ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ፍኖተ ዴሞክራሲ ፍካሬ ዜና ህዳር 05 ቀን 2008 ዓ.ም. (November 15, 2015) # የውጪ ምንዛሪ እጥረት ከምን ጊዜውም በላይ እየተባበሰ መሆኑ ታወቀ፡፡ # የስንዴና ዘይት ርጭት ወራት ይፈጃል ተባለ # በረሃብ የተጠቁ ወገኖች ከአካቢባቸው እንዳይንቀሳቀሱ በፖሊስ እየታገዱ ነው # መዘዘኛው …

በረሃብ የተጠቁ ወገኖች ከአካቢባቸው እንዳይንቀሳቀሱ በፖሊስ እየታገዱ ነው:: የውጪ ምንዛሪ እጥረት ከምን ጊዜውም በላይ እየተባበሰ መሆኑ ታወቀ፡፡ Read more »

የመኢአድ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበረው አብርሃም ጌጡ በ5000 ሺህ ብር ዋሥ እንዲወጣ ፍርድ ቤቱ ወሠነ:: ያለ ምንም ማሥረጃ ከመንገድ ላይ ይዞ ማዕከላዊ ዘቅዝቆ ሲገርፍህ ይከርምና በ5000 ሺህ ብር ዋሥ ውጣ ይልሃል!!

የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) 1) የአልኮል መጠጥ አለመውሰድ ምክንያቱ የሰውነታችንን ካልሲየም መጠን ስለሚቀንስ 2) ሲጋራን ማጤስ ማቆም ምክንያቱ በደም ውስጥ የሚገኝን ካልሲየም መጠን እንዲሁ ስለሚቀንስ 3) ወተት እና የወተት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችን ማዘውተር 4) በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን …

የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

የአለም የጤና ድርጅት በኢትዮጵያ የተከሰተው የአየር ንብረት ለውጥ ለጤና ያሰጋል አለ::ድርጅቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በጤና ዙሪያ ለውጦችን ብታመጣም የተከሰተው የአየር ንብረት ለውጥ በዜጐቿ ህይወት ላይ የጤና ችግር ሊያመጣ እንደሚችል ተናግሯል፡፡ ድርጅቱ አክሎም አፋጣኝ …

በኢትዮጵያ የተከሰተው የአየር ንብረት ለውጥ ለጤና ያሰጋል :: (የአለም የጤና ድርጅት) Read more »

«ወያኔ» ብለው የሚጠሯት የዛፍ አይነት ለግጦሽ የሚጠቀሙት ሳር መሃል እየገባች ትበቅላለች፡፡ እሷ በበቀለችበት ቦታ ሁሉ ምንም ነገር አይበቅልም፤ ወይም ይደርቃል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በአፋር ክልል ስለተከሰተው ድርቅና ረሃብ፣ አቶ ሃሰን መሃመድ የተባሉ የክልሉ ነዋሪን በትላንትናው ምሽት አቅርበው ነበር፡፡ ጋዜጠኛዋ ጽዮን …

የረሃቡ እና የድርቁ ምክንያት የዝናብ እጥረት ብቻ ሳትሆን ወያኔ የምትባል አረም ናት ሲሉ የአፋር ነዋሪ ገለጹ Read more »

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለቤት አባት የሆኑት አቶ አሰፋ ሩዎ ሂወራ በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ነዋሪዎችን የቤት ካርታ በመቀበል በአመት ከ25 ሺ እስከ 30 ሺ ብር እንደሚከፍሉ አስታውቀው የባንክ ብድር ከወሰዱ በሁዋላ፣ ብድሩን ለመመለስ ሳይችሉ በመቅረታቸው የቤታቸውን ካርታ ያስያዙ ሰዎች ቤታቸው በሃራጅ ሊሸጥባቸው መሆኑን ተናግረዋል። ነዋሪዎች …

ወደ አውሮፓ ተሻግረው ለተሻለ ኑሮ በሚል ተስፋ ሰንቀው በሊቢያ ውስጥ የሚገኙ ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሊቢያ በከፍተኛ ችግር እና ሰቆቃ ውስጥ ናቸው ያለው የመንግስታቱ ማህበር ሕገወጥ የሰው ደላሎች ከፍተኛ ግፍ እየፈጸሙባቸው መሆኑን በአመታዊ ሪፖርቱ አስቀምጧል:: ሪፖርቱ እንዳለው ስደተኞች ጥገኝነት ፈላጊዎች …

ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች በሊቢያ ከፍተኛ ሰቆቃ ውስጥ ናቸው ሲል የመንግስታቱ ማህበር ገለጸ:: Read more »

ህወሓት ክፍፍልዋ በጣም ተባብሶ በረሃብ እየሞተ ያለው ህዝብ እስከ መርሳት ኣድርስዋታል። ከሶስት ሳምንት በላይ የዘለቀ ስብሰባ እያካሄዱ ለማመን የሚያስቸግሩ ወንጀሎች እንደተሰሩ እየሰማን ነው። ስለ ግምገማዎቹ ሌላ ቀን እመለስበታለው። ሰሞኑ ኣቶ ኣባይ ወልዱ ኣፅቢ፣ ሳዕሲዕ ፃዕዳእምባ፣ ኢሮብ በረሃብ የተጠቁ ወረዳዎች እየጎበኙ …

ህወሓት ክፍፍልዋ በጣም ተባብሶ በረሃብ እየሞተ ያለው ህዝብ እስከ መርሳት ኣድርስዋታል። Read more »

በቢቢሲ የቀረበችው ብርቱኳን አሊ በኢቢሲ(ኢቲቪ) እንድታስተባበል ተደርጋለች::ብርቱኳን አሊ ቢቢኤን አነጋግሯታል ቢቢኤን በዛሬው ሰኞ ህዳር 6/2008 ዝግጅታችን http://goo.gl/C2EOeQ ድምጻችን ይሰማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የወገኖቹን ህይወት ለመታደግ የመረባረብ ዜግነታዊ ብቻ ሳይሆን ሀይማኖታዊ ግዳጅም አለበት! በማለት መግለጫ አወጣ -በቢቢሲ የቀረበችው ብርኳን አሊ በኢቢሲ(ኢቲቪ) እንድታስተባበል …

