ግርማ ካሣ ([email protected]) ”ከፌዴሬሽኑ ጀርባ ልንሰለፍ ይገባል” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ጽሁፍ፣ እጅግ በጣም በርካታ ምላሾች በኢሜል ደረሱኝ። ኢሜሎቹ በሙሉ የተቃውሞ ኢሜሎች ናቸው። አንዳንዶቹ ከመቃወም አልፈው ስድብና ዛቻም አዝለዋል።

በታሽጉ ፓኬቶች ውስጥ ተደብቀው የተጓጓዙ ቦንቦች ጉዳት ሳያደርሱ በፊት ከተደረሰባቸው ወዲህ በአውሮፓ ስጋቱ እያየለ መጥቷል። ሰኞ ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ብራስልስ ላይ የአውሮፓ የሀገር ውስጥ ሚንስትሮች ስጋቱን ተከትሎ ተወያይተዋል።

ቢቢሲ ባለፈው መጋቢት ወር ባወጣው በዚህ ዘገባ ላይ የእርዳታ ገንዘቡን ያሰባሰበውን የሙዚቃ ቡድን “ባንድ ኤድ”ን የመራውን ሙዚቀኛ ሰር ባብ ጌልዶፍን  ከትናንት በስቲያ ባሠራጨው ዘገባ ይቅርታ መጠየቁን ከዚህ በቀደመው ዘገባ አስደምጠናል። ከኢትዮጵያ መንግሥት የኮሚኒኬሽን መሥሪያ ቤት የወጣ መግለጫ ደግሞ “ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ …

ቢቢሲ፣ ባንድ ኤድና የኢትዮጵያ መንግሥት Read more »

(በመላኩ ደምሴ) የኢትዮጵያን የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የፖሊሲ አማራጮችን የሚዳስስና የውሳኔ ሐሳቦችን የሚያቀርብ ኮንፈረንስ በመጪው ማክሰኞና ረቡዕ አዲስ አበባ ውስጥ ሊካሄድ ነው፡፡

(በታምሩ ጽጌ) የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከአራት ወራት በፊት በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠርጣሪዎች ላይ የተላለፈን ትዕዛዝ ሳይፈጽም በመገኘቱ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ተላለፈ፡፡

በሆላንዳዊው የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባል በሚስተር ቲዝ በርማን የተመራው የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን፣ ከአምስት ወራት ዝምታ በኋላ የግንቦት 2002 ምርጫ ትዝብት ሪፖርቱን በነገው ዕለት ይፋ ያደርጋል፡፡

(በየማነ ናግሽ) በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የወለንኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ወቋተህዴን) ፓርቲ አምስት ከፍተኛ አመራሮችና አንድ አባል ለ12 ቀናት ታስረው ከቆዩ በኋላ ባለፈው ዓርብ ተፈተዋል፡፡

– አራት ኮሌጆች ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ከስረዋል እየተባለ ነው (በታምሩ ጽጌ) መንግሥት የትምህርት ሥልጠና ጥራትና አግባብነትን ለማረጋገጥ በሚል፣ ማንኛውም የግል ከፍተኛ ተቋማት የሕግና የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ ያስተላለፈውን ክልከላ ተከትሎ፣ በርካታ የርቀት ትምህርት መምህራን ከሥራ እየተሰናበቱ መሆኑን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

(በጋዜጣው ሪፖርተር) ባለፈው ዓርብ የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ አማካሪዎች ቡድን ሪፖርቱን  ለተባበሩት መንግሥታት ሲያቀርብ፣ ካሁን በኋላ ግፊቱና ጫናው የሚበዛው በበለጸጉ አገሮች ላይ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስታወቁ፡፡

(በታደሰ ገብረ ማርያም) ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በቦሌና በየካ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ሁለት አካባቢዎች በድምሩ 56 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታዎችን አስፋፍቶ ይዟል ተብሎ የተገለጸው ፍጹም ሀሰት ነው ሲል አስታወቀ፡፡

(በታምሩ ጽጌ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለይ ገርጂ መብራት ኃይል፣ ኢምፔሪያል ሆቴል አካባቢ፣ ካዛንችስ፣ ጐፋ መብራት ኃይልና አልፎ አልፎ በሌሎቹም አካባቢዎች ባሉ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ነዋሪዎች በጠራራ ፀሐይ እየተዘረፉ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

(በሚኪያስ ሰብስቤ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ፣ ሌሎች 13 የወቅቱ የድርጅቱ ሠራተኞች የሚገኙበትን የሙስና ክስ ጉዳይ እያየ ያለው የከፍተኛው ፍርድ ቤት አንደኛ ደረጃ የወንጀል ችሎት፣ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ለኅዳር 22 ቀን 2003 ዓ.ም. ቀጠሮ ይዟል፡፡

