የካቲት 7 ቀን 2007 በናይጄሪያ ሊካሄድ የታቀደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በስድስት ሳምንታት እንዲራዘም የሃገሪቱ ነጻ የምርጫ ኮሚሽን( Independent National Electoral Commission) ያሳለፈው ውሳኔ ከፍተኛ ትችት ገጥሞታል። የሃገሪቱ ጦር ሰራዊት በናይጄሪያ የዴሞክራሲ የስርዓት ግንባታ ጣልቃ እየገባ ነው የሚል ስጋት አይሏል።

የአውሮጳ ህብረት እና ዩኤስ አሜሪካ በመካከላቸው ሊያቋቁሙት ያሰቡትን ነፃ የንግድ ቀጠናን የተመለከተውን ስምንተኛውን የድርድር ዙር በዚህ ሳምንት በብራስልስ በዝግ ስብሰባ አካሄዱ።

በኢትዮጵያ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ የድህነት መጠን መቀነሱን የዓለም ባንክ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል። ባንኩ ባወጣው ዘገባ ፣ ፈጣን የኤኮኖሚ እድገት በማሳየት ላይ ባለችው ኢትዮጵያ ድህነት በ30% ነው የቀነሰው። ያም ቢሆን ግን፣ አንድ ሦስተኛው የሀገሪቱ ሕዝብ አሁንም በከፋ ድህነት ውስጥ እንደሚገኝ እና ወደ ድህነት አዘቅት

ባንድ ወቅት የጦር አምባገነን ነበሩ። አሁን የናይጀሪያ ፕሬዚደንት ሆነው ለመመረጥ ይፈልጋሉ። የጠቅላላ ተራማጆች ኮንግረስ ፓርቲ ዕጩ ሙሀማዱ ቡሀሪ በፕሬዚደንት ጉድላክ ጆናታን አንፃር ለፕሬዚደንታዊው ምርጫ የቀረቡ፣ ደህና ዕድል አላቸው የሚባሉ፣ በተለይ በብዛት ሙሥሊሞች የሚኖሩበት የሰሜናዊ ናይጀሪያ ሰፊ ድጋፍ ያላቸው ጠንካራ ተፎካካሪ ናቸው።

በዛሬው ዕለት በደቡብ ጀርመን ርእሰ ከተማ ሙዑንሸን(ሙዩኒክ) ለተከፈተው ጉባዔ መላው ዓለም ዐቢይ ግምት ሰጥቶታል። ለዚህም በቂና አንገብጋቢ ምክንያት አለው። ጸጥታ ተመልካቹ ጉባዔ ፣ ለዋና ዋና አወዛጋቢ ጉዳዮች ፣ በስብሰባው ወቅት ፥ አለያም ከዚያ

የጀርመንና የፈረንሳይ መሪዎች በበኩላቸዉ አዲስ የነደፉትን የሠላም ዕቅድ ለዩክሬንና ለሩሲያ መሪዎች ለማስረዳት ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ላይ ናቸዉ።አንዳድ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ባንፃሩ በምሥራቃዊ ዩክሬኑ ጦርነት ሽንፈት የገጠመዉን የኪየቭን መንግሥት ከዉድቀት ለማዳን ማስታጠቅ አለብን ይላሉ

ሁላችንም ከልጅነት አንስቶ የምናስታውሳቸው ፤ አስቂኝ፤ አሳዛኝ ወይም አስገራሚ ገጠመኞች አሉን። እነዚህን ታሪኮች ግን ስንቶቻችን ዋጋ ሰጥተን፤ በቃላት አስውበን ወረቀት ላይ እናሰፍራቸዋለን። ከትምህርት ቤት ዘመኔ አንስቶ መፃፍ ያስደስተኝ ነበር የምትለው ሕይወት እምሻው፤ በትርፍ ጊዜዋ አጫጭር ታሪኮች እየፃፈች የብዙዎችን ትውስታ ቀስቅሳለች።

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ከተቋቋመ አንስቶ በተለያዩ ሃገራት የፈጸሙ የዘር ማጥፋትና ሌሎች ከባድ ወንጀሎችን በመከታተል አጥፊዎች በነፃ መንቀሳቀሳቸዉ እንዲያከትም ለማድረግ በመሥራት ላይ ይገኛል።

