ፍልሰትና ስደት፥ ሽብርና አክራሪነት በአውሮጳ
በአውሮጳ ታላላቅ ከተሞች ማለትም በፓሪስ እና ኮፐንሐገን የሽብር ጥቃቶች ከተሰነዘቱ በኋላ የአውሮጳ ኅብረት የደኅንነት ስጋት ገብቶታል። የኅብረቱ የሀገር ውስጥ እና የፍትኅ ሚንስትሮች ባሳለፍነው ሳምንት አሸባሪነትን ለመዋጋት
በአውሮጳ ታላላቅ ከተሞች ማለትም በፓሪስ እና ኮፐንሐገን የሽብር ጥቃቶች ከተሰነዘቱ በኋላ የአውሮጳ ኅብረት የደኅንነት ስጋት ገብቶታል። የኅብረቱ የሀገር ውስጥ እና የፍትኅ ሚንስትሮች ባሳለፍነው ሳምንት አሸባሪነትን ለመዋጋት
በፊንጫ ስኳር ማምረቻ በደረሰው የእሳት አደጋ አንድ ሠራተኛ እሳቱን ለማጥፋት ባደረገው ሙከራ ሕይወቱ መጥፋቱ ተገለጠ። ሌሎች ሠራተኞችም በደረሰባቸው አደጋ በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ተጠቅሷል።
የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ተፈጥሮን ለማድነቅ፤ በሌሎች አካባቢ የማይገኙ አዕዋፍና የዱር እንስሳትን ለመመልከትና ተራሮችን የመዉጣት ፍቅር ያላቸዉን ቱሪስቶች በመሳብ ይታወቃል። በበጋ ወራት በተለያዩ አካባቢዎች የእሳት ቃጠሎ እየተነሳ ጉዳት ማድረሱ ይደጋገማል። በንብረትና በተፈጥሮ ሀብት ላይም ቀላል የማይባል ችግር ሲያስከትል ይሰተዋላል።
10 ዙር መድረክ ላይ ሲፋለም የቆየ አውስትራሊያዊ ወጣት ቡጢኛ ለሁለት ቀናት ራሱን ስቶ ከቆየ በኋላ ዛሬ ሕይወቱ ማለፉ ተነግሯል። የአርሰናሉ አማካይ ጌዲዮን ዘላለምን በቀጥታ ወደ ብሔራዊ ቡድኔ ማካተት እሻለሁ ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝ ተናግረዋል። በቅድሚያ ግን ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል፤ ከማን?
120 መቀመጫዎች ላሉት እና ‘ክነሰት’ በመባል ለሚታወቀው የእስራኤል ምክር ቤት ነገ ምርጫ ይካሄዳል።በምርጫው 26 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሳተፋሉ። ለረጅም አመታት ስልጣን ላይ የቆዩት ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከስልጣንና ከፓርቲ ካባረሯቸው ዚፒ ሊቭኒ እና ከኢዝሃቅ ሄርዞግ ጠንካራ ፉክክር ገጥሟቸዋል።
የዩኤስ አሜሪካ አብራሪ አልባ አውሮፕላኖች በኬንያ የዌስት ጌት የገበያ ማዕከል ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አቀነባብሯል ባሉት የአሸባብ አመራር ላይ ጥቃት ፈጸሙ። በጥቃቱ የአሸባቡ መሪ መሞቱን የዜና ወኪሎች ቢዘግቡም: ዜናው እስካሁን በይፋ አልተረጋገጠም።
ወደ ስዊድን የሚሄደው የስደተኛው ቁጥር ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በጣም መጨመሩን የሀገሪቱ የስታትስቲክስ መስሪያ ቤት ያወጣው መዘርዝር አሳየ።
