በአዲስ አበባ የመንገድ ፕሮጀክቶች ባለድርሻ አካላት እየተወነጃጀሉ ነው

-    ዘንድሮ ከ1900 በላይ ቤቶች ይፈርሳሉ

በዳዊት ታዬ

በአዲስ አበባ መንገዶች ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸሞች መስተጓጐል ምክንያት በባለድርሻ አካላት መካከል ያለመግባባት በመፈጠሩ አንደኛው ሌላኛውን ተጠያቂ እያደረገ ነው፡፡