መዝ/101/ንግረኒ ውኅዶን ለመዋእልየ ኢትስዶኒ በመንፈቀ አመትየ፤የዘመኔን አእነስተኛነት ንገረኝ በዘመኔም እኩሌታ አትውሰደኝ የድልድይ ነገር ሲነሳ መቺም በየትውልድ ቀዬአችን የተሻገርናቸው ያየናቸው በትዝታ የምንቃኛቸው በርካታዎች ናቸው መቼም ከነዚህ ውስጥ ታላላቅ ድልድዮቻችን ውስጥ ሁላችን ባናያቸው እንኩአን በስም የምናቃቸው ውስጥ አዋሽ፤ባሮ፤ተከዜ፤አባይ፤መቺም በነዚህ ታላላቅ ድልድዮችችን ግንብታውን …

እኛ እና ድልድዮቻችን – ወንድወሰን ከሀገረ እንግሊዝ Read more »

ሙሉ ገ. ኢሕአዴግ በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ እና ነገ “ከፍተኛ የኾነ ሕዝባዊ ንቅናቄ እና ውይይት” ማከሄድ ጀመረ። በዚሁ “ሕዝባዊ ንቅናቄ” ላይ የአምስት ዓመቱን የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለሕዝቡ ለመስበክ የኢሕአዴግ ካድሬዎች ክፍተኛ የኾነ ርብርብ ሲያደርጉ መሰንበታቸውንም የአዲስ ነገር የአዲስ አበባ …

የአምስት ዓመቱን የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለመስበክ ዛሬ እና ነገ “ሕዝባዊ ንቅናቄ” ይካሄዳል Read more »

ኢሕአዴግ የምርጫ 2002 እፍረቱን ለማረሳሳት (ሊረሳ የሚችል ከሆነ) ብዙ ሙከራዎችን ማድረግ ነበረበት። የመጀመሪያው እና ትልቁም “የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” ተብሎ የቀረበው ሰነድ ነው። ዕቅዱ በይዘቱም ሆነ በቅርጹ ሰፊ የሐሳብ ልውውጥን የሚጋብዝ ነው። እስካሁን በብዛት ትኩረት የተሰጠው ግን ዕቅዱ ሊሳካ የሚችል …

[አንድ ለቅዳሜ ] ሥልጣን እንጂ ተጠያቂነት የሌለበት “የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” Read more »

ወ/ሮዋ በሐውልቱ ምረቃ ዕለት ንግግር ሲያደርጉ ወይዘሮዋ ‹‹ሲኖዶሱ በእኛ ገንዘብ ምን አገባው?›› በሚል የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ አፈጻጸም በመቃወም ተግባራዊነቱን የሚያደናቅፍ ቡድን አደራጅተው ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ ጠንካራ ትችት የሰነዘሩባቸውን ብፁዓን አባቶች እየደወሉ በመሳደብ እየዛቱባቸው ነው፤ …

ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ቅጽር ግቢ እንዳይገቡ የተጣለባቸው እገዳ እየተከበረ አይደለም Read more »

(Addisu Tesfaye):- I read Dilwonberu’s article, posted on Deje Selam, which was written with the intent of defending the patriarch Paulos statue. Anyone who reads the article could understand the implicit and explicit message Dilwenberu tried to convey. Explicitly, he …

Patriarch Paulos Statue and its Catholic origin: A Rejoinder to Dilwenebru’s Article Read more »

ጥቅምት 1998 በዘረኝነት የተለከፉ ሰዎች ጭካኔን፣ በየቤታችን በራፎች፤ በገዛ ዓይኖቻችን ያየንበት ወር ነው። ዘረኛ የሆነ ሰው ከራሱ ዘውግ ውጭ ያሉ ሰዎችን እንደ ጥቃቅን ነፍሳት በመቁጠር እየተዝናና እንደሚጨፈልቃቸው ተመልክተናል። ቀድሞ በአውሮፓ በናዚ ጀርመን፣ በቅርቡ በሰርቪያና በኮሶቮ፤ እንዲሁም በአፍሪካ ሩዋንዳ የታየው ዓይነት …

ሰማዕታት ለጣሉብን ኃላፊነት ብቁዎች ነንን? እራሳችንን እንጠይቅ! Read more »