መጋቢት ስድስት ቀን 1957 ዓም! (እአአ ፣ 1965 ዓም) በዓለም ታሪክ በፖለቲካው በኤኮኖሚውና በማሕበራዊ ኑሮ የማይረሱ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዘመን! በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት፣ ኃያላኑ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ሶቭየት ሕብረት፣ በዓለም ዙሪያ ተጽዕኖአቸውን ለማስፋፋት በግልጽም፤ በሥውርም ይዘምቱ የነበረበት ጊዜ ነው፣ 1965 ።
መጋቢት ስድስት ቀን 1957 ዓም! (እአአ ፣ 1965 ዓም) በዓለም ታሪክ በፖለቲካው በኤኮኖሚውና በማሕበራዊ ኑሮ የማይረሱ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዘመን! በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት፣ ኃያላኑ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ሶቭየት ሕብረት፣ በዓለም ዙሪያ ተጽዕኖአቸውን ለማስፋፋት በግልጽም፤ በሥውርም ይዘምቱ የነበረበት ጊዜ ነው፣ 1965 ።
ደቡብ አፍሪቃ በሕጋዊ እና ሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገሯ የሚገቡ የውጭ ዜጎች ቁጥር ለመቀነስ በማሰብ ባለፈው ዓመት አንድ ጠንካራ ሕግ አውጥታለች። ከብዙ ወራት ወዲህ የተጀመረው ሕጉን ተግባራዊ የማድረጉ ሂደት ግን ብዙ ቀውስ የታየበት እና በቱሪዝም እና ከውጭ በሚገባ ወረት ላይ አሉታዊ መዘዝ አስከትሏል።
ሠላማዊ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘው የቫኑዋቱ ደሴት «ፓም» በተሰኘ ዝናብ በቀላቀለ ከባድ አውሎ ንፋስ ተናወጠች። በዚህ ክስተት ደሴቲቱ ከባድ አደጋ ደርሶባታል።
የሳዑዲ መሪዎች የስቶክሆልምን እርምጃ ለመበቀል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሯ በአረብ ሊግ ጉባኤ ላይ ንግግር እንዳያሰሙ ሲያግዱ፤ በስቶኮሆልም የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደርንም ወደ ሐገራቸዉ ጠርተዋል።
የመድረክ ባለሥልጣናት ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት አባላቶቻቸዉን የሚያስሩ፤ የሚደበድቡና የሚያንገላቱት የየአካባቢዉ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ፖሊሶች ናቸዉ።
ቡሩንዲ አጠቃላይ ምርጫ ልታካሂድ ጥቂት ወራት ቀር ቷት ሳለ ፣ ከወዲሁ ፍርሃት የነገሠ መስሏል። ፕሬዚዳንት ፒዬር እንኩሩንዚዛን የሚተቹ በየጊዜው የግድያ ዛቻ እንደሚሰነዘርባቸው ይነገራል።
የሁለቱ ድርጅቶች ተወካዮች በተለይ በደቡብ ሱዳን ላይ ሥለተጣለዉ ማዕቀብ ገቢራዊነትና ቦኮ ሐራምን በጋራ የሚወጉበትን ዕቅድ ትኩረት ሰጥተዉት ነበር።
የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኞችን ለመከታተል የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራሞችን መቀጠም መቀጠሉን አንድ ጥናት አመለከተ።
