ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን በርሊን ተደረገ

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለፈው ኖቨምበር ስድስት ቀን 2012 እ.ኤ.አ. በአይነቱ ልዩ የሆነ በተለያዩ መፈክሮች እና በኢትዮጵያ ባንዲራ ያሸበረቀ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን አደረጉ። ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው በጀርመን የፖለቲካና የሲቪክ ማህበራት አንድነት ድርጅት (EPCOU) ሲሆን፣ በዕለቱም ከተለያዩ የጀርመን አካባቢ የሚኖሩ ቁጥራቸው ከ290 በላይ የሚገመት ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል።