ሩስያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ግብፅ ውስጥ የሚገኙ 11,000 ሀገር ጎብኚ ዜጎቿን አስወጣች። ዛሬ እሁድም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አርካዲ ድዎርኮቪችን ዋቢ አድርጎ የሩሲያ ዓለም አቀፍ የዜና ኤጀንሲ (RIA) ዘግቧል።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የሃገሪቱ ዘለቄታዊ የኢኮኖሚ ጥቅሞች በባዶ ካዝናዎች ተተክተዋል ይላል ከባንኮች አከባቢ የሚወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት በላኪነት ስራ ላይ በብዛት ተሰማርተው የሚገኙት የገዢው መደብ ባለስልጣናት እና ዘመድ አዝማዶቻቸው እንዲሁም በጥቅም ትሥሥር ላይ የተለጠፉ አቆርቋዥ ነጋዴዎች ንግድን ሽፋን በማድረግ …

የባንክ ባለሙያዎች ከውጪ ምንዛሬ ጋር በተያያዘ ሐገሪቷ አደጋ ውስጥ ናት ይላሉ:: (ምንሊክ ሳልሳዊ) – Read more »

በከፍተኛ ድርቅ ተመትተው ነዋሪዎቻቸው ክፉኛ ለጠኔ ተጋልጠው የሚልሱት የሚቀምሱት በማጣታቸው ከሞት አፋፍ ላይ ሆነው የሚገኙባቸው አምስቱ ቀበሌዎች ጨጨሆ፣ ፈንጠርያ፣ ቀንጠብጣ፣ አይጠላ እና እንድ ሌላ ለጊዜው ስሙን ያላወቅነው ቀበሌ ናቸው፡፡ በሰሜን ጎንደር የወገራ ወረዳዎቹን ሶሚያ፣ ጓሪ፣ ግጭሆ እና ቧግሽ የተባሉትን አራት ቀበሌዎች ጨምሮ እስካሁን ዘጠኝ ቀበሌዎች ክፉኛ በድርቅ ተመትተው ከ50ሺህ እስከ 60 ሺህ ህዝብ ተርቦ የስደትና […]

አቶ ጋሻው ደበበ

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ቦርድ፣ የንግድ ምክር ቤቱን ዋና ጸሐፊ ከሥራ እንዲታገዱ ወሰነ፡፡

ዘጠኝ አባላት ያሉትና በአቶ ሰለሞን አፈወርቅ የሚመራው የንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ፣ ዋና ጸሐፊው አቶ ጋሻው ደበበ ከኃላፊነታቸው እንዲታገዱ ውሳኔ ያሳለፈው ባለፈው ሐሙስ ጥቅምት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. እንደሆነ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ቦርዱ በዋና ጸሐፊው ላይ የዕገዳ ዕርምጃውን የወሰደበት ዋነኛ ምክንያት ግልጽ ባይሆንም፣ ከሥራ የታገዱ መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ በንግድ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት በኩል ተፈርሞ እንዲደርሳቸው ቦርዱ ከስምምነት ላይ መድረሱ ታውቋል፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ወገኖች እንደተሰማው፣ በቦርዱና በዋና ጸሐፊው መካከል ከዚህም ቀደም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ አለመግባባቶች ነበሩ፡፡ በዚህም ምክንያት እንዲህ ያለው ዕርምጃ ይጠበቅ ነበር ይላሉ ምንጮች፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞም ቦርዱ በንግድ ምክር ቤቱ ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ አሉ የሚባሉ ችግሮችን ሲያሰባስብ እንደነበር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በተለይ ንግድ ምክር ቤቱ በቅርቡ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ዕውቅና በሰጠበት ፕሮግራም ላይ ታየ የተባለው የፕሮግራም መፋለስና ጉድለት፣ የቦርድ አባላቱን አስቆጥቶ ነበር ተብሏል፡፡ በዚህ ምክንያትም አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር በማስታወስ፣ የዋና ጸሐፊው ከሥራ መታገድ አንደኛው ምክንያት ከዚህ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት የሚሰነዝሩ አሉ፡፡