የአዉሮጳ ኅብረት የሀገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሁለት ቀን ጉባኤ የኅብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችዉ ብራስልስ ጀምረዋል። ሚኒስትሮቹ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስጋትነቱ እየተጠናከረ በመጣዉ በሽብር እንቅስቃሴና በሕገወጥ ወደአዉሮጳ ስለሚገቡ ስደተኞች ጉዳይ እንደሚነጋገገሩ ይጠበቃል።
ከ 20 ዓመት በፊት በሥነ-ጥበቡ መድረክ ማበብ የጀመረዉ የዝያን ግዜዉ እንቡጥ ሰዓሊ እንግዳጌጥ ለገሰ በአሁኑ ወቅት አሉ ከሚባሉት ታዋቂ ኢትዮጵያዉያን ሰዓሊዎች ይመደባል ይላል፤ መቀመጫዉን በርሊን ላይ ያደረገዉ ሰዓሊዎችንና ስራቸዉን የሚያስተዋዉቀዉ የመገናኛ መረብ።
ፓርቲዉ በምርጫዉ ለመሳተፍ አጩዎቹን ሰይሞ፤የመወዳደሪያ አላማዎቹን ለይቶ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ነበር።በዚሕ መሐል ነዉ ፓርቲዉ በአቶ ግርማ ቋንቋ «ለመወዳደር አይደለም ዉድድር ለመመልከት እንኳን ያልተዘጋጁ» ላሏቸዉ ሰዎች የተሰጠዉ።
አሸባብ በጣም መዳካሙን የሶማሊያ መንግሥትና ደጋፊዎቹ መናገር ከጀመሩ ከሁለት ዓመት በላይ ተቆጠረ።ሶማሊያ ግን የአክራሪዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ጥቃት ተለይቷት አያዉቅም።ሆቴሎች፤ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፅሕፈት ቤቶች፤ አብያተ-መንግሥታት፤ መስሪያ ቤቶች፤ የጦር ሠፈሮች፤ አዉሮፕላን ማረፊያዎች፤ የመሰብሰቢያ አዳራሾች ሁሉም ይጠቃሉ፤ ሁሌም ይሸበራሉ።
ከ 20 ዓመት በፊት በሥነ-ጥበቡ መድረክ ማበብ የጀመረዉ የዝያን ግዜዉ እንቡጥ ሰዓሊ እንግዳጌጥ ለገሰ በአሁኑ ወቅት አሉ ከሚባሉት ታዋቂ ኢትዮጵያዉያን ሰዓሊዎች ይመደባል ይላል፤ መቀመጫዉን በርሊን ላይ ያደረገዉ ሰዓሊዎችንና ስራቸዉን የሚያስተዋዉቀዉ የመገናኛ መረብ።
ባለፈው ሳምንት፣ በዛሬዋ ዕለት ነበረ፣ የሳይንሱ ዓለም ፣ በተለይም የጥንታዊው ሰውም ሆነ ቅድመ ሰው ቅሪተ አካል ተመራማሪዎች ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ 2,8 ሚሊዮን ዓመት ገደማ ዕድሜ ያለው መንገጭላ ከ 5 ጥርስ ጋር መገኘቱን በይፋ በማሳወቅ ደስታቸውን
በማሊ ዋና ከተማ ባማኮ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ የደረሰዉ ጥቃት በሀገሪቱ መንግሥትና በቱአሬግ አማፅያን መካከል የተጀመረዉን የሰላም ድርድር ለማደናቀፍ ያለመ ነዉ በማለት መንግሥትና ፈረንሳይ አዉግዘዋል። በጥቃቱ አንድ የቤልጅና አንድ የፈረንሳይ ዜጎችን ጨምሮ አምስት ሰዎች ተገድለዋል።
