”ሂሩት በቀለ ሞተች” የሚባለው ወሬ ሐሰት መሆኑ ተረጋገጠ
ለአዲስ ድምፅ ራዲዮ ቃለምልልስ ሰጠች
Ethiopia Zare (ሐሙስ ጥቅምት 25 ቀን 2003 ዓ.ም. November 4, 2010)፦ ”ታዋቂና ተወዳጅዋ አርቲስት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች” ሲል በአሜሪካን ሀገር የሚገኘው ”የሀገር ፍቅር ራዲዮ” ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 20 ቀን 2003 ዓ.ም. ያሠራጨውን ዘገባ ተከትሎ ወሬው ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ተዳርሶ ከፍተኛ ኀዘን በኢትዮጵያውን ዘንድ ተፈጥሮ ነበር። ዜናው ሐሰት መሆኑንና አርቲስቷ በሕይወት እንደምትገኝ ከአዲስ ድምፅ ራዲዮ ጋር ቃለምልልስ በማድረጓ ተረጋግጧል።