዳደር ተመዝግበው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅኔር ይልቃል ጌትነት፤ በምርጫ ቦርድ ደንብ ከአጩነት መሠረዛቸው ተነገረ።
የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በምስራቅ አፍሪቃ ለአራት ቀናት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀቁ። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ጀርመናውያን ስለ አፍሪቃ ያላቸው አመለካከት መለወጥ አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በጤፍ መገኛነቷ ብቻ ሳይሆን እንደ እህል ለምግብነት በመጠቀሟም የምትጠቀስ ብቸኛ ቀዳሚ ሀገር ናት። ጤፍን ከተራ የዱር ተክልነት ወደምግብነት በመለወጥ የኢትዮጵያ ገበሬ ግንባር ቀደም ተጠቃሚ መሆኑን የእጸዋት እና እህል ዘር ተመራማሪዎች ያረጋገጡት እዉነት ነዉ።
የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር፣ ምንም እንኳን እልባት ላልተገኘለት የዩክሬይን ቀውስ መፍትሔ በማፈላለጉ ጥረት ቢጠመዱም፣ በማዕከላይ እና በምሥራቅ አፍሪቃ የአራት ቀናት ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የአፍሪቃ ጉብኝታቸውን ቀጥለው ዛሬ ወደ ሩዋንዳ አቅንተዋል። ሚንሥትሩ ከሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ዛሬ በመዲናዪቱ ኪጋሊ ተገኝተው ንግግር አሠምተዋል።
ባለፈው ቅዳሜ በአንዳንድ ፍቅረኛሞች ዘንድ የፍቅረኛሞች ቀን ወይም «ቫለንታይንስ ደይ» ተከብሎ ውሏል። በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ፤የሎው ሙቭመንት በሚል የተሰባሰቡ ወጣቶች ይህንን ቀን፤ ከፆታዊ ፍቅር መግለፃ ቀን ባሻገር፤ ሰዎች ለተቸገሩ በጎ ነገር የሚያደርጉበትም ቀን ሆኖ እንዲውል ወስኖ ተንቀሳቅሷል።
ከመካከለኛው ምሥራቅ እስከ አፍሪቃው ቀንድ አልፎም እስከ ምዕራብ አፍሪቃ ፤ IS ፤ አሸባብና ቦኮ ሃራምን በመሳሰሉ ጽንፈኛ ታጣቂ ኃይሎች በመዛመት ላይ ላለው አካራሪ አመለካከት ምን ዓይነት የጋራ መፍትኄ እንደሚያሻ ለመምከር ፤ የዩናይትድ ስቴትስ
ሰማያዊ ፓርቲ ፤ ከ 200 በላይ የተመዘገቡ የፓርቲው እጩ ተወዳዳሪዎ ች፣ በምርጫ አስፈጻሚዎች ተሰርዘውብኛል ሲል ማማረሩን ፣ ዮሐንስ ገብረአግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ያስረዳል። የምርጫ ቦርድ ምላሽ፤ ሰማያዊ ፓርቲ ፤ ምርቻ ቦርድ እውቅና ባልሰጠው
ናይጄሪያ በቦኮ ሃራም ታጣቂ ቡድን ጠንካራ ይዞታ በተባሉ አካባቢዎች ላይ የአውሮፕላን ድብደባ እየፈጸመች ነው። በተመሳሳይ ከትናንት በስተያ በአውሮፕላን ጥቃት ለናይጀሪያ በሚጎራበተዉ የኒጀር ግዛት በቀብር ስርዓት ላይ ከነበሩ ሰዎች በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
የደቡብ ሱዳን አማጺ ቃል አቀባይ ጄኔራል ሉል ሯይ ኩአንግ ከሪየክ ማቻር አፈነገጡ። ቃል አቀባዩ በደቡብ ሱዳን የኑዌር መንግስት የማቋቋም ሃሳብ አላቸው ተብሏል። ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በበኩላቸው የስልጣን ዘመናቸውን ለሁለት ተጨማሪ ዓመታት የማራዘም ሃሳብ ይዘው ብቅ ብለዋል።
ምንም እንኳን ለኢቦላ ተብሎ በተለይ የተሰራ መድኃኒት ባይኖርም በሽታው በቶሎ ህክምና ካገኘ የኅመምተኛው ሕይወት የመትረፍ ዕድል ከፍተኛ ነው።
ግሪክ ያቀረበችው ጥያቄ የዩሮ ተጠቃሚ አባል ሃገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች ነገ በሚያደርጉት ስብሰባ ውሳኔ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
አረና ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ከ100 በላይ እጩዎቹ ቢመዘገቡም በተለያዩ አካባቢዎች በደረሰባቸው ጫና ምክንያት በርካቶች ከውድድር መውጣታቸውን ፓርቲው አመልክቷል። የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት ሳይቀሩ ካርድ የለም ተብለው እንዲመለሱ መደረጉን የፓርቲው የሕዝብ ግኑኙነት ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
በዚሁ ዓለም ዓቀፍ ትርዒት ላይ ከ100 ሃገራት የመጡ ልዩ ልዩ ድርጅቶች ተሳትፈዋል ። በዚሁ የቤት እቃዎችና የጌጣጌጦችና ቅርጻ ቅርጾች ትርዒቱ ላይ 7 የአፍሪቃ ሃገሮች ቢሳተፉም ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ በትርዒቱ ላይ የተወከሉ ድርጅቶች እንዳልነበሩ