በቢቢሲ የቀረበችው ብርቱኳን አሊ በኢቢሲ(ኢቲቪ) እንድታስተባበል ተደርጋለች ብርቱኳን አሊ ቢቢኤን አነጋግሯታል Read more »

የአዲስ አበባ መስተዳደር ‹‹ህዳር 18/2008 አልፏል›› በሚል የሰማያዊ ፓርቲን ደብዳቤ እንዳልተቀበለው ታወቀ ሰማያዊ ፓርቲ ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ለማድረግ በመብራት ኃይል አዳራሽ ህዳር 18/2008 ዓ.ም ስብሰባ እንደሚያደርግ ለአዲስ አበባ መስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የላከው ደብዳቤ ‹‹ቀኑ አልፎበታል›› በሚል …

የአዲስ አበባ መስተዳደር ‹‹ህዳር 18/2008 አልፏል›› በሚል የሰማያዊ ፓርቲን ደብዳቤ እንዳልተቀበለው ታወቀ Read more »

በሀገራችን የተከሰተውን ረሀብ ተከትሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የወገኖቹን ህይወት ለመታደግ የመረባረብ ዜግነታዊ ብቻ ሳይሆን ሀይማኖታዊ ግዳጅም አለበት ሲል ድምፃችን ይሰማ ገለጸ፡፡ በሀገራችን የተከሰተውን ረሀብ አስመልክቶ ከ‹‹ ድምፃችን ይሰማ›› የተሰጠ መግለጫ ድምፃችን ይሰማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የወገኖቹን ህይወት ለመታደግ የመረባረብ ዜግነታዊ …

በሀገራችን የተከሰተውን ረሀብ ተከትሎ ህይወት ለመታደግ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዜግነታዊ ብቻ ሳይሆን ሀይማኖታዊ ግዳጅም አለበት ሲል ድምፃችን ይሰማ ገለጸ፡፡ Read more »

የሌባ አይነ ደርቅ መልሶ ልብ ያድርቅ::በኢትዮጵያ ረሃብ አለ:: በኢትዮጵያ ድርቅም አለ::በድርቁም በረሃቡም የከፋ ሞት አለ::(ምንሊክ ሳልሳዊ) ‪#‎EthiopiaFamine‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ Minilik Salsawi – አባወራ አይውጣልሽ ተብላ የተረገመች ሴት ወይዘሮ ይመስል ሃገራችን በሰከሩ ፖለቲከኞች እየተናወጠች ነው::የወያኔ ባለስልጣናት እና ጭፍሮቻቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ …

የሌባ አይነ ደርቅ መልሶ ልብ ያድርቅ::በኢትዮጵያ ረሃብ አለ:: በኢትዮጵያ ድርቅም አለ::በድርቁም በረሃቡም የከፋ ሞት አለ::(ምንሊክ ሳልሳዊ) Read more »

መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም የስፖርት ዘገባዎች መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ ። [youtube http://www.youtube.com/watch?v=GtkHQNNs2kc]

ወያኔ ለረሃብ ዕርዳታ ሰብሳቢ እነ ብቻ ነኝ አለ::… የወያኔ ብአዴን ካድሬዎች ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኛነት ማቀንቀን ያስፈልጋል አሉ፤ ኢትዮጵያዊነት የሚመጣው ከብሔረሰብ መጠናከር በኋላ ነው ተባለ፤……. የአቃቂ ቃሊቲ ሕዝብና ምዕመናን የታቦት ማደሪያ ቦታው ይከበርልኝ እያለ ነው።……. የአይሲስ አሸባሪዎች በፓሪስ በተለያዩ ቦታዎች በሰነዝሯቸው ጥቃቶች …

የወያኔ ብአዴን ካድሬዎች ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኛነት ማቀንቀን ያስፈልጋል አሉ፤ ኢትዮጵያዊነት የሚመጣው ከብሔረሰብ መጠናከር በኋላ ነው ተባለ፤ Read more »

በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ አቃቤ ህግ የጠየቀው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ … አቃቤ ህግ የሽብርተኝነት ክስ መስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ተበይኖላቸው በነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የጠየቀው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ፡፡ ዛሬ …

በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ አቃቤ ህግ የጠየቀው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ Read more »

የማላዊ መንግስት ፖሊስ 20 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ይዞ አሰረ:: የማላዊ መንግስት የደድዛ አውራጃ ፖሊስ በሞዛምቢክ እና በማላዊ ድንበር ላይ በሕገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ገብተዋል ያላቸውን 20 ኢትዮጵያውያንን በመያዝ ማሰሩን አስታወቀ::በሕገወጥ መንገድ ማላዊ በመግባት ወደ ሞዛምቢክ ለማቋረጥ የሞከሩት እንዚሁ ኢትዮጵያውያን በእጃቸው ምንም …

የማላዊ መንግስት ፖሊስ 20 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ይዞ አሰረ:: Read more »

ኣሳ ዘይትን የመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) *በአየር ብክለት ምክንያት የሚመጡ ችግሮችን ይከላከላል በኦሜጋ 3 የበለፀው የአሳ ዘይት በአየር ብክለት ምክንያት ሊከሰቱ ከሚችሉ የልብና ተያያዥ ህመሞች የመከላከል አቅም አለው። *የመገጣጠሚያ ህመም ስሜትን ማስታገስ የመገጣጠሚያ ህመም ካለዎት ሁለት የሾርባ …

ኣሳ ዘይትን የመመገብ የጤና ጥቅሞች (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

Girma Bekele – የዛሬ መሪዎቻችን ማለትም የፖለቲካው ሞተር አንቀሳቃሾች ፣የፖለቲካ መኪናው መሪ ዘዋሪዎች ከ30 ዓመታት በፊት የነበረው ረሃብ (እንደዛሬው ከድርቅ የመጣው) ያስከተለውን የዜጎች ዕልቂት ለፖለቲካ ሥልጣን መወጣጫ መሰላል ማለትም- ለረሃቡ የመጣውን ዕርዳታ ለአቅም ግንባታ (መሳሪያ መግዢያና ሠራዊት መመልመያ)፣ ረሃቡን በ‹‹ገዢው …