ኢኳቶሪያል ጊኒ ዉስጥ በመካሄድ ላይ ያለዉ የአፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ ከወትሮዉ በተለየ ትናንት የበርካታ ተመልካቾችን ትኩረት ስቦ ነበር። በትናንቱ ጨዋታ ጋና ተፎካካሪዉ የነበረችዉን የአስተናጋጅዋን ሀገር የኢኳቶሪያል ጊኒን ቡድን ሶስት ለዜሮ ሊሸኝ ሲቃረብ ደጋፊዎች ግርግር ቢፈጥሩም ጨዋታሽ መልኩን ለዉጦታል።

ዮርዳኖሳውያን፣ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ማታ ፤ ራሱን «እስላማዊ መንግሥት » ያለው አሸባሪ ቡድን የጭካኔ ተግባሩ እስከምን ድረስ እንደሆነ ባዩት ቪዲዮ ከጥልቅ ሐዘን ጋር ለመገንዘብ ችለዋል። የጦር አይሮፕላን አብራሪ፣ ሙዓስ ኧል ካሳባ፤ ባለፈው

ሥነ-ጥበብ የሕይወትን እውነታ መልሰን እንድንመለከት እና እድንመዝን የሚረዳን የጥበብ ዓይነት መሆኑን የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ። ስመጥር ከሆኑት ኢትዮጵያን ሰዓልያን መካከል ገብረ ክርስቶስ ደስታና፤ እስክንድር ቦጎስያን በጀርመን የሥነ-ጥበብ ክህሎትና ሥራቸዉ በሰፊዉ ይታወቃል።

የጀርመን ፕሬዝዳንት ዮአሂም ጋውክ የአምስት ቀናት የታንዛኒያ ጉብኝት ነገ ያበቃል ። የጉብኝታቸው ዋነኛ ዓላማ የረዥም ጊዜ ታሪክ ያለውን የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር ነው ። ጋውክ ከታንዛኒያ ባለሥልጣናት ጋር ከተወያዩባቸው ዐርዕስት ውስጥ የሁለቱ ሃገራት የኤኮኖሚ ግንኙነት ይገኝበታል ።

የጀርመን ወታደሮች የኤቦላ ተሐዋሲን መስፋፋት ለመግታት በሚካሄደዉ ዘመቻ ለመሳተፍ ወደዚያ ማቅናታቸዉን የሚደግፉ እንዳሉ ሁሉ ስኬት አልታየም በሚል የሚተቹም አልጠፉም። ለዚህ ተግባር ወደላይቤሪያ ዘምተዉ የተመለሱ ወገኖች ላይቤሪያ ዉስጥ የኤቦላ ወረርሽኝ እየቀነሰ መሄዱን ያመለክታሉ።

በእስር ላይ የሚገኙት ስድስት ጦማሪያንና ሶስት ጋዜጠኞች የሚዳኙት የመሃል ዳኛ በፈቃዳቸው ራሳቸውን አገለሉ።ተከሳሾቹ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ያቀረቡትን የዳኛው ይነሱልን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎት የነበረ ቢሆንም የመሀል ዳኛው አቶ ሸለመ በቀለ በፈቃደኝነት ራሳቸውን አግልለዋል።

የብሪታንያ ፤ የሕዝብ እንደራሴዎች ፣ ትናንት ከቀትር በኋላ ፣ በአዲስ የሥነ ተዋልዶ ሥነ ቴክኒክ በመታገዝ ፣ አንድ ሕጻን ከሦስት ግለሰቦች ፤ ማለትም ከእናትና አባት ሌላ የአንዲት ሌላ ሴት ዘረ መል እንዲወርስ ማድረግ የሚቻልበትን ሁኔታ ፤ በድምፅ ብልጫ ፤ በሕግ መምሪያው ም/ቤት