የቦርዱ ዕገዳ ጊዜያዊ ይሁን ሙሉ በሙሉ ከሥራ ማሰናበትን የሚያጠቃልል መሆኑ ማረጋገጫ አልተገኘም፡፡ በሌላ በኩል ግን አቶ ጋሻው ከዚህ ውሳኔ በፊት መልቀቂያ ሳያስገቡ እንዳልቀሩ ይነገራል፡፡

ቦርዱ በአቶ ጋሻው ላይ እንዲወሰድ የወሰነው ዕርምጃ ንግድ ምክር ቤቱ በየዓመቱ በሚያካሂደውና ባለፈው ሐሙስ በይፋ በተከፈተው ‹‹የኢትዮጵያን ይግዙ›› ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት መክፈቻ ዕለት መሆኑ ደግሞ፣ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡

በዕለቱ አቶ ጋሻው የንግድ ትርዒቱን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ሲመሩ እንደነበር፣  የመክፈቻ ፕሮግራሙ ከተጠናቀቀ በኋላ ቦርዱ ተሰብስቦ ውሳኔውን ማሳለፉ የምንጮች መረጃ ያመለክታል፡፡

አቶ ጋሻው ንግድ ምክር ቤቱን ከስድስት ዓመታት በላይ በዋና ጸሐፊነት በመምራት፣ በንግድ ምክር ቤቱ ረዘም ላለ ጊዜ በያዙት ኃላፊነት የቆዩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

በእሳቸው ዋና ጸሐፊነት ወቅት አራት ፕሬዚዳንቶች የተፈራረቁ መሆኑም፣ አቶ ጋሻው ከሌሎች ዋና ጸሐፊዎች በተለየ በቦታው የቆዩ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል፡፡

ወደ ንግድ ምክር ቤቱ ከመምጣታቸው ቀደም ብሎ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በንግድ ሚኒስቴር አገልግለዋል፡፡    

በንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ ዕገዳ የተደረገባቸውን አቶ ጋሻውንና የቦርድ ሰብሳቢውን አቶ ሰለሞን ሪፖርተር ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም፣ ሁለቱንም በአካልም ሆነ በስልክ ለማግኘት አልተቻለም፡፡ 

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

በቀን 24 ትርፍ ሰዐት ስላለኝ youtube ጋር የወጡትን አብዛኛውን የሀገሬን ፊልሞች አይቻለሁ ። እንዴት ነው አዲስ አበባ የሚኖሩ እንስቶች ቲሸርት ብቻ ለብሰው መውጣት ጀመሩ እንዴ? መቸም ያን ቀሚስ ነው ማለት ይከብዳል ። ወይ ካሜራው ረዘም ያለ ቀሚስ ሲሆን ምስሉ አይገባለትም …

ተዋናዮቻችንና አለባበሳቸው : Melkam-selam Molla (Ethiopian Movie) Read more »

የወያኔ መንግስት ቴሌኮም አገልግሎት በተለይ ስልክና ኢንተርኔት ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር፣ በዜጎች ላይ የሚፈፅመውን አፈና እና እስር፤ በተያያዘም ኢትዮጵያ በቴሌና ኢንተርኔት በአቅርቦት ያለችበትን አነስተኛ ደረጃ የሚያሳይ ጥልቅ ሪፖርት ነው፡፡ በተለይ ማህበራዊ ድረገፅና ቴሌ ኮም ተጠቃሚዎች ላይ የሚደርሰውን አፈና እና የአቅርቦች ችግር …

የወያኔ መንግስት ስልክና ኢንተርኔት ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር፣ በዜጎች ላይ የሚፈፅመውን አፈና እና እስር፤ የሚያሳይ ጥልቅ ሪፖርት Read more »

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News የጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (November 06, 2015 News) – የዘንድሮ የወያኔ ብሄረሰብ ቀን በጋምቤላ ይደረጋል የተባለ ሲሆን የግዳጅ መዋጮ ተጀምሯል – ውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውን ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የገንዘብ ፈሰስ …

