አምባሳደር ተወልደ ከፓርቲው ለቀቁ ከኢየሩሳሌም አርአያ
የሕወሐት ማ/ኰሚቴ አምባሳደር ተወልደ ገብሩ (በቅጽል ስማቸው ተወልደ አጋሜ) በገዛ ፈቃዳቸው ከፓርቲው እንደለቀቁ ምንጮች አረጋገጡ። ባለፈው በተካሔደው የፓርቲው ጉባኤ ላይ የመልቀቂያ ጥያቄ አቅርበው ከማ/ኰሚቴ አባልነት እራሳቸውን እንዳገለሉ አስታውቀዋል። በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ተወልደ «አጋሜ» ከ 1993ዓ.ም በሑዋላ ተዛውረው በአትሌቲክስ ፌዴረሽን ያለሙያቸው ተመድበው ቆይተዋል። በተጨማሪ ባለቤታቸው ሮማን ገ/ስላሴ በፓርቲው ሊ/መንበር « አይኖዋን ማየት አልፈልግም» ተብለው ከፓርቲው ርቀው […]