ዓርብ ጥቅምት 26 ቀን 2003 ዓ.ም የአዉሮፓ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ሰኞ ጥቅምት 29 ቀን 2003 የመጨረሻ ሪፖርቱን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ሪፖርቱ በኢትዮጵያ የተደረገዉን የ2002 ምርጫ፣ የአለም አቀፍ መስፈርትን ያላሟላ እንደሆነና ዲሞክራሲያዊ ወይንም ፍትሃዊ ተደረጎ ሊቆጠር እንደማይችል፣ መረጃዎችን በመዘርዘር …

ከ3 ቀናት በኋላ የአዉሮፓ ሕብረት ታዛቢ ቡድን ሪፖርቱን ይፋ ያደርጋል Read more »

የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ በዜና ሥርጭቱ “የኔም ስም ነው የጎደፈው” በማለት ቢቢሲ ይቅርታ እንዲጠይቅ መግለጫ አውጥቷል። ቢቢሲ ዘገባውን ባሠራጨበት ጊዜ “የዘገባውን ትክክለኛነት አውቃለሁ” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ቃለ ምልስስ የሰጡትን “በወቅቱ የህወሓት ታጋይ የነበርኩ” የሚሉትን አቶ ገብረመድኅን አርአያን አነጋግረናል፡፡ ለዝርዝሩ ዘገባውን …

ቢቢሲ ጌልዶፍን ይቅርታ ጠየቀ Read more »

ዲሞክራቶች በሁለት ሺህ ስድስት ሁለቱንም ምክር ቤቶች በሁለት ሺህ ስምንት ደግሞ ዋይት ሐውስን እንደተቆጣጠሩ ሲታወቅ በዚያ መልክ የመቀጠሉ ነገር ግን አጠራጥሯል፡፡ በዚህ ድባብ መሃል ደግሞ ቅዳሜ ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ ታዋቂ የፖለቲካ ኮሜዲያኖች የጠሩት “RESTORE SANITY” (“ኧረ ልቦና ይስጠን” ብለን በግርድፉ …

በዩናይትድ ስቴትስ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ የተወካዮች ምክር ቤትና የአገረ ገዢዎች ምርጫ ነገ ማክሰኞ ይካሄዳል። Read more »

ቀሲስ መብራቱ (ከፌስቡክ የተወሰደ) (ቀሲስ መብራቱ ኪሮስ (ቶሮንቶ : ካናዳ):- ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን በጻፈው መልእክት በ11ኛው ምዕራፍ አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረጉ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን የእምነት ተጋድሎ በአጭሩ ይተርካል። ስለ ሁሉም “እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል”  ካለ በኋላም እነዚህ ታላላቅ የእምነት ምስክሮች …

ዋኖቻችሁን አስቡ (ዕብ ፲፫፥ ፯) Read more »

የአለም ባንክ በቅርቡ ባደረገው ጥናት፣ ውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው በየአመቱ የሚልኩት ገንዘብ 3.2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ገልጿል። ይህ ቁጥር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚያወጣው ቁጥር ጋር እጅግ ይራራቃል። ብሔራዊ ባንክ በየአመቱ ከውጭ ኢትዮጵያውያን ተላከ እያለ የሚያወጣው ገንዘብ አንድ ቢሊዮን …

አቅሙን ያወቀ ማህበረሰብ ፖለቲካዊ ተጽእኖዎችን ለማድረግ ሊንቀሳቀስ ይችላል!!! Read more »

የአለም ባንክ በቅርቡ ይፋ ባደረገው የጥናት ውጤት ኢትዮጵያ በየአመቱ ውጭ አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የምታገኘው ገንዘብ 3.2 ቢሊዮን ዶላር ነው ማለቱን አፍሪክ-ኒውስ የተባለው የዜና አውታር ዘግቧል። ይህ ቁጥር በወያኔ አገዛዝ ቁጥጥር ስር ያለው ብሔራዊ ባንክ በየአመቱ ከሚያስቀምጠው በእጥፍ ድርብ የሚበልጥ ነው፤ …

የአለም ባንክ ውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በየአመቱ ወደ አገራቸው የሚልኩት ገንዘብ መጠን ብሔራዊ ባንክ ከሚለው በሶስት እጥፍ ይበልጣል አለ Read more »

በ1994 አመተ ምህረት በአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ተቋቁሞ እና በየአመቱ ሲካሄድ የቆየው ታላቁ ሩጫ በዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ቁጥጥር ስር ሳይወድቅ እንዳልቀረ የሚያመለክት መረጃ ለግንቦት 7 ድምጽ የዝግጅት ክፍል ደርሷል። በህዝቡ ዘንድ “የብሶት መግለጫ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ዝግጅት፤ በተለይ ከ97ቱ …

