የምሥራቅ ዓባይ ተፋሰስ ሚኒስትሮች ስምምነትን የሱዳንና ኢትዮጵያ መሪዎች አፀደቁ

–    የግብፅ ውሳኔ እየተጠበቀ ነው
–    በግብፅ መንግሥት ከፀደቀ ደቡብ ሱዳን አባል ትሆናለች

በዮሐንስ አንበርብር

ሦስቱ የምሥራቅ ዓባይ ተፋሰስ አገሮች፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያና ሱደን የውኃ ሀብት ሚኒስትሮች ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ የደረሱበትን ስምምነት የሱዳንና የኢትዮጵያ መሪዎች አፀደቁ፡፡ የግብፅ መንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው፡፡