ከአማን ዉሎዉን የተሰማዉ ግን የዚያች ሐገር ሕዝብ ለሁለት መከፈሉን ጠቋሚ ነዉ።ገሚሱ እንደ ገዢዎቹ ሁሉ ሶሪያና ኢራቅ የመሸጉትን አማፂያን መዉጋት አለብን ይላል።ሌላዉ ደግሞ ምን አግብቶን

የስፖርቱ ድግስ ግን አልተጓደለም።በየስታዲዮሙ ይዘምራል፤ይዘፍናል፤ ይጨፈራል፤ይደነሳል።-ተመልካች።ተጫዋቹም፤ የኮትዲቫሩ ያያ ቶሬ እንደሚለዉ ለየብሔራዊ ክብሩ ይፋለማል-በኳስ ሥለ ኳስ።

ርዕሠ-ከተማ ሠነዓን ጨምሮ አብዛኛ ሐገሪቱን የሚቆጣጠሩት የሁቲ አማፂያን፤ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የሽግግር መንግሥት እንዲመሠረቱ የሠጡት የሠወስት ቀን ቀነ-ገደብ ነገ ማምሻዉን ያበቃል።

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሃይሎች ትናንት አዲስ አበባ ላይ አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራረሙ መባሉ ይታወሳል።ካሁን ቀደም ሶስት ተመሳሳይ ስምምነቶችን ፈርመው ተግባራዊ ማድረግ ያልቻሉት ሳልቫ ኪር እና ሪየክ ማቻር ወደ ጦርነት ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዛሬ ዘግቧል።

የቀድሞው የጀርመን ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ፎን ቫይሴከር ባለፈው ቅዳሜ አርፈዋል ። ለ10 ዓመታት የጀርመን ፕሬዝዳንት የነበሩት የፎን ቫይሴከር ማንነት የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

በሕፃንነት ተገቢዉን ክትባት ማግኘት አስቀድሞ በመከተብ ለመከላከል ከሚቻሉ በሽታዎች፣ የአካል ጉዳት እንዲሁም ሞት ለመዳን እንደሚረዳ ይታመናል። ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት በሚሰጠዉ ክትባት የስድት ሚሊዮን ሕፃናትን ሕይወት ማትረፍ ተችሏል።

በአፍሪቃ ዋንጫ ጨዋታዎች ጋና፣ ኮትዲቯር፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ለግማሽ ፍፃሜ ደርሰዋል። አስተናጋጇ ያለፈችበት ጨዋታ ዳኝነት ውዝግብ አስነስቷል። ቡንደስ ሊጋው ጀምሯል፤ አስገራሚ ውጤቶች ተከስተዋል። የጀርመኑ ኃያል ባየር ሙንሽን በዎልፍስቡርግ የ4 ለ1 ከባድ ሽንፈት ቀምሷል። ተጨዋቾቹ አንዳች ብራቅ ወረደብን ብለዋል።

የ 90 ዓመቱን የዝምባባዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤን ፤ የወቅቱ ፣ የሕብረቱ ፕሬዚዳንት ይሆኑ ዘንድ የመረጠው የዘንድሮው የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ፤ የተለያዩ ጉዳዮችን አንስቶ በመከረበት ወቅት በአንዳንድ ዐበይት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።

በሰሜናዊ ናይጄሪያ የሚንቀሳቀሰው እስላማዊ ቡድን ቦኮ ሃራም የማይዱግሪ ከተማን ለመቆጣጠር ለሁለተኛ ጊዜ የከፈተው ጥቃት አልተሳካም። በዚህ ወር በሚካሄደው የናይጄሪያ ምርጫ ላይ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል የሚል ስጋት በማየሉ የቀጠናው ሃገራት ወታደራዊ እርምጃ ጀምረዋል።

አምባገነን፤ ወታደራዊ፤ ሶሻሊስታዊ፤ ጦረኛ እየተባለ የሚወገዝ፤የሚወቀስ፤ የሚተቸዉ የደርግ ሥርዓት ከተወገደ ሃያ-አራት ዓመት ሊደፍን እነሆ ወራት ቀሩት።ያኔ የነበረዉ ተስፋ ወይም ቃል የተገባዉ የመድብለ ፓርቲ፤ የዴሞክራሲ፤ የፍትሐዊ ሥርዓት ግንባታ፤ እዚሕ ደርሷል።ከእንግዲሕስ?