ከአምባገነንነት ግርጃ በቀር ይህ ምን ሊባል ይችላል? Read more »

የዓለም የጤና ድርጅት በአዳጊ ሃገራት የሚገኙ 225 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች እርግዝና እንዳይከሰት ለማድረግ ወይም ለማዘግየት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን የወሊድ መከላከያ እንደማይጠቀሙ ያመለክታል።

ሀገራችን መሬት ላይ እንድ ሌላ ግዙፍ የርሀብና የችጋር ዳመና እያንዣበበ ነው። አንዳንድ ቦታም ግዳይ መጣል መጀመሩን እየሰማን ነው። ይህ ችግር በሰብዓዊ ዕውቀትና ሀይል የሚፈታ ሆኖ ለምንድነው እንዲህ እየተመላለሰ የሚጎበኘን? ሌሎች ሀገሮች ተመሳሳይ የአየር ሁኔታ ችግር እየገጠማቸው እንደኛ ለአዋራጅ ጉስቁልናና ልመና አልተዳረጉም። እኛ ጋ ምን የተሰወረብን ነገር አለ? የአፍሪካ የውሀ ሰገነት የምትባልና ከማንም የማይተናነስ የተፈጥሮ ጸጋ […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

የመልካም አስተዳደር መጓደል በልማት እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ ማነቆ ነው። ሕዝብንም የልማት ውጤት ተጠቃሚ እንዳይሆን ያደርጋል፣ በሚል ሕዝብ እና መንግሥት አዘውትረው በቅሬታ ሲናገሩ ይሰማል።

በሀገሪቱ የተከሰተውን ረሀብ በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ለዓለም ህዝብ ይፋ መሆኑን ተከትሎ መንግስት መረጃዎችን ለማፈንና ለመደበቅ እየሞከረ ነው። መንግስት ለክልል መንግስታትና በውጪ ሀገራት ላሉ ኤምባሲዎቹ ባስተላለፈው መመሪያ ረሀብ ወደ ተከሰተበት አካባቢ ጋዜጠኞች እንዳይሄዱ፣ የረድዔት ድርጅት ሰራተኞችም መረጃ እንዳያቀብሉ ብርቱ ጥረት …

ጋዜጠኞች ረሀቡን እንዳይዘግቡ ገደብ ተቀመጠ። Read more »

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለን ልዩነት “ጠባብ ነው” ማለታቸው እያነጋገረ ነው፡፡ፓትርያርኩ ይህን የተናገሩት ባለፈው ሳምንት በዓዲግራት ሀገረ ስብከት ተገኝተው የደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን በመረቁበት ወቅት ሲሆን በሥነ ሥርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል …

ፓትርያርኩ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከካቶሊክ ጋር ያለን ሃይማኖታዊ ልዩነት “ጠባብ ነው” ማለታቸው እያነጋገረ ነው Read more »

 ሰሞኑን ቢቢሲ በሰሜን ኢትዮጵያ ወሎ አካባቢ ተገኝቶ ድርቁ ባስከተለው ረሃብ ላይ ያቀረበው ዶክመንተሪ፤ በተለያዩ አለማቀፍ ሚዲያዎች አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተ ሲሆን መንግስት በድርቁ የሰው ህይወት አልፏል የሚባለውን አልቀበልም ብሏል፡፡ በ1977 ዓ.ም የተከሰተው አስከፊ ድርቅ የብዙዎችን ህይወት በቀጠፈበት ወሎ ቆቦ አካባቢ የቢቢሲው …

ቢቢሲ በኢትዮጵያ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ላይ ያቀረበው ዘገባ አነጋጋሪ ሆኗል Read more »

የፕላስቲክ ቱቦዎችንና መገጣጠሚያ ማሽነሪዎችን ለማስመጣትና በአገር ውስጥ ለመገጣጠም ከኢትዮጵያውያን ጋር ባለድርሻ በመሆን ያቋቋሙትን ኩባንያ መጠቀሚያ በማድረግ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤልሲ ከፍተው ካገኙት የውጭ ምንዛሪ ውስጥ ከ62.2 ሚሊዮን ብር በላይ በውጭ ባንክ በመደበቅ የተጠረጠሩ ሁለት የውጭ ዜጐች ተከሰሱ፡፡

 

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ክስ የመሠረተባቸው ተጠርጣሪ ተከሳሾች፣ በትውልድ አሜሪካዊና በዜግነት ደቡብ አፍሪካዊ መሆናቸው የተገለጸው ሚስተር ማይክል ማትሰንርና እንዲሁም ግብፃዊ መሆናቸው የተገለጸው ሚስተር አይመን አብድል ሞተልብ ሙሳ ኢሳ መሆናቸው በክሱ ተገልጿል፡፡

ግለሰቦቹ የተከሰሱት በከባድ የማታለል ወንጀልና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መሆኑንም ክሱ ይጠቁማል፡፡

ተከሳሾቹ ድርጊቱን እንዴት እንደፈጸሙት ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንደገለጸው፣ ኢትዮጵያውያንና ግብፃዊው ሚስተር አይመን በጋራ ባቋቋሙት ስታር ፓይፕና ፊቲንግስ ኩባንያ ውስጥ፣ ሚስተር ማትሰን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ይቀጠራሉ፡፡ ሚስተር አይመን ለብቻቸው ያቋቋሙት ጎልደን ትሬዲንግ ከሚባለው ኩባንያ በተጨማሪ ከሚስተር ማትሰን ጋር በጋራ ያቋቋሙት በዱባይ የሚገኝ ዋሶ ቴክኖሎጂ ግሩፕ የሚባል ኩባንያ አላቸው፡፡ በመሆኑም ተከሳሾቹ ከህንድና ከቻይና ወደ አገር ውስጥ እንደሚያስገቡ የገለጹትን የፕላስቲክ ቱቦና መገጣጠሚያ ማሽነሪዎችን፣ በኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ለማጓጓዝ የተለያየ መጠን ያለው ዶላር ለማስጫኛ በመክፈል ዕቃዎቹን እንዳስገቡ መግለጻቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ 