የዮርዳኖስ ንጉሥ ዳግማዊ አብዱላኽ ፣ በሽትራስቡርግ ከተማ በመገኘት ለአውሮፓ ፓርላማ ንግግር አሰምተዋል። ዮርዳኖስ፤ ራሱን IS ወይም ISIS እያለ የሚጠራውን አክራሪና አሸባሪ ቡድን ለመውጋት ፤ ከዓለም አቀፉ ጥምረት ጋር በመቀላቀል ድርሻዋን
ደብዳቢዉ ከአቶ ተማም ጋር አብሮ በነበሩና ባካባቢዉ ሰዎች ትብብር ተይዞ ሲጠየቅ የአዕምሮ በሽተኛ ይመስል የተለያዩ ፖለቲካዊ ርዕሶችን እያነሳ ይናገር እንደነበር የዓይን ምስክሮች አስታዉቀዋል።
የናይጄሪያው እስልምና አክራሪ ቡድን ቦኮ ሃራም በኢራቅና ሶሪያ እስላማዊ መንግሥት መሰረትኩ ላለው አይ.ኤስ. (IS) ታጣቂ ቡድን ታማኝነቱን መግለጹ የፖለቲካ ተንታኞችን ትኩረት ስቧል።
የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከትናንት በስተያ ታስቦ ዉሏል። ላለፉት በርካታ አስርት ዓመታት በመላዉ ዓለም የሴቶችን መሠረታዊ መብቶች ለማስከበር የተደረጉ ጥረቶች ቢኖሩም አሁንም እጅግ ረዥም ጉዞ እንደሚቀር የተመድ ዋና ጸሐፊ ያመለከቱት። ዘንድሮ የሴቶች ቀን ሲታሰብም የተመረጠዉ መሪ ቃል «እዉን አድርጉት» የሚል ነዉ።
በሩስያና በአዉሮጳ ሕብረት መካከል ዉጥረት ባለበት በአሁኑ ወቅት የአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዣን ክሎድ ዩንከር፣ አዉሮጳ አቀፍ ጦር ሠራዊት እንዲቋቋም ሐሳብ ማቅረባቸው በአዉሮጳ ሃገራት ፖለቲከኞች ዘንድ ከፍተኛ ዉይይትን ቀስቅሶአል።
የባርሴሎናው ሊዮኔል ሜሲ ዳግም ሐትርቲክ በመስራት በላሊጋው ያስቆጠረው ግብ ከሪያል ማድሪዱ ክሪስትያኖ ሮናልዶ ተስተካክሏል። የስፔኑ ኃያሉ ሪያል ማድሪድ አሠልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ሜዳ ውስጥ በደጋፊያቸው ዘለፋ እና ጩኸት ገጥሟቸዋል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ትናንት ፓሪስ ከተማ ውስጥ ፍፁም የበላይነታቸውን አስመስክረዋል።
የዓለምና የአካባቢዉ ሐያላን ላለፉት አስራ-ሁለት ዓመታት የበላይነትን ለማረጋገጥ የገጠሙት ሽኩቻ ሱኒ ኩርዶችን ከሱኒ አረቦች፤ ሱኒ አረቦችን፤ ከሺዓ-አረቦች፤ ሱኒ ኩርድ፤ ሱኒ አረቦችን ከሺዓ ፋርሶች ጋር ደም አቃብቷል።ሽኩቻዉ አሁን መናሩ ደግሞ አISIS ቢጠፋ እንኳን የጦርነቱ ዑደት ፍፃሜ አለመሆን እንዳይጠቁም ማስጋቱ ይቀርም
ላይቤሪያ ከገዳዩ የኢቦላ ተህዋሲ ነጻ የምትሆንበትን ቀን በጉጉት እየጠበቀች ነው። ባለፈው ሳምንት የመጨረሻዋ የኢቦላ ህመምተኛ ከሆስፒታል ወጥተዋል።ላለፉት ሁለት ሳምንታት አዲስ የኢቦላ ህመምተኛ አለመገኘቱ ተሰምቷል።ባለፈው አመት በምዕራብ አፍሪቃ የተከሰተው የኢቦላ ተህዋሲ ወረርሽኝ ከሶስት ሺ በላይ ላይቤሪያውያንን ለሞት ዳርጓል።
ሲኖትራክ የተባለ ገልባጭ የጭነት ተሽከርካሪ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰቅጣጭ አደጋን እያደረሰ ለነዋሪዉ ስጋት መሆኑ ተገለፀ።
በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያት በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ማርች ስምንት የሚታሰበውን የሴቶች ቀን ትናንት ለመጀመርያ ጊዜ አክብረዉት ዋሉ።
የክሬምሊን ቤተ-መንግሥት ተቺ ቦሪስ ኔምትሶቭን ሩስያ መዲና ሞስኮው ክሬምሊን ቤተመንግሥት አጠገብ በጥይት ገድለዋል ተብለው በጥርጣሬ ከተያዙት ኹለት ሰዎች መካከል አንደኛው ግድያውን መፈፀሙን አምኗል መባሉ ተዘገበ። ኹለቱ በግድያ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ከሌሎች ሦስት ተጠርጣሪዎች ጋር ሞስኮው በሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተጠቅሷል።
ምርጫዉን በበላይነት የሚመራዉና የሚያስተባብረዉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ አላማ አስፈፃሚ ነዉ ከሚለዉ ጀምሮ፤ ቦርዱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ይከፋፍላል፤ ከተከፋፈሉ ፖለቲከኞች ላንዱ ሕጋዊ ዕውቅና እየሰጠ ሌላዉን ይነፍጋል፤ የምርጫ ሕግን በመፃረር ዕጩዎችን በዕጣ እለያለሁ በሚል የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች በዉድድሩ እንዳይቀርቡ አግዷል።
በጣም ሆዴን አባብቶታል ከአድማጮቼ መለያየቴ» ። አድማጮቼ ችግራቸው ችግሬ ሆኖ ይሰማኛል ። የሚልኩት ደብዳቤ ማለት መልክት ሁሉ ፍቅር ያሳድርብኛል ።»
በጣም ሆዴን አባብቶታል ከአድማጮቼ መለያየቴ» ። አድማጮቼ ችግራቸው ችግሬ ሆኖ ይሰማኛል ። የሚልኩት ደብዳቤ ማለት መልክት ሁሉ ፍቅር ያሳድርብኛል ።»
በሞዛምቢክ ታዋቂው የመንግሥቱ ተቃዋሚ ፕሮፌሰር ዢል ሲስታክ ከጥቂት ቀናት በፊት የተገደሉበት ድርጊት ሰፊ ተቃውሞ ቀሰቀሰ። የተቃውሞ ወገኖች በሕገ መንግሥታዊው የሕግ ዘርፍ ላይ ያተኮሩት ፕሮፌሰር እና ጠበቃ ሲስታክን የገደሉት የገዢው ፓርቲ፣ «ፍሬሊሞ» አክራሪ ኃይላት ተጠያቂዎች ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ገልጸዋል። መንግሥት ይህን ወቀሳ አስተባብሏል።
የኡጋንዳ መንግሥት በመቶዎች የሚቆጠሩ የጤና ባለሞያዎችን ወደ ካረብያዋ ሃገር ትሬኔዳድና ቶቤጎ ሊልክ ማቀዱ እያወዛገበ ነው ። የጤና ባለሞያዎች እጥረት ካለባት ከኡጋንዳ እነዚህ ሙያተኞች ወደ ሌላ ሃገር ይሄዳሉ መባሉን መንግሥትን እያስተቸው ነው ። መንግሥት ግን ኡጋንዳ በዚህ ታተርፋለች እንጂ እትጎዳም ይላል ።
አብዛኛውን ጊዜ የውጭ ሀገር ዜጎች ስለ ኢትዮጲያ ሲናገሩ ፤ሀገሪቷን በበጎ ከሆነ ፤የጥንት ሰዎች ቅሪት መገኛ፣ የቆንጆዎች ሀገር፣ የመሳሰሉት ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ አሁን ድረስ የ1977ቱ አይነት ድርቅ እና ርሀብ ሀገር አድርገው ይቆጥሯታል ። እናንተስ ፤ ኢትዮጵያ በውጭ ዜጎች ዘንድ ምን አይነት ገፅታ አላት ትላላችሁ?