24ኛው የአፍሪቃ የመሪዎች ጉባኤ ትናንት በአዲስ አበባ ከተማ ተጠናቋል። ጉባኤውን በቦታው ተገኝቶ ሲከታተል የነበረው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊ የጉባኤውን ማጠቃለያ አስመልክቶ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

የምርጫዉ ዝግጅት እና ሒደቱ በሚያነጋግርበት፤ ፓርቲዎችንና ምርጫ ቦርድን በሚያወዛግብበት መሐል ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ሑዩማን ራይትስ ዋች ባወጣዉ ዘገባ የኢትዮጵያ መንግሥት በነፃ መገናኛ ዘዴዎችና በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርሰዉ ጫና እና በደል እየባሰ መምጣቱን በዝርዝ ዘግቧል

24ተኛው የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለክፍለ ዓለሙ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ዓርብ ቅዳሜ ጥር 22 ቀን 2007 ዓ. ም.አዲስ አበባ ውስጥ ጀምሮ ዛሬ ተጠናቋል። በጉባኤው ኢቦላ፣ ቦኮ ሃራም፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳንን የተመለከቱና ሌሎች ጉዳዮች ተነስተዋል።

የኤቦላ ወረርሽኝ በምዕራብ አፍሪቃ ባለፈው መጋቢት ወር ከተከሰተ በኋላ በወረርሽኙ አስተላላፊ ተኀዋሲ የሚያዘው ሰው ቁጥር ከሰኔ 2014 ዓም ወዲህ አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ መቀነሱን የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት አስታወቀ። ዓለም አቀፉ ድርጅት ባወጣው ዘገባ መሠረት፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ በተኀዋሲው ይያዝ የነበረው ሰው ብዛት ወደ 100 ወርዶዋል።

በአዲስ አበባ 11 ሰዎች መጫን የሚችሉ ከ10,000 በላይ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡና በተለምዶ ‘ሚኒ-ባስ’ ተብለው የሚጠሩ መኪናዎች መኖራቸውን በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰሩ ጥናታዊ ጽሁፎች ይጠቁማሉ።

የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ንኮሳዛና ድላማኒ ዙማ ባሰሙት ንግግር ከናይጀሪያ አልፎ ወደ አካባቢው አገራትም እየተስፋፋ በመጣው በቦኮሃራም ላይ የጋራ ውጤታማና ወሳኝ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የተመድ የሰብዓዊ መብት ተመልካች ኮሚሽን ቡድን የኤርትራ መንግሥት በዜጎቹ ላይ ይፈፅመዋል የሚባለውን የመብት ጥሰት ለማጣራት በብሪታንያ ምርመራ ጀመረ። ቡድኑ ሁለተኛ ሳምንት የያዘውን ምርመራውን በብሪታንያ የሚኖሩ ኤርትራውያንን በማነጋገር በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ከ 2 ቀናት በፊት ፣ አያሌ መገናኛ ብዙኀን በሰፊው ያወሱት ርእሰ ጉዳይ ቢኖር ፤ ከ 70 ዓመት በፊት በዛሬዋ ፖላንድ የምትገኘው አውሽቪትዝ የተባለችው ፣የህዝብ ማጎሪያና፣ ሰው በሰው ላይ በዓለም ታሪክ ታይቶ ያልታወቀ ግፍ የሠራባት ቦታ ነጻ

በናይጀሪያ አጠቃላይ ምርጫ ሊጀመር ሶስት ሳምንታት ገደማ በቀሩት ባሁኑ ጊዜ የአውሮጳ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን አባላት ወደ ናይጀሪያ እንደሚልክ አስታውቋል፣ ይሁንና፣ ታዛቢዎቹ የፀጥታ ችግር ወደሚታይበት ሰሜናዊ የሀገሪቱ ከፊል እንደማይሠማሩ የታዛቢው ቡድን መሪ ሳንቲያጎ ፊሳስ ገልጸዋል።