ተከሳሾቹ ከቻይናና ከህንድ ከ2004 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ በኢትዮጵያ ንግድ መርከብ እያስጫኑ ዕቃውን ሲያስገቡ፣ ለማስጫኛ ያልተከፈለውን የገንዘብ መጠን፣ በሐሰተኛ የማስጫኛ ደረሰኝና የንግድ ሽያጭ ደረሰኝና በሐሰተኛ ማኅተም ተጠቅመው ወንጀሉን እንደፈጸሙ የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ በቻይና የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ወኪል የሆነው ‹‹የቻይና የውቅያኖስ አጓጓዥ ኤጀንሲ ሻንጋይ›› የሚል ሐሰተኛ የጭነት ደረሰኝ በማዘጋጀት፣ ‹‹የመጫኛ መነሻ ወደብ ሻንጋይ ቻይና፣ ጭነት ማራገፊያ ጂቡቲ የባህር ወደብ፣ መድረሻ ሞጆ ደረቅ ወደብና አጓጓዥ የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ›› የሚል ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው የተለያየ መጠን ያለው ዶላር እንደተከፈለ በማስመሰል፣ ጠቅላላ ድምሩ 62,278,179 ብር ዱባይ ሚስተር ማይክልና ሚስተር አይመን በጋራ በዱባይ ማሽሩክ ባንክ በከፈቱት ‹‹ዋሶ ቴክኖሎጂ ግሩፕ›› ተብሎ በሚጠራው ድርጅታቸው አካውንት ውስጥ እንዲገባ ማድረጋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ የተጠቀሰውን ያህል ገንዘብ ዱባይ በሚገኘው የድርጅታቸው አካውንት ማሽሩክ ባንክ ያስገቡት፣ ለምሳሌ ዕቃውን ያስጫኑት በ19,000 ዶላር ከሆነ ኤልሲ ከፍተው የውጭ ምንዛሪ ከጠየቁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ በሚያቀርቡት ሐሰተኛ ሰነድ 40,000 ዶላር እየተቀበሉ፣ ልዩነቱን ለግላቸው ማድረጋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ 

ቻይናና ህንድ ውስጥ ላለው ስታር ፓይፕና ፊቲንግስ ፋብሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሲላክ ‹‹የተመረተበት አገር ቻይና፣ ለማሽነሪው ለአንዱ ብቻ የተከፈለ 385,370 ዶላር›› በማለትና ትክክለኛ ምርት ለማስመሰል ‹‹በስቴት ኦፍ ቴክሳስ ንግድ ምክር ቤት የተረጋገጠ›› የሚል ሐሰተኛ ሰነድ ማኅተም ተደርጐበት እንደቀረበ ክሱ ይገልጻል፡፡

በስቴት ኦፍ ቴክሳስ ንግድ ምክር ቤት በተመዘገበው የቻይና ኩባንያ የተመረተ እውነተኛ ምርት ለማስመሰል፣ ተከሳሾቹ ዋሶ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ፕሮፎርማ ሰብስቦ እንዳረጋገጠ የሚያሳይ የንግድ ደረሰኝ በማቅረብ፣ እውነተኛ አስመስለው በሐሰተኛ ሰነድ እየተገለገሉ፣ ከዘጠኝ ጊዜያት በላይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሪ በመውሰድ የተጠቀሰውን ገንዘብ ዱባይ ወደሚገኘው አካውንታቸው ለማሸሽ መቻላቸውን ክሱ ያብራራል፡፡

ተከሳሾቹ ‹‹ለኢትዮጵያ ንግድ መርከብ በቻይና ውቅያኖስ ጉዞ ኤጀንሲ የተከፈለ የውጭ ምንዛሪ›› በማለት በሐሰት ባዘጋጁት የተለያየ ሰነድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያወጡትን የውጭ ምንዛሪ፣ ወደ ዱባይ ማሽሩክ ባንክ በመላክ ከባድ የማታለል ወንጀል መፈጸማቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ሚስተር ማትሰን በቁጥጥር ሥር ሲሆን፣ በዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠትና የክሱን ሒደት ለማስቀጠል ለኅዳር 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ተቀጥሯል፡፡ ሚስተር አይመን ሊገኙ ባለመቻላቸው በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ተሰጥቶ ለመጠባበቅ ለታኅሳስ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

ከሁለቱ የውጭ ዜጎች ጋር ክስ የተመሠረተባቸውና በ100,000 ብር ዋስ በውጭ ሆነው ክሳቸውን እንዲከታተሉ ትዕዛዝ የተሰጠባቸው ደግሞ አቶ ወሰንዓለም ገብረ እግዚአብሔር ይባላሉ፡፡

አቶ ወሰንዓለም የተጠረጠሩት ሚስተር ማትሰን የስታር ፓይፕና ፊቲንግስ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሳሉ፣ ከድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ ውጪ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ካስቀመጠው ገንዘብ ውስጥ፣ ሦስት ሚሊዮን ብር ‹‹ለሚመለከተው ሁሉ›› ተብሎ በተሰጣቸው ውክልና በድርጅቱ ስም በማውጣታቸው መሆኑን ክሱ ያብራራል፡፡ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት በሌላ ሰው ጥቅም ላይ የሥራ አመራር ጉዳት ማድረስ ወንጀል መከሰሳቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያብራራል፡፡     

 

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባባሪያ ቢሮ (OCHA) የአስቸኳይ መልስ ፋንድ ክፍል ሰርፍ (CERF) ለኢትዮጵያ ከገጠሙት ሁሉ የከፋ በሆነ ድርቅ ለተጎዱ ማህበረሰቦች የአስራ ሰባት ሚሊዮን ዶላር አስቸኩዋይ ርዳታ ትናንትና ሰጠ።

የወተቱ እንቆቅልሽ

አቶ ደረጀ ዳዲ በሰንዳፋ ከተማ ወተት አምራች ነው፡፡ የራሱን ብቻም ሳይሆን ከአካባቢው ገበሬዎች እየሰበሰበ አዲስ አበባ አምጥቶ ለአከፋፋዮች ያስረክባል፡፡ በቀን እስከ 800 ሊትር ወተት ያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ በቅርቡ የዓለም አቀፍ

የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት (IRLI) ጥናትን በመጥቀስ በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ ከተሞች በተሰበሰቡ ወተቶች ውስጥ አፍላቶክሲን የተሰኘ ኬሚካል መገኘት በመገናኛ ብዙኃን በመዘገቡ ምክንያት፣ ትልቅ ኪሳራ እንደደረሰበት አቶ ደረጀ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ በዚህም በአሁኑ ወቅት በቀን ከ300 ሊትር በላይ ማቅረብ አልቻለም፡፡ በወተት ውስጥ ለአፍላቶክሲን መገኘት ምክንያት የሆነው የሻገተ ፋጉሎ መሆኑ በጥናቱ ቢጠቀስም፣ ሪፖርተር በተለያዩ የሰንዳፋ ከተማ ወረዳዎች ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ወተት አምራቾች ፋጉሎን ለመኖነት መጠቀም ካቆሙ ዓመታት መቆጠራቸውን ገልጸዋል፡፡ ከኑግ ዘይት ሲጨመቅ ተረፈ ምርት የሆነው ፋጉሎ ዋጋ በኩንታል 800 ብር መሆኑም፣ ከዋጋ አንፃር ተመራጭ እንደማያደርገውም ያስረዳሉ፡፡ በበረህ ወረዳ ከዳቤ ቀበሌ ወተት አምራች የሆነው አቶ ይገዙ አሰፋም የአፍላቶክሲን መገኘት ዜና በእጅጉ ገቢያቸውን እንደጐዳው ገልጿል፡፡

ባለፈው ሳምንት ተቀባዮች ሙሉ በሙሉ ወተት እንዳልተረከቡት ይናገራል፡፡ እሱም በአካባቢው ፋጉሎን ለእንስሳት መኖ ጥቅም ላይ እንደማይውል፣ ይልቁንም ቢሾፍቱ ከተማ ከሚገኝ ዓለማ ካውዳይስ የእንስሳት መኖ ከተሰኘ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመጣጠነ መኖ እየገዙ እንደሚጠቀሙ አስረድቷል፡፡ በበረህ ወረዳ ግራር ቀበሌ ኗሪና ለሰንዳፋ አካባቢ የእንስሳት መኖ አቅራቢና ወተት አምራች የሆነው አቶ ተሾመ መንግሥቱም፣ በአካባቢው ፋጉሎን ለመኖነት እንደማይጠቀሙ ይናገራል፡፡ እሱም በቀን እስከ 160 ሊትር ወተት ያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፈው ሳምንት ምንም ተረካቢ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡ በወተት ንግዳቸው ላይ እንደዚህ ያለ ኪሳራ ያስከተለው መረጃ ትክክል አለመሆኑ በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙኃን ቢገለጽም፣ ብዙም የተቀየረ ነገር እንደሌለ አምራቾቹ ሪፖርተር ባነጋገራቸው ወቅት ገልጸዋል፡፡

ምርምሩ የተካሄደው ከአዲስ አበባ፣ ከቢሾፍቱ፣ ከሰበታ፣ ከሰንዳፋና ከሱልልታ ከተማ በተወሰዱ የወተት ናሙናዎች ላይ ሲሆን፣ አፍላቶክሲን በወተት ናሙናዎቹ ውስጥ (0.41 ማይክሮ ግራም በሊትር) መገኘት ዜና በኋላ ለወትሮ የወተት ገበያ ግርግር በነበረበት ሰንዳፋ ከተማ፣ ገበያው እረጭ ማለቱን ሪፖርተር በከተማው ተዘዋውሮ ካነጋገራቸው አምራቾች ማረጋገጥ ችሏል፡፡ አምራቾቹ ወጣ የተባለው ምርምር ገበሬውን ክፉኛ የጐዳ፣ በአገር ሀብት ላይም ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ በመሆኑ ነገሮች ወደነበሩበት ይመለሱ ዘንድ መንግሥትና የሚመለከታቸው ሁሉ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ጥናቱን በሚመለከት የመንግሥትንና ጥናቱን የሠራው የዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት አስተያየትን፣ እንዲሁም መንግሥት የወሰዳቸውን ዕርምጃዎች በሚመለከት የተጠናቀረው ዘገባ በማኀበራዊ ገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡ (በዘገባው ሚሊ ግራም ተብለው የተቀመጡት መለኪያዎች ማይክሮ ግራም ተብለው እንዲነበቡ የዝግጅት ክፍሉ ያሳስባል)   

 

በ50 ሺሕ ብር ዋስ ይፈቱ የተባሉት መምህር ግርማ ይግባኝ ተጠየቀባቸው

በተጠረጠሩበት ሐሰተኛ ሰነድ መጠቀም ወንጀል ተጨማሪ ጊዜ ተጠየቀባቸው

የእሳቸው ተከታይና የሚሏቸውን ነገር ሁሉ ያደርጉ የነበሩን ግለሰብ ቤት በማሸጥና ገንዘቡንም እንዲፀለይበት በማለት ወስደዋል ተብለው ተጠርጥረው የታሰሩት መምህር ግርማ ወንድሙ፣ በ50,000 ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ፖሊስ ይግባኝ ማለቱ ታወቀ፡፡ 

የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ለመምህር ግርማ የፈቀደውን የ50,000 ብር ዋስትና የተቃወመው ፖሊስ፣ ቅሬታውን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት አቅርቧል፡፡ ፖሊስ ባቀረበው መከራከሪያ ነጥብ ላይ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለኅዳር 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

ተጠርጣሪው ሐሰተኛ ሰነድ መጠቀማቸውን ገልጾ ፖሊስ ባቀረበው ክስ ምክንያት መምህር ግርማ ኅዳር 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን፣ እሳቸው ከቤተክህነት እንደተሰጣቸው የገለጹት ሰነድ በፎረንሲክ ተመርምሮ ሐሰተኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ሌላ ተጨማሪ የሚመረመር ሰነድ እንዳለውና ተጨማሪ ሰነድ ሰጥተዋል የተባሉት የቤተ ክርስቲያን አባት በአገር ውስጥ አለመኖራቸውን በማስታወቅ፣ ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ 

