ዶይቸ ቬለ በዚህ ሳምንት ያስተናገደው ሰባተኛው የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን መድረክ ትናንት ተጠናቀቀ። በጉባዔው ከ100 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ወደ 2,000 የሚጠጉ የመገናኛ ብዙኃን፣ የፖለቲካ እና የኤኮኖሚው

በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ዜጎች አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸዉን መቀጠላቸዉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ «ዩ ኤን ኤች ሲአር»

«ሃሳብ አልጠል ሲል፤ በልብ የያዙት፤ በጭንቅላት የሚጉላሉት፤ በቀለም ቡሩሽ፤ በስዕል መልክ አልወጣ ሲል፤ ቃላት ቋጥሮ ግጥምን የመደርደር ባህላችን የቆየና የሚኖር ነዉ። የሥነ-ጥበብ ቤተሰቡ ሥነ-ግጥም በከፍተኛ ደስታ እና ኃዘን እንዲሁም ፍቅር ግዜ ሃሳባችንን በቃላት አምቀን የምንተነፍስበት ዘዴ ነዉ» ይሉናል፤ ሰዓሊና ገጣሚ እሸቱ ጥሩነህ

የሰውነት አካላትን እያደማ ለሞት የሚዳርገው የኤቦላ ተኀዋሲ (ቫይረስ) ሥርጭት በምዕራብ አፍሪቃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ። በጊኒ በላይቤሪያ እና በሴራልዮን 467 ሰዎች በኤቦላ ተይዘው መሞታቸውን የዓለም የጤና ድርጅት በእንግሊዝኛ ምህፃሩ «ዳብል ዩ ኤች ኦ» አስታውቋል ።

ኤርትራ ዉስጥ በእስር ላይ የሚገኘዉን የጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅ ጉዳይ አስመልክቶ ከዚህ በፊት በአፍሪቃ የሰብዓዊ ጉዳይ ኮሚሽን ጥያቄያቸዉ እንዲታይላቸዉ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ሶስት የሕግ ባለሙያዎች በኤርትራ ባለስልጣናት ላይ ክስ አቀረቡ።

የአፍሪቃ መሪዎች ባለፈዉ ሳምንት ባካሄዱት ጉባኤ አንድ መሪ በስልጣን ላይ እያለ ክስ እንዳይመሠረትበት መስማማታቸዉ ትችት አስከትሏል። የአፍሪቃ የፍትህና የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት የተሰኘዉ መድረክ ስልጣን ላይ የሚገኙ መሪዎችና ባለስልጣናትን መክሰስ እንዳይችል የታገደ ነዉ።

በያመቱ በሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ሞቃት ወራት ፣ በሳይንስ የኖቤል ሽልማት ያገኙ ጠበብት ከታዳጊ ሳይንቲስቶች ጋር ተገናኝተው ሐሳብ የሚለዋወጡበት ጉባዔ ዘንድሮም ፣ ባለፈው እሁድ በደቡባዊቷ የቦደን ሴ (ቦደን ባህር ) ጠረፍ ከተማ ተጀምሮ እስከፊታችን

ከዓለማችን 162 ሃገራት በሰላም ረገድ ኢትዮጵያ 139 ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አንድ መዘርዝር አመለከተ። ጎረቤት ኬንያ ደግሞ 132ኛ ናት። ይኸዉ መዘርዝር ከሽብር ስጋት አኳያ ኢራቅን በአንደኛ ደረጃ ሲያሰፍር፣ አይስላንድ በዓለም ሰላም የሰፈነባት ሀገር ብሏታል። ኢትዮጵያ ከ157 ሃገራት 37ኛ ናት።

ግንቦት ሰባት እንደሚለዉ የብሪታንያ ዜግነት ያላቸዉ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ባለፈዉ ሳምንት ሰኞ የመን አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፀጥታ አስከባሪዎች ከተያዙ በኋላ ያሉበት ሥፍራና ሁኔታ አይታወቅም

የዩክሬይን ጦር በምሥራቃዊ የሀገራቸው ከፊል በሚንቀሳቀሱት መፍቀሬ ሩስያ ሚሊሺዎች አንፃር የጥቃት ዘመቻቸውን ማጠናክራቸውን አስታወቁ። የዜና ምንጮች እንዳመለከቱት፣ የዩክሬይን ፕሬዚደንት ፔትሮ ፖሮሼንኮ

የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች የቀድሞውን የላክሰምበርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዦን ክሎድ ዩንከርን ለሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንትነት አጭተዋል ። የዩንከር መታጨት ከብሪታኒያ በኩል ተቃውሞ ገጥሞት ነበር ።

የተመድ የአካባቢ ተፈጥሮ ጥበቃ መርሃግብር ከተቋቋመ ረዥም ዓመታት አስቆጥሯል። በዚህ ጊዜ ዉስጥ እንደድርጅቱ የበላይ ኃላፊ እምነት የአካባቢ ተፈጥሮን የሚመለከቱ ጉዳዮች በቂ ነዉ ባይባልም ትኩረት እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።

።«አፍሪቃዉያን ጥሩ ይፋለማሉ» ፃፈ ኦ ግሎቦ የተሰኘዉ የብራዚል ዕለታዊ ጋዜጣ በዛሬ እትሙ «ግን ይሸነፋሉ» እያለ ቀጠለ ጋዜጣዉ።የናጄሪያ ሽንፈትም ከአልጄሪያዉ ብዙ የተለየ አይደለም።ጥሩ ተጫዉተዋል።በፈረንሳይ ሁለት ለዜሮ ከመሸነፍ ግን አላመለጡም።ጥሩ ፍልሚያ ግን ሽንፈት።ለምን?

በምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ በምትገኘው የሄብሮን ከተማ አቅራቢያ ከሁለት ሳምንት ተኩል በፊት የታገቱት የሶስት ወጣት እስራኤላዉያን አስከሬን ትናንት በዚያው መገኘቱን የእስራኤል መንግሥት አረጋገጠ። በእስራኤል መንግሥት ዘገባ መሠረት፣

የሁለገቡን አርቲስት ተስፋዬ ገሠሠ የሙያ ብቃት ያከበረ ዝግጅት በዩኤስ አሜሪካ ሜሪላንድ ውስጥ ተካሄደ። ባለፈው ዓርብ በጣይቱ የባህል ማዕከል አዘጋጅነት በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ለሕክምና ወደ አሜሪካ ያቀኑት የአርቲስቱ ስራዎች

የቻይና ፣ ሳውዲ ዐረቢያ ፣ ሕንድ፣ አውሮጳ እና የዩኤስ አሜሪካ ባለሀብቶች በአፍሪቃ እስያና ደቡብ አሜሪካ ሃገራት በብዙ ሄክታር የሚቆጠር የእርሻ መሬት ለብዙ ዓመታት በርካሽ ዋጋ እየተኮናተሩ ነው።

የዩናይድት ስቴትስና የብሪታንያ መሪዎች የባግዳድ ገዢዎችን በሐስት ወንጅለዉ ኢራቅ ላይ የለኮሱት እሳት ያቺን ሐገር-ሰወስትም አንድም እንዳትሆን ፖለቲከኞችዋን በሐይማኖት ሐራጥቃ ሰነጣጥቆ ሕዝቧን ያስፈጃል።

ብራዚል ውስጥ በመካሄድ ላይ ያለው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በአጓጊነቱና በልብ ሰቃይነቱ ቀጥሏል ። 16 ቡድኖች ከተሰናበቱበት የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ፍፃሜ በኋላ የቀጠለው የጥሎ ማለፉ ግጥሚያ ባለፈው ቅዳሜ በአስተናጋጇ በብራዚል አሸናፊነት

ዶይቸ ቬለ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው ዓለምአቀፍየመገናኛብዙኃንመድረክዛሬ ተከፈተ። በዚህ ሶስት ቀናት በሚቆየው መድረክ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ እስከ 2000 የሚደርሱ ተካፋዮች ይሳተፋሉ።

የእስልምና ቅዱስ ጦርነት አካኺያጅ አማፅያንን ለመዉጋት እንዲያስችል የኢራቅ መንግስት ከሩስያ የገዛቸዉ የጦር ጀቶች ኢራቅ ገቡ። እንደ ኢራቅ መንግሥት ገለፃ፤ ከሩስያ አምስት ጥቅም ላይ የዋሉ ጀቶች ኢራቅ ደርሰዋል።

ብራዚል ላይ እየተካሄደ ባለዉ የዓለም የእግር ኳስ ጨዋታ፤ ቅዳሜ ምሽት የደቡብ አሜሪካ አራት ሀገራት ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች የሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ዉድድር ተጀምሯል። ብራዚል ከቺሊ፤ ኮሎምቢያ ከዑሯጓይ። ብራዚልና ቺሊ ባካሄዱት ግጥምያ በብራዚል 4 – 3 በሆነ ዉጤት ጨዋታዉ ተጠናቆአል። ኮሎምቢያ ዑሯጓይን 2-0 አሸንፋለች

ብራዚል ላይ እየተካሄደ ባለዉ የዓለም የእግር ኳስ ጨዋታ፤ ዛሬ የደቡብ አሜሪካ አራት ሀገራት ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች በሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ዉድድር ጀምሯል። ብራዚል ከቺሊ፤ ኮሎምቢያ ከዑሯጓይ። ብራዚል ከቺሊ፤ 1- 1 በሆነ አቻ ነጥብ ነበር ወደ እረፍት የወጡት። ሁለቱ ቡድኖች ዛሬ መሸናነፍ ይኖርባቸዋል።

የተቀበሩ ፈንጂዎችን ምርት እና ዝውውርን የሚከለክለው የኦታዋ ውል የሚፈተሽበት ሦስተኛው ዓለማቀፍ ጉባዔ ትናንት በሞዛምቢክ ተጠናቀቀ። ውሉን የተፈራረሙት ሀገራት የመጀመሪያውን ጉባዔ ያካሄዱት ከ15 ዓመታት በፊት ነበር ። ደቡባዊትዋ አፍሪቃ ሀገር ሞዛምቢክ ያኔ በዓለም እጅግ ብዙ ፈንጂዎች ከተቀበሩባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ነበረች።

የተቀበሩ ፈንጂዎችን ምርት እና ዝውውርን የሚከለክለው የኦታዋ ውል የሚፈተሽበት ሦስተኛው ዓለማቀፍ ጉባዔ ትናንት በሞዛምቢክ ተጠናቀቀ። ውሉን የተፈራረሙት ሀገራት የመጀመሪያውን ጉባዔ ያካሄዱት ከ15 ዓመታት በፊት ነበር ። ደቡባዊትዋ አፍሪቃ ሀገር ሞዛምቢክ ያኔ በዓለም እጅግ ብዙ ፈንጂዎች ከተቀበሩባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ነበረች።

ብራዚል ላይ እየተካሄደ ባለዉ የዓለም የእግር ኳስ ጨዋታ፤ ዛሬ የደቡብ አሜሪካ አራት ሀገራት ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች በሚያደርጉት ግጥምያ የጥሎ ማለፍ ዉድድሩ ይጀምራል። ብራዚል ከቺሊ፤ ኮሎምቢያ ከዑሯጓይ። በደቡብ አሜሪካ የሚገኙት ሀገራት በዘንድሮዉ የእግር ኳስ ግጥምያ፤

በአስተናጋጅ ሀገር ብራዚል ፣ ባለፉት 2 ሳምንታት ከዓለም ዙሪያ በተወከሉ ባጠቃላይ የ 32 ሃገራት ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የሰነበተው የመጀመሪያ ዙር ውድድር፣ ትንንት ማምሻውን ተደምድሟል። የዓለም የእግር ኳስ ፌደሬሽን

ከ 9 ዓመት በፊት የካርቱምና የጁባ ባለሥልጣናትና ተወካዮች ፣ ጦርነት አቁመው ውል ሲፈራረሙ በአካባቢው ዘለቄታ የሚኖረው ሰላም ይሠፍናል የሚል ብሩሕ ተስፋ ነበረ ያኔ ያሳደረው። ግን አልሆነም። ይባስ ብሎ በዚያው በደቡብ ሱዳን ሁለት የሥልጣንና

የአውሮፓው ሕብረት መሪዎች ትናንት ከብራሰልስ 150 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው፣ ከአንድ መቶ ዓመት በፊት፣ በአንደኛው የዓለም ጦርነት አውድማነት በምትታወቀው ከግማሽ ሚሊዮን የማያንስ ሠራዊት ባለቀባትና ለመጀመሪያ ጊዜ መርዘኛ የሰናፍጭ ጋዝ ሰለባ

