እኛ እና ድልድዮቻችን – ወንድወሰን ከሀገረ እንግሊዝ
መዝ/101/ንግረኒ ውኅዶን ለመዋእልየ ኢትስዶኒ በመንፈቀ አመትየ፤የዘመኔን አእነስተኛነት ንገረኝ በዘመኔም እኩሌታ አትውሰደኝ
የድልድይ ነገር ሲነሳ መቺም በየትውልድ ቀዬአችን የተሻገርናቸው ያየናቸው በትዝታ የምንቃኛቸው በርካታዎች ናቸው መቼም ከነዚህ ውስጥ ታላላቅ ድልድዮቻችን ውስጥ ሁላችን ባናያቸው እንኩአን በስም የምናቃቸው ውስጥ አዋሽ፤ባሮ፤ተከዜ፤አባይ፤መቺም በነዚህ ታላላቅ ድልድዮችችን ግንብታውን ስናስብ የውጣባቸው ገንዘብ እውቀት ስናስብ ለሃገር በተለይም በአካባቢው ለሚኖሩ ኑሮአችን ብለው በዛ ለሚመላለሱ ከመገንባታቸው ቀደም በሎ የነበሩ ችግሮችን ስናስታውስ ያሰቡት ሳይደርሱ ስንቱ በውሀ ተበላ ስንቱ መኃል ቀረ ከውሀው ከመበላት በባሰ በውኅው ውስጥ ባሉ አውሬዎች ስንቱ ተበላ ሰንት የጋማ ከብትና የቤት እንስሳት ሳይቀሩ የመከራው ተጋሪዎች ነበሩ በዚህ ድልድይ መገንባት ሽክም ቀሎላቸዋል ብንል ማጋነን አይሆንም ባሮ ድልድይ ሲገነባ ለጊዜው ስማችውን የዘነጋሁት የአውራ ጎዳና ባለስልጣን መ/ቤት እውቅ መሀንዲስ በአውሬ መበላትታችውን አውቃለሁ ሀውልት ይቁምላቸው አይቁምላቸው አላውቅም ህዝብን ውደፈለገበት አሸጋግረው እሳቸው አልፈዋል ድልድዮ ግን ስራቸውን ሲናገር ይኖራል በዚህ ድልድይ መገንባት የተጎዱ በውሀው ውስጥ ተቀምጠ ፍጥረታትን እየሳቡ ደም ይመጡ የነበሩ አውሬዎች በርግጥ ተጎድተዋል እድላቸው እርስ በእርስ መበላላት ይሆናል;።
እኔ ዛሬ አነሳሴ በኢትዮጲያ.ኦ.ዶ.ተ.ቤተክርስቲያን ዙሪያ ስላሉ ድልድዮቻችን ያሻግሩናል ወይስ ለአውሬ ያስበሉናል መዳህኒታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የድንግል ማሪያም ልጀ እራሱ በደሙና በስጋው በመሰረተው ድልድይ የሰውን ልጅ ከሞት ወደ ህይወት አሸጋግሮ ከራሱ ጋር ያስታረቀበት ያ በቀራንዮ የፈሰሰ ደም ያ በቀራንዮ የተወጋ ስጋ ከባርነት ወደ ዘላለም ነጻነት ያሸጋገረን ክቡር የህይወት ድልድይ ተጠብቆ እንዲኖር በዚሁ ላይ በጎቹን እንዲያሸጋግሩ ከሰው መርጦ ለሹመት ከእንጨት መርጦ ለታቦት እንዲሉ ከሰው መርጦ በሾማቸው ሀዋርያት ዛሬ ላይ ደረስን ዛሬ ዛሬ እንዳለመታደል ሆኖ በእነጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በሰማእቱ በእነ አቡነ ጴጥሮስ በእነ አቡነ ሚካኤል በሰማእቱ በእነ መምህር ገብረስላሴ እረ ሰንቱ እልፍ አእላፍ ሰማእታት እና በእነዛ ድንቅ ድንቅ ሊቃውንት ቤት አርተፊሻል መሰል አንደበትና ልባቸው የተለያየ የበጎቻቸው እንግልትና ስቃይ ግድ ያልሰጣቸው የእግዚአብሄር ህንጻዎች(ፍጥረታት) በጥይት ሲፈርሱ መቃወምን አግባብ አይደለም የሚሉ አጥፊዎች ሲወቀሱ ሀጢያት ነው የሚሉን ከራሳቸው ታርቀው በጎቻቸውን መቼ ነው ማሩን ብለው እውነተኛ ድልድይነታቸውን የሚያሳዩን ሉቃስ/ም/11/ቁ50 አለም ከተፈጠረ ጀምሮ የፈሰሰው የነቢያት ሁሉ ደም ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደሱ መካከል እስከፈሰሰው እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ ከዚህ ትውልድ እፈልጋልሁ፤ እያለ እስራኤላውያንን የጠየቀ አምላክ እኛንስ በጅማው አቡዬ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የታረዱት ካህንና መእመን ወይስ በስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በፈሰሰው በባህታዊው ደም ወይስ በሰሜን ሸዋ በቅዱስ ሚካኤል ቢተክርስቲያን ደጃፍ ላይ ባልታወቀ ሰው ተብሎ ከጀርባቸው በጥይት የተደፉት ካሀን ወይስ በአሰቦት ገዳም የታረዱ መነኮሳት ደም ወይስ በብጹ አቡነ ቲዋፍሎስ ወይስ ቀብራቸው ባልታወቀው በአባ ሳሙኤል ደም ወይስ በዘራቸው ተመርጠው ከነንብሳቸው ገደል በተጣሉ ነፍሳት በዘራቸው ተመርጠው አድራሻቸው በጠፋው ነብሳት ቤትኛው እንጠየቅ ቤትኛው አንጠየቅ ይሆን ይህስ ደም መፋሰስ ማብቂያው መች ይሆን መቼም ዝምታን የመረጠች አንደበት ባለቤቱዋ ሲጠይቃት መልሱዋ ምን ይሆን።