ኢትዮጵያዊው ዑሴይን ቦልት የራሱን ሪከርድ አሻሻለ
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ለለውጥ ያህል ለምን አንባቢን ፈገግ ልታደርግ በምትችል የአዲስ አበባ ዘመነኛ ቀልድ አልጀምርም? … አንድ የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣን በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ሲዝናና ያመሻል። ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ወደቤቱ ሊሄድ ቄንጠኛ ፕራዶ መኪናውን ሊያስነሳ ቢሞክር ያልታሰበ ብልሽት ያጋጥመውና ሞተሩ ለመነሣት እምቢዬው ይለዋል። ቢለው፣ ቢለው አልሆነለትም። ከዚያም ሌላ ምርጫ ሲያጣ ላዳ ታክሲ ያስጠራና ወደቤቱ እንዲያደርሰው ሹፌሩን ይጠይቀዋል።