የታላቁ ሩጫ ቲኬት ገበያ ላይ መሆኑ ሳይታወቅ ተሸጦ ማለቁ አነጋጋሪ ሆኖ ሰነበተ Read more »

“ሂውማን ራይትስ ዋች” የተባለው አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሰራተኛ የሆኑት ሚስ ሌስሊ ሌፍኮው ሰሞኑን ባወጧቸው ጽሁፎች የአውሮፓ እና የካናዳ መንግስታት አፋኝ የሆነውን የወያኔ አገዛዝ እየረዱ ነው ብለዋል። “ሂውማን ራይትስ ዋች” በቅርቡ ባወጣው ሰፊ ሪፖርት፣ ምእራባውያን መንግስታት ለወያኔ በአመት ከ3 …

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ የውጭ እርዳታን ለአፈና ማዋሉ መወገዙ እንደቀጠለ ነው Read more »

ኖርዌይ በምግብ ፕሮግራሞች እና በህጻናት እርዳታ ስም የምትለግሰውን ገንዘብ ከሙስና እና ከምዝበራ ለመከላከል የአገሪቱ እርዳታ ሰራተኞች በቂ ስራ እየሰሩ አይደለም ሲሉ የኖርዌይ ኦዲተር ጄኔራል ማውገዛቸው ተዘግቧል። “ሂውማን ራይትስ ዋች” በቅርቡ ባወጣው ሰፊ ሪፖርት፣ ምእራባውያን በድሆች ስም ለወያኔ አገዛዝ የሚሰጡት እርዳታ …

የኖርዌይ መንግስት ኦዲተር ጄኔራል የአገሪቱን የእርዳታ ቁጥጥር ሂደት አወገዙ Read more »

የፌዴራል ፖሊስ አባል እና የቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሰርቬላንስ ክፍል ሃላፊ የሆነ ግለሰብ በሙስና ምክንያት መታሰሩን አፍሪክ ኒውስ የተባለው የዜና ድረ-ገጽ ዘግቧል። ሳጅን ማሞ ሻሎ የተባለው ግለሰብ አንዲትን ሴት በሽብርተኝነት ታስራ እንደምትከሰስ ነግሮ እራሷን ለማዳን ስትል ጉቦ እንድትሰጠው በማስፈራራቱ ምክንያት …

አንድ የፌዴራል ፖሊስ ባለስልጣን መታሰሩ ተዘገበ Read more »

የመንግስት ሆስፒታሎች በጉቦ እና በዝምድና ካልሆነ በስተቀር አገልግሎት ወደማይሰጡበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ሲል የግንቦት 7 ድምጽ ዘጋቢ ከአዲስ አበባ በላከው መረጃ አመልክቷል። ከጊዜ ወደጊዜ ብቃታቸው እየጎደለ የሄደው የመንግስት ተቋማት፣ እና በተለይም ሆስፒታሎች፣ የአገልግሎት ደረጃቸው እና ሽፋናቸው ዝቅ እያለ መሄዱን በተደጋጋሚ …

በአዲስ አበባ ከተማ በምጥ ላይ ያሉ ነፍሰ ጡሮች የሆስፒታል አልጋ ለማግኘት እንደሚንከራተቱ ታወቀ Read more »

የዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናት እና ካድሬዎች የኢትዮጵያን ህዝብ ከሚበዘብዙባቸው መንገዶች ውስጥ ብዙ የማይወራላቸው የቀበሌ መናፈሻዎች መሆናቸውን የሚጠቁም መረጃ ሰሞኑን ለዝግጅት ክፍላችን ደርሷል። በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሁሉም ቀበሌዎች ሊባል በሚችል ሁኔታ በወሳኝ አካባቢዎች የተቋቋሙ የህዝብ መናፈሻ ማእከላት እንዳሉ ይታወቃል። …

ህዝብ ንብረት ከሆኑት የቀበሌ መናፈሻዎች የሚገኘው ትርፍ የወያኔ ካድሬዎች ሽልማት ነው ተባለ Read more »

ለአዲስ ድምፅ ራዲዮ ቃለምልልስ ሰጠች Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥቅምት 25 ቀን 2003 ዓ.ም. November 4, 2010)፦ ”ታዋቂና ተወዳጅዋ አርቲስት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች” ሲል በአሜሪካን ሀገር የሚገኘው ”የሀገር ፍቅር ራዲዮ” ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 20 ቀን 2003 ዓ.ም. ያሠራጨውን …

”ሂሩት በቀለ ሞተች” የሚባለው ወሬ ሐሰት መሆኑ ተረጋገጠ Read more »