ዛሬ ማምሻዉን በጉጉት ከሚጠበቁት ዉድድሮች አንዱ በጀርመን እና በዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ ቡድኖች መካከል የሚካሄደዉ የእግር ኳስ ግጥሚያ ነዉ። የብዙዎችን ዐይን ወደ ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ እንዲያተኩር የሚያደርገዉ ደግሞ በምናባዊ ትንታኔ በሁለት የጀርመን ቡድኖች መካከል የሚደረግ ፉክክር መምሰሉ ነዉ።

በናይጀሪያ ሰዓት አቆጣጠር ትናንት አመሻሹ ላይ በዋና ከተማ አቡጃ ህዝብ በሚያዘወትረዉ የገበያ ማዕከል የደረሰ ፍንዳታ ለ21 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል። ከ50 በላይ ሰዎችም መጎዳታቸዉ ተነግሯል።

የኬንያ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መንግሥት ጥያቄአቸውን እንዲቀበል ያቀረቡት ጥሪ በጎ ምላሽ ካላገኘ በሃገሪቱ የሰፈነው ውጥረት ሊባባስ እንደሚችል አንድ የፖለቲካ ተንታኝ አስታወቁ ።

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት በ«UNESCO» ዘጠኝ መካነ ቅርሶችን እና አንድ የማይዳሰስ ቅርስን፤ በአጠቃላይ አስር ታሪካዊ ቅርሶችን አስመዝግባለች። ጀርመን ደግሞ ከስፔን እና ከጣልያን ለጥቃ 39 ቅርሶችን በዓለም ቅርስነት በማስመዝገብ ሶስተኛዋ የዓለም ሀገር ናት።

የኢጣልያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን፣ ፣ኮስታ ሪካ፤ ዑሩጓይና ኢንግላንድ ከሚገኙበት መ ምድብ፣ ትናንት ከዑሩጓይ ጋር ባደረገው ግጥሚያ እኩል ለኩል መለያየት ብቻ ለቀጣዩ ዙር ግጥሚያ ከኮስታሪካ ጋር በሁለተኛነት ለማለፍ የነበረው ዕድል በ 1-0

ጫት ወደ ብሪታንያ እንዳይገባና እንዳይሸጥ ብሎም፤ ጫት ሲቅምም ሆነ ሲሸጥ የሚገኝ ሰው በገንዘብ እንደሚቀጣና ለእሥር እንደሚዳረግ የወጣው ድንጋጌ ከትናንት አንስቶ ተግባራዊ መደረጉ ተነገረ። ሕጉ ሥራ ላይ መዋሉ ፤

በዓለም ዙሪያ የውጭ ባለሃብቶች ውረታ እጎአ በ2013 አፍሪቃን ጨምሮ አድጓል ። ግን በአፍሪቃ የእድገቱ መጠን ከሌላው የዓለም ክፍል ጋር ሲነፃጸር ዝቅ ያለ ነው ። የተባበሩት መንግሥታት የንግድና የልማት ጉባኤ በምህፃሩ UNCTAD ትናንት ባወጣው ዘገባ መሠረት በዓለም ዙሪያ የመሰረተ ልማት ግንባታና የኩባንያዎች እንቅስቃሴ በ9 በመቶ አድጓል ።

በመላ ኢትዮጵያ የሚታየው የጨው እጥረትና ውድነት፣ በአንጻሩ ደግሞ አፋር ውስጥ ፣ በአፍዴራ፣ ዶቢና ካዳባ በተሰኙት ቦታዎች ያለው የጨው ክምችት፣ ጤናማ የግብይት ሥርዓት አለመኖሩን ያመለክታል ይላል አካባቢውን ጎብኝቶ የተመለሰው ዘጋቢአችን ፣ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ።

ኢትዮጵያ፤ ከባሕር ልክ በታች 120 ሜትር ዝቅ ካለው ቦታ አንስቶ 4,620 ሜትር ከፍታ እስካለው ሥፍራ ፣ የሚያቃጥል የቀን ሐሩር ፣ የሚያኮማትር የሌሊት ቁር ፣ እንዲሁም ለዘብ ያለ የአየር ጠባይ ያላት ሀገር በመሆኗ ፤ ላገር ጎብኝዎች መስሕብነት