የቻይና ኤኮኖሚ ባለፉት ሁለት አሠርተ ዓመታት ባለሁለት አሀዝ እድገት በማስመዝገብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁለተኛዋ ናት። ይኸው 12,2% የነበረው የእድገት መጠን ግን በሚቀጥሉት ጊዚያት በጉልህ ሊቀንስ እንደሚችል የምጣኔ ሀብት ጠበብት ገምተዋል። ይህም በቻይና ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በዓለም ኤኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳርፍ እንደሚችል ጠበብት ጠቁመዋል።
የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች ከስምምነት እንዲደርሱ በአደራዳሪና ሸምጋዮች የተሰጣቸዉ የጊዜ ገደብ ዛሬ እኩለ ለሌሊት ከመሆኑ አስቀድሞ ያከትማል። ሆኖም እስካሁን ከአዲስ አበባ የሚወጡ ዘገባዎች ተደራዳሪዎቹ የተጠበቀዉ ስስምነት ላይ መድረሳቸዉን አያመለክቱም።
ከጠፋ አንድ ዓመት ሊሞላዉ ጥቂት ቀናት የቀረዉ የማሌዢያ አዉሮፕላን ጉዳይ ዛሬም እንዳነጋገረ ነዉ። በበረራ ታሪክ ለደረሰ አደጋ ከፍተኛ ወጪና ኃይል አሰባስቦ ከተከናወነ ፍለጋ በኋላ ያለ ዉጤት የተጠናቀቀበት የበረራ ቁጥር MH 370። አዉሮፕላኑ የጠፋበት ቀን ሲታሰብ ፈላጊዎቹ ለተሳፋሪዎቹ ቤተሰቦች የሚሰጡትን የመጨረሻ ቃል እየፈለጉ ነዉ።
«…የሃገሬ ሰዉ ፤ ከአሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም፤ አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም፤ አሁንም ጉልበት ያለህ በጉልበት እርዳኝ፤ ጉልበትም የሌለህ ለልጅህ ለሚስትህ ለሓይማኖትህ ስትል በሃዘን እርዳኝ።
የግብፅ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በካርቱም፣ ሱዳን በዐባይ ወንዝ ውሃ ክፍፍል እና ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ለሶስት ቀናት ያደረጉትን ዉይይት ዛሬ አጠናቀዋል። የውይይቱ ውጤት ገና በይፋ አልወጣም።
መንግሥታት በኢንተርኔት አማካይነት ከዜጎቻቸዉጋር የሚደረግ ግንኙነት E-Government በመባል ይታወቃል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ክፍል ባደረገዉ ጥናት መሰረት ደቡብ ኮሪያ፤አውስትራሊያ፤ሲንጋፖር እና ፈረንሳይ ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ቀዳሚዉን ሥፍራ ይይዛሉ።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት እና የዓማፅያኑ መሪ ሪየክ ማቸር በምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ሸምጋይነት ትናንት እንደገና በአዲስ አበባ የጀመሩትን የሰላም ድርድር ዛሬም ቀጥለው ዋሉ። ደቡብ ሱዳን ከታህሳስ ፣ 2013 ዓም ወዲህ
የቱኒዚያ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የድረገጽ ጸሐፊ በሆነዉ ቱኒዚያዊ ያሲን አያሪ ላይ የጦሩን ስም በማጥፋት ወንጀል እስራት ፈረደ። ያሲን የተከሰሰዉ የሀገሪቱ የጦር ኃይል መኮንኖች እና የመከላከያ ባለስልጣናት የሚፈፅሙትን የገንዘብ ብክነት አስመልክቶ ከሀገሩ ዉጭ ሆኖ በድረገጽ በመጻፉ ነዉ።
በምዕራብ አፍሪቃ የተከሰተውን የኤቦላ ስርጭት ለማብቃት የተደረገውን ዘመቻ ለመገምገም ትናንት በብራስልስ የተጠራው ዓለም ስብሰባ በበሽታው የተጎዱት ሀገራት ውስጥ የተኀዋሲው ስርጭት በጠቅላላ እስኪያቆም ድረስ መቀጠል እንዳለበት አሳሳበ።
የዩክሬን መንግሥትና አማፅያን ከሁለት ሳምንት በፊት ሚንስክ ቤላሩስ ውስጥ የተስማሙበት የተኩስ አቁም አሁንም መጣሱ ቀጥሏል ። ከስምምነቱ በኋላ በሩስያ ይደገፋሉ የሚባሉት አማፅያን በአንዳንድ የምሥራቅ ዩክሬን ከተሞች ይዞታቸውን እያጠናከሩ ነው ። ለመሆኑ በምሥራቅ ዩክሬን ከተሞች ህይወት ምን ይመስላል ?