የመምህር ግርማ ጠበቆች ፖሊስ ያቀረበውን ማመልከቻና ተጨማሪ ቀናት በመቃወም፣ ደንበኛቸው በዋስ ተለቀው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የጠበቆቹን ማመልከቻ በማለፍ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ለፖሊስ ፈቅዷል፡፡ 

 

አርሶ አደሩን በመግደል የተጠረጠረው ፖሊስ መሰወሩ ተጠቆመ

‹‹መያዣ አውጥተን እያፈላለግነው ነው›› ፖሊስ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰያን ደብር ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ፣ በአካባቢው የተመደበ ፖሊስ አርሶ አደሩን ገድሎ መሰወሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ሟች አርሶ አደር ጌቱ ዘውገ የሚባል የ27 ዓመት ወጣት መሆኑን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ለመሞቱ ምክንያቱ የሆነው ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ከአንድ ሌላ አርሶ አደር ጋር በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተጋጩበት ምክንያት ባይታወቅም ሟች አቶ ጌቱ ከአንድ የአካባቢው ሰው ጋር ሲጣላ የአካባቢው ነዋሪዎች ገላግለዋቸው ወደየቤታቸው የሄዱ ቢሆንም፣ በአካባቢው ግጭት እንደነበር ሪፖርት የደረሰው ተጠርጣሪ ምክትል ሳጅን ግርማ ብርሃኑ፣ ወደ  ሟች ቤት መምጣቱን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ ተጠርጣሪው ምክትል ሳጅን ግርማ ሟችን ይጠራና ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዞት ለመሄድ በመነጋገር ላይ እያሉ ሌሎች ሁለት ፖሊሶች ይደርሳሉ፡፡ አንዱ ፖሊስ ሟች ላይ ድብደባ እየፈጸመበት እያለ፣ ምክትል ሳጅኑ በያዘው ክላሽኒኮቭ ጠመንጃ ተኩሶ እንደገደለው የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል፡፡

በወቅቱ በተፈጠረው ግርግር ተጠርጣሪውን ማንም ሊይዘው እንዳልቻለና ወደ ላይ እየተኮሰ ከአካባቢው መሰወሩን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ በመተባበር በሟች ላይ ድብደባ የፈጸመበት ሌላው ፖሊስ መያዝና በሕግ መጠየቅ ሲገባው፣ ከአካባቢው ዞር ተደርጎ ሌላ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር መመደቡ የአካባቢውን ነዋሪዎች እንዳስቆጣ ተናግረዋል፡፡ ሟች በቅርቡ ትዳር የያዘ መሆኑንና ቤተሰቡን እንደሚረዳ፣ በአካባቢው ተወዳጅ ወጣት አርሶ አደር እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፣ በቤተሰቦቹ ፊት በጠራራ ፀሐይ ገድሎት የተሰወረውን የፖሊስ ባልደረባ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ለሕግ እንዲያቀርቡት ጠይቀዋል፡፡

በአርሶ አደሩ ላይ ተፈጽሟል ስለተባለው የግድያ ወንጀል ማብራርያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደነባ ወረዳ ፖሊስ መምርያ ኃላፊ ኢንስፔክተር መስፍን ደጉ ግድያው መፈጸሙን አረጋግጠዋል፡፡ ወንጀሉ እንደተፈጸመና ተጠርጣሪው ምክትል ሳጅን ግርማ ብርሃኑ ግን እንዳልተያዘ የገለጹት የመምርያ ኃላፊው፣ ፖሊስ ምርመራውን ጨርሶ መያዣ በማውጣት ተጠርጣሪውን ለመያዝ እየሠራ መሆኑንና ከኅብረተሰቡ ጋር ተባብረው በቅርቡ በቁጥጥር ሥር እንደሚያውሉት ተናግረዋል፡፡

ግድያው የተፈጸመው በሁለት ግለሰቦች መካከል በተነሳ ፀብ ምክንያት መሆኑን በተደረገው ምርመራ መረጋገጡን የገለጹት ኢንስፔክተሩ፣ ሟች ለሕግ አልገዛም በማለት በፖሊሶች ላይ ዕርምጃ ሊወስድ ሲል ግድያው ሊፈጸም እንደቻለ መረጃ ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የአካባቢው ፖሊስና ነዋሪዎች ተስማምተውና ተከባብረው እንደሚኖሩ የገለጹት የመምርያ ኃላፊው፣ አንዳንድ ጊዜ ሳይታሰብ ወንጀል የሚፈጸም በመሆኑ ፈጻሚውን በሕግ ፊት ማቅረብ ግድ ስለሆነ፣ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ተጠርጣሪውን ይዞ ለማቅረብ አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 

 

“ሃብት ያለው ሰው አይታሰርም። ተፈርዶባቸው እስር ቤት ያሉ ባለ ሃብት መንገድ ላይ ሲሄዱ ሌላ ሰው ገጭተው ሌላ ክስ ተመሠረተባቸው። አቃቤ ሕግ ምሥክር ማስፈራራት የሃሰት መረጃ ማስጠናት። በጥናቱ ካገኘናቸው ውስጥ ናቸው።” አቶ ተካ ገብረ የሱስ፤ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዲሬክተር።

ከልክ ያለፈ ላብ (ሃይፐርሃይድሮሲስ) (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) ከልክ ያለፈ ላብ ከእጅ፣ከእግር፣ከብብት እና ፊት አካባቢ በመመንጨት ሙሉ ሰውነትን በላብ እንዲዘፈቅ ያደርጋል። በዚህ ችግር የሚጠቁ ሰዎች መጠነኛ የሚባል የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ለማድረግ እስኪቸገሩ ድረስ በከባድ ላብ ይዘፈቃሉ። ከዚያም ባለፈ ለማህበራዊ ችግሮችና …

ከልክ ያለፈ ላብ (ሃይፐርሃይድሮሲስ) (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

Minilik Salsawi – አንድ – ለፓሪሱ ጥቃት አስለቃሽ የተቀጠሩ ይመስል የወያኔ ካድሬዎች ሙሾውን ተያይዘውታል::የኢትዮጵያ ረሃብ ሕዝብን እየገደለ እያሳደደ ባለበት በዚህ አደገኛ ጊዜ ላይ የድርጊት መረሃ ግብሮች ሁሉ ሕዝብን ለማዳን መረባረብ በሚጠበቅበት ወቅት የፓሪሱን ጥቃት እንደ አጀንዳ ይዞ ማራገብ አገዛዙ ምን …

ለራስዋ ያላወቀች ለቅዱስ ገብርኤል መድሃኒት ጠየቀች::የፓሪሱን ጥቃት የረሃቡን ጉድ ለመሸፈን አጀንዳ ማድረግ ዝቅጠት ነው:: Read more »

በትላንትናው እለት በገለፅነው መሰረት በሀገራችን በተከሰተው ቀውስ (ድርቅ/ርሃብ) ዙሪያ ‹‹ያገባኛል!›› የምንል ዜጎች በበጎፈቃደኝነት ኮሚቴ አቋቁመናል፡፡ ዛሬ ባደረግነው አስቸኳይ ስብሰባ የተገኙ 13 ሰዎች የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡ 1. ሁላችንም እንደዜጋ ከራሳችን በመጀመር ሚናችንን መወጣት ይኖርብናል፡፡ በዚህም መሰረት ከእያንዳንዳችን በነፍስ ወከፍ በትንሹ ከ100 …

‹‹ቤዛ እንሁን!›› ወገን ተርቧል፤ እንድረስለት! የበጎ ፈቃደኝነት ኮሚቴ ተቋቋመ:: Read more »

ቃር የምንለው ወይንም በህክምና አጠራሩ ሃርትበርን (Heartburn) በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት ሲሆን አብዛኞችን የሚያጠቃ እና እጅግ የተለመደም ችግር ነው። በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት መሰማት በአብዛኛው ከምግብ በኃላ እና እንቅልፍ ስንተኛ የሚብስ ነው። ይህም የሚከሰተው የጨጓራ ውስጥ አሲድ ወደ ላይኛው የምግብ …

ቃር (Heartburn) (በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር) Read more »

“ሬድ ቡል”ን የመሳሰሉ ሃይል ሰጪ መጠጦች በተለይ ከአልኮል መጠጥ ጋር ተደባልቀው ሲጠጡ የጤና ችግር ሊያስከትሉ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ፡፡በአውሮፓ የተደረገ ጥናት እንዳረጋገጠው፣ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ እድሜያቸው ከ18-29 ዓመት የሚደርሱ ወጣቶች፣ እንደ “ሬድ ቡል” ያሉ ሃይል ሰጪ መጠጦችን …

ሃይል ሰጪ መጠጦች በተለይ ከአልኮል መጠጥ ጋር ተደባልቀው ሲጠጡ የጤና ችግር ያስከትላሉ ተባለ Read more »

    በቅርቡ የተቋቋመው የኩላሊት እጥበት ማዕከል፣ ለኩላሊት ሕመምተኞች የእጥበት ህክምና ለመስጠት በኤስ ኤም ኤስ እያሰባሰበ ያለው ገንዘብ፣ “ለታለመለት ዓላማ አልዋለም”፤ መባሉ እያወዛገበ ነው፡፡ ባለፈው አርብ ጥቅምት 26 ሬዲዮ ፋና ባስተላለፈው ዘገባ፣ ማዕከሉ ለኩላሊት ህመምተኞች የእጥበት አገልግሎት ለመስጠት ከህዝብ ከሚሰበሰበው የበጐ አድራጐት ገቢ፣ ኮሚሽን እየከፈለ መሆኑን ጠቅሶ ድርጊቱ ህገወጥ ነው ብሏል፡፡ 524 ሺህ ብር ኮሚሽን ተቀብያለሁ ያሉ ግለሰብም በዋቢነት ማቅረቧ ታውቋል፡፡ የማዕከሉ የቦርድ አባልና የገቢ አሰባሳቢ ኦፊሰር ደራሲና ዳይሬክተር አንተነህ ሃይሌ በበኩሉ፤ “የኩላሊት እጥበት ማዕከሉ በSMS ከህዝብ ከሰበሰበው 7 ሚሊዮን ብር ውስጥ 4 ሚሊዮን ብር ተመዝብሯል የሚል ዘገባ በሬዲዮ ፋና መሰራጨቱን ጠቁሞ፤ 7 ሚ. ብር የሚለውን ከየት አምጥቶ እንዳወራ አናውቅም ብሏል፡፡ “የፋና ሃሰተኛ ዘገባ የህዝቡን በጐነት የሚረብሽና የህሙማንን ህልም የሚያጨልም ነው፤” ሲልም ተችቷል፡፡“የፋና ዘገባ እውነትን ማዕከል ያደረገ አይደለም፤” ያሉት የማዕከሉ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ሳሙኤል ይርጋ፤ “ለሚሠራው ሥራ የሚከፈል ኮሚሽን የለም” ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ማዕከሉ ከገራዶ ፊልም ፕሮዳክሽን ጋር ስለፈጸመው የሥራ ውል የተጠየቁት ሰብሳቢው፣ “ማዕከሉ ሥራ ሲጀምር ምንም ገንዘብና የሰው ሃይል ስላልነበረው የኤስኤምኤሱን አጠቃላይ ሥራ እንዲያከናውንና ለእድለኞች ሽልማት ከገቢው ከ10 በመቶ ያልበለጠ ሒሳብ እንዲወራረድለት ውል ፈጽመናል” ብለዋል፡፡ እያንዳንዱም ወጪ በደረሰኝ እንደሚገባና እንደሚወጣ ከቀሪው ጋር የሚያሳይ የባንክ ስቴትመንት እንዳለ ገልፀዋል፡፡ ሬዲዮ ፋና ያለ መረጃ ያሰራጨውን ዜና በተመለከተ፣ ይቅርታ እንዲጠይቀን ደብዳቤ አስገብተናል – ብለዋል ሰብሳቢው፡፡

