አጫጭር የሀገር ቤት ወሬዎች

(ምናባዊ አጫጭር ዜናዎች) ይነጋል በላቸው

ኢትዮጵያ የሁለት ፕሬዝደንቶች ሀገር መሆኗ ተገለጸ ዘግይቶ የደረሰ አስደሳች ዜና – የመለስ ፎቶ ሀገር አስለቀቀ የኑሮ ውድነቱ ሕዝብን እያስለቀሰ ነው የኢትዮጵያ ኤፍ ኤሞች መንግሥታዊ አደራቸውን በብቃት እየተወጡ ናቸው ተባለ New Tense has been found in Ethiopia!

ኢሣት ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ እንዳይሠራጭ ታፈነ

ከአንድ ዓመት ተኩል ስኬታማ አፈና በኋላ የተጣለበትን ተደጋጋሚ የአየር ሞገድ እመቃ ተቋቁሞ ላለፉት ጥቂት ሣምንታት በኢትዮጵያ ሥርጭቱን ጀምሮ የነበረው የኢሣት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ከትናንት በስቲያ ኅዳር 4 ቀን 2005 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ዝነኛ ሥርጭቱ መቋረጡ ታወቀ። ባለፉት የሥርጭት ጊዜያት ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የብሶት መተንፈሻና የታፈኑ የሀገር ቤት ዜናዎች ማወጃ ሆኖ መሰንበቱ የሚታወቅ ነው።