እኔ ወደዝች ቀደምት ቤተክርስቲያን መለስ ብዬ በዝና ከማውቃቸው ጠንካራ ድልድዮቻችን ውጪ እግዚአብሄር አድሎኝ በዘመኔም ከዛሬው ከሚታየው ደስታና ተድላ ይልቅ ያን ሰማያዊ መንግስት የሚመለከቱ እምቢኝ ስልጣን እምቢኝ ሀብት በማለት ማተባቸውን ያልበጠሱ ቃላቸውን ያላጠፉ እግዚአብሄር በሰጣቸው ከብር ላይ የአለሙ ድሪቶ ያላጉዋጉዋቸው በህይወት ካለፉብን ውጭ ዛሬም በህይወት ያሉንን ድልድዮች ስመለከት ዳግም የመነመነው ተስፋዬን ያለመልሙልኛል ፤አይለፍከነ ማይከለ እሳት ወማይ ወይጻእከነ ውስተ እረፍት፤ቅዱስ ዳዊት በሳትና በውሃ የመሰለው የዘመኑን ስልጣንና ሀብት ነው በዚህ እሳትና ውሃ ያላችሁም ልትገቡም ያኮበኮባችሁም እግዚአብሄር አምላክ ልቦና እንዲሰጣችሁ የዘመትር የምእመን ጽሎት ነው። አንድ በልጅነቴ እሻገረው የነበረውን ድልድይ ዛሬ ላይ ቆሜ ሳየው የሰፈሩ ሰው ለመሻገሪያ የሰራው እንደነገሩ የሆነ ድልድይ ነው ያኔ ልጅ በመሆኔ በዛ በተበላ ድልድይ ላይ መውጣቴ መቼም ማመዛዘን በማይቻልበት ዘመን ለነብሰም ለስጋም በዙ አይታሰብም ዛሬ ግን በእንደዚያ ያለ ሾላካ ድልድይ ላይ የምሻገር የዋህ አይደለሁም ዛሬ ለነብሴም ለስጋዬም ምቾት ያለው አስተማማኝነቱን አረጋግጬ አምኜ የምሄድበት ደልድይ እፈልጋለሁ አባ ጳውሎስ ተጠራጣሪ አድርገውኛል ዙርያቸው ያሉትን ታጣቂዎች በመነኮሳት ስም የመነኮሳት ልብስ አልብሰው ከደባለቁብን ወዲህ የአባ ጳውሎስን መልክተኛ አምኜ እንዳልቀርብ ሆኛለሁ ነብሳቸውን ከደጋግ አባቶቻችን ጋር ያሳርፍልኝ አቡነ ፓስሊዮስ የአቡነ ጳውሎስ ምክትል የነበሩት አባቴ በቤተክህነት የምመላለስባትን ሰአታት ለካ ታዝበውኝ ኖሩዋል አስጠርተው ያውቁኝ ስለነበር እዚህ ቢሮ የምትመላለሰው ምንድን ነው እኔ የምጨርስልህ እንደሆን እኔ ልጨርስልህ አለዚያ እዚህ ቢሮ እይገባህ እነዚህን ሰዎች ጉዳይህንም አይጨርሱልህም እነዚህ ሰዎች ደህንነት (ስለላ)ስራ ነው የሚሰሩት ካህናት አይደሉም ሊቄ ቢሮ ሄደህ አነጋግር ሁለተኛ ወደዚህ ቢሮ እንዳትገባ ብለው ከመለሱኝ ወዲህ አባ ፓውሎስ ለራሳቸውም ሆነ ለቤተክርስቲያኑዋ ክብር ደንታቢስ መሆናቸውን በሚገባ ተረድቻለሁ። ሰሞኑን አባቶቻችን ከወደ አዲስ አበባ መልካም ሀሳብ አንሰተው ውሳኔ አስተላልፈዋል ሲባል ደስታዬ ወሰን አልነበረውም መቼም ለሰላምና ለእርቅ የሚነሳን ኬየትኛውም ወገን ይሁን በርቱ ማለት በጸሎት መርዳት መደገፍ የክርስትና መርህ ነው እስከዚች ሰአት ግን በተለይ አባ ጳውሎስ ተነኩብን እያሉ ያሉ ቤተክርስቲያንት አሁንም በድፍረት ድምጻቸውን ማጥፋታቸው ያሳዝናል አባ ፓውሎስ ያላመኑበትን ድንጊያ (ጣኦት)መፍረስ እሰየው እልል ያስብል ነበር ፤ኢሳ/59/16/እግዚአብሄር አየ ፍርድም ስለሌለ ተከፋ ሰውም እንደሌለ አየ፤ አባቶቻችን ውሳኔ መተግብሩን አምላክ ይርዳችሁ ነው አለያ ዛሬ ይፍረስ ያላችሁት ድንጊያ ለከርሞ በርክቶ ይፍረሱ ይፍረሱ እንዳይሆን አንድ ድንጊያ ማንሳት ካልተቻለ እንደሚታየኝ ድንጊያዮ በርክቶ እንዳትችገሩ ወላዲት አምላክ ከናንተ ትሁን፤ ዘዳግም/ም/17/ቁ22/አምላክህ እግዚአብሄር የሚጠላውን ሀውልት ላንተ አታቁም፤
የቤተክርስትያናችንን አንድነት አምላክ ይጠብቅልን
ሰላምም በምድሪቱ ያምጣልን
ወንድወሰን ከሀገረ እንግሊዝ ተጻፈ/2010 ኦ7