ፓትርያርኩ ከካቶሊክ ጋር ያለን ሃይማኖታዊ ልዩነት “ጠባብ ነው” ማለታቸው እያነጋገረ ነው

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለን ልዩነት “ጠባብ ነው” ማለታቸው እያነጋገረ ነው፡፡ፓትርያርኩ ይህን የተናገሩት ባለፈው ሳምንት በዓዲግራት ሀገረ ስብከት ተገኝተው የደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን በመረቁበት ወቅት ሲሆን በሥነ ሥርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ተስፋ ሥላሴ መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡
ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ፣ “ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጋር  ያለንን ጠባብ የሃይማኖት ልዩነት ጠብቀን፣ በዜግነታችንና በክርስቶስ ልጅነታችን በዋና ዋና የልማት ሥራዎች ዙሪያ በጋራ በመሥራት፣ ለክርስቶስም ለሰው ልጅም ደስታን የሚሰጥ አገልግሎት ማበርከት  ይጠበቅብናል፤” ብለዋል – ድረ ገጹ እንደዘገበው፡፡ይሁንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ያላቸው የእምነትና የሥርዓት አስተምህሮ ልዩነት መሠረታዊ መሆኑን የጠቀሱ አስተያየት ሰጪዎች፣ ፓትርያርኩ ሃይማኖታዊ ልዩነቱ ጠባብ እንደሆነ ተናግረዋል ተብሎ በሰፈረው ዘገባ ግር መሰኘታቸውን ጠቁመዋል፡፡

   በስፔናዊው ሚጌል ሊያንሶ ተፅፎ የተዘጋጀውና ከ60 በላይ በሚሆኑ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተሳትፎ፣ 10 ሽልማቶችን ያሸነፈው “Crumbs” (ስብርባሪ) የተሰኘው ሳይንሳዊ ልብወለድ ፊልም፤ ትላንት ምሽት በአቤል ሲኒማ ተመረቀ፡፡ ከዓለም ጦርነቶች ፍፃሜ በኋላ ምን ሊፈጠር እንደሚችል በሚያመለክተው በዚህ ፊልም ላይ ዳንኤል ታደሰ (ጋጋኖ) በመሪ ተዋናይነት የተጫወተ ሲሆን ባሳየው የትወና ብቃትም አድናቆት ተችሮታል ተብሏል፡፡ ለትወናው አምስት ሺህ ዩሮ (125ሺ ብር) እንደተከፈለው ጋጋኖ ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡ ፊልሙ በአውሮፓና በአሜሪካ በተለያዩ ከተሞች ለእይታ ቀርቦ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን ከ60 በላይ ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተሳትፎ፣ ከ10 በላይ ሽልማቶችን ማግኘቱን የፊልሙ ፕሮዲዩሰር አርቲስት ዮሐንስ ፈለቀ ገልጿል፡፡ “ክረምብስ” ፊልምን፣ ለመስራት 200ሺ ዶላር እንደፈጀ ተናግሯል፡፡   

መንግስት በስልጤ ዞን እየፈፀመ ያለው የሂጃብ ገፈፈ በመቃወም በዛሬው እለት በሻሸመኔ ከተማ ተቃውሞ ተካሄደ። በዛሬው እለት በነበረው ተቃውሞ የመንግስትን በሃይማኖት ጣልቃ ገብነትና የሂጃብ ገፈፋ ተቃውመዋል። ዝርዝሩን በምሽት ዝግጅታችን ቢቢኤን ይዞ የሚቀርብ ይሆናል። ድምፃችን ይሰማ እየተደረጉ ያሉ የሂጃብ ገፈፋና ብሄራዊ ጭቆናንን …

በስልጤ ዞን እየፈፀመ ያለው የሂጃብ ገፈፈ በመቃወም በዛሬው እለት በሻሸመኔ ከተማ ተቃውሞ ተካሄደ። Read more »

‹‹ርሃቡን ያመጣው የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ነው!›› • ‹‹ለመፍትሄው መረባረብ አለብን›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ የሰጡት አስተያየት ‹‹የርሃቡ የቅርብ ጊዜ ምክንያቱ የዝናብ እጥረት ነው፡፡ የዝናብ እጥረት ድርቅን እስከተለ፡፡ ርሃቡን ያመጣው ግን የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ነው፡፡ የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ለረዥም ጊዜ፣ …

‹‹ርሃቡን ያመጣው የኢህአዴግ የስልጣን ስስት ነው!›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት Read more »

አቦ አታድርቁና! ስንቱን ነገር ፈትፍተን አጉርሰናችሁ እንችለዋለን?! ‘ድርቁን ፖለቲሳይዝ አታድርጉት’ ከመባባል በፊት ቁጥር ቅነሳውን ምን አመጣው? ያው ፖለቲሳይዝድ የሆነ ነገር ስለሆነ አይደል? ድርቅ (drought) የዝናብ መቅረት እንጂ የምግብ መጥፋት (famine) አይደለም። በትክክለኛ ትርጓሜው ሲታይም፥ መንግስት ሕዝብን እንዲያገለግል የሚሾም፣ አስተናባሪ እንጂ …

‘ድርቁን ፖለቲሳይዝ አታድርጉት’ ከመባባል በፊት ቁጥር ቅነሳውን ምን አመጣው? Yohanes Molla Read more »

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በያዝነው አመት አጋማሽ 15 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ መንግስት በበኩሉ 8.2 ሚሊዮን ህዝብ እንደተራበ አምኗል፡፡ ሰሞኑን ቢቢሲ በሰራው ዘገባ በርሃቡ ምክንያት በየቀኑ 2 ህፃናት እየሞቱ እንደሆነ ገልፆአል፡፡ ለተራቡት ዜጎች እርዳታ ባለመድረሱ በርካቶች ወደ …

ለተራቡት ዜጎች እርዳታ ባለመድረሱ በርካቶች ወደ ከተሞች እየተሰደዱ ነው፡፡ Read more »

ኀዳር ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለስድስት ከፍተኛ ጡረተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለእያንዳንዳቸው በ25 ሚሊየን ብር ወጪ በስጦታ የሚለገሳቸው የመኖሪያ ቤት እየተገነባ መሆኑ ሰሞኑን በመገናኛ ብዙሃን ይፋ ከሆነ በሁዋላ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡ በተለይ በረሃብ ምክንያት ከ 15 ሚሊየን ያላነሱ ወገኖችን ችግር ላይ በወደቁበት፣ በከተሞች አካባቢ ከፍተኛ ኑሮ ውድነትና የስራ …