የዘንድሮ የወያኔ ብሄረሰብ ቀን በጋምቤላ ይደረጋል የተባለ ሲሆን የግዳጅ መዋጮ ተጀምሯል Read more »

ቡድኑ በቀጣዩ ኦሎምፒክ ማጣሪያም አይሳተፍም የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ሉሲ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሚመለከተው አካል መላክ የነበረበትን የተሳትፎ ማረጋገጫ ደብዳቤ ባለመላኩ በሰራው ጥፋት ሳቢያ፣ በካሜሩን አስተናጋጅነት ከሚካሄደው የ2016 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ውድድር ውጭ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ እግር …

ለሉሲዎች ከ2016 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ኦሎምፒክ ማጣሪያም ውጭ መሆን ፌዴሬሽኑ ተጠያቂ ነው ተባለ Read more »

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ችግራቸውን እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላለፉት 20 ቀናት መጠየቅና ማግኘት እንዳልቻሉ የጠቆሙት ቤተሰቦቹ፤ የጤንነቱ ጉዳይ እንዳሳሰባቸው በመግለፅ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለችግራቸው እልባት እንዲሰጣቸው በደብዳቤ አመለከቱ፡፡ የጋዜጠኛው ቤተሰቦች በደብዳቤያቸው እንደገለፁት፤ ከጥቅምት 7 ቀን …

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እንዳንጠይቅ ተከለከልን ሲሉ ቤተሰቦቹ አመለከቱ Read more »

“ዲሞክራሲያዊ ውይይት ከሌለ አገሪቱ እንደአገር አትቀጥልም” ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፤ “ከጋዜጠኞች የሚሰነዘርብኝን ትችት አልፈራም፤ ነጻ ሚዲያ ለዲሞክራሲ ግንባታው ሂደትና ለልማት እጅግ ወሳኝ ነገር ነው” ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ትናንት ዘገበ፡፡ “ፍጹም እንዳልሆንን እናውቃለን፤ በመሆኑም ከማንኛውም ጋዜጠኛ የሚቀርብብንን ትችት ለመቀበል ዝግጁ …

ጠ/ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም፤ የጋዜጠኞችን ትችት አልፈራም አሉ Read more »

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም በገንዘብ የታጀቡ ናቸው፡፡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡ ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ሕገወጥ ገንዘብና ሥልጣናቸውን ላለማጣት ሕግን ከመጣስና ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ ሌላውን አስወግደው እነሱ ብቻ የሚቆጣጠሩትና የእነሱን ፍላጎት …

መንግስታዊ ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች በገንዘብ የታጀቡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡ Read more »

“ክ/ከተማው ቦታው አይነካባችኹም ብሎ አዘናግቶናል፤ ለሌላ ዓላማ መዋሉ አሳዝኖናል” /ምእመናን/ “ለሌላ ዓላማ ሳይውል አጥቢያዎቹ በዕቅዳቸው እንዲያለሙት አመራር ይሰጥላቸው” /ቅ/ሲኖዶስ/ “ልማቱ በዓለ ጥምቀቱን ታሳቢ ያደረገ ነው፤ ቦታው በታቦት ማደርያነቱ ይቀጥላል” /ክ/ከተማው/ (አዲስ አድማስ፤ ናፍቆት ዮሴፍ፤ ቅዳሜ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.) ላለፉት 52 ዓመታት በበዓለ ጥምቀት ማክበርያነት እና በታቦት ማደርያነት ሲያገለግል የነበረው የባሕረ ጥምቀት ቦታ ለሌላ …

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እንዳንጠይቅ ተከለከልን ሲሉ ቤተሰቦቹ አመለከቱ

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ችግራቸውን እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል

       በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላለፉት 20 ቀናት መጠየቅና ማግኘት እንዳልቻሉ የጠቆሙት ቤተሰቦቹ፤ የጤንነቱ ጉዳይ እንዳሳሰባቸው በመግለፅ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለችግራቸው እልባት እንዲሰጣቸው በደብዳቤ አመለከቱ፡፡
የጋዜጠኛው ቤተሰቦች በደብዳቤያቸው እንደገለፁት፤ ከጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ  ምክንያቱን ባላወቁት ሁኔታ ተመስገን በሚገኝበት ዝዋይ ማረሚያ ቤት ቤተሰብም ሆነ ወዳጅ ዘመድ እንዳይጠይቀው መከልከሉ መላው ቤተሰቡን ስጋት ላይ ጥሎታል፡፡
የጤናው ጉዳይ በእጅጉ ያሳስበናል ያሉት ቤተሰቦቹ፤ በተለይ ቀደም ብሎ የነበረበት ህመም ተባብሶ የግራ ጆሮው መስማት እስከመቸገር እንዳደረሰውና የወገብ ህመሙ እረፍት ነስቶ አላስተኛ እያለው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በተደጋጋሚ ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ቢመላለስም ተመስገንን ማግኘት እንዳልቻለ የሚናገረው የተመስገን ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ፤ የማረሚያ ቤቱ ጥበቃዎች “ለምን መጠየቅ ተከለከልን?” ስንላቸው፤ “የበላይ ትዕዛዝ ነው” ይሉናል፤ ብሏል፡፡ በዚህም የተነሳ ተመስገንን ላለፉት 20 ቀናት እንዳላዩትና ቤተሰቡንም ለጭንቀት እንደዳረገ ይገልፃል፡፡
“የቤተሰባችን አባል በሆነው ተመስገን ላይ በተለየ ሁኔታ ተደጋጋሚ የህግ ጥሰት እየደረሰ ነው” ያሉት ቤተሰቦቹ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ጣልቃ በመግባት ችግሩን እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቀድሞ ይሠራበት በነበረው “ፍትህ” ጋዜጣ ላይ በወጡ ጽሑፎች ምክንያት፣ ተከሶ የ3 አመት እስራት ተፈርዶበት፣ ማረሚያ ቤት እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ 

ቴክኖ ሞባይል ላለፉት 3 ወራት አላመረተም

    በሀገሪቱ በተከሰተው የውጭ ምንዛሪ እጥረት የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ምርት ማምረት እስከማቆም የደረሱ ሲሆን በአስመጪና ላኪነት የንግድ ስራ ላይ የተሠማሩ ነጋዴዎችም መቸገራቸውን ገልፀዋል፡፡
ከ900 በላይ ሠራተኞችን ይዞ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በማምረት ሥራ ላይ የተሠማራው የቴክኖ ሞባይል አምራቹ ዊጉዩ ኩባንያ፤ በውጭ ምንዛሪ እጥረቱ የተነሳ ላለፉት 3 ወራት ምርት ማምረት ማቆሙን አስታውቋል፡፡
ኩባንያው የውጭ ምንዛሪ ከባንክ ቢጠይቅም “ትንሽ ጊዜ ታገሱ” የሚል መልስ እንደተሰጠው የቴክኖ የአስተዳደር ክፍል ሃላፊ አቶ ገነነ አዘነ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
ሃላፊው እንዳሉት፤ ኩባንያው ጠንካራ የገንዘብ አቅም ያለው በመሆኑ ለኪሣራ ባይዳረግም ስራ ባቆመባቸው ወራት በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አጥቷል፡፡
“ችግራችንን ለመንግስት አሳውቀናል፤  በቅርብ ጊዜ ችግሩ ይፈታል የሚል ተስፋ አለን” ብለዋል፤ ሃላፊው፡፡
ኩባንያው በቀን ከ10ሺህ በላይ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን አምርቶ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ያቀርብ እንደነበርና በአሁን ሰአት በምንዛሪ እጥረቱ የተነሣ ሙሉ ለሙሉ ምርት ማቆሙን ጠቁመው፣ ያጋጠማቸው ችግር ጠንከር ያለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በተመሳሳይ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው በአስመጪነትና ላኪነት ስራ ላይ የተሠማሩ ነጋዴ በበኩላቸው፤ የዶላር እጥረቱ ከአንድ አመት በላይ እንደሆነው፤ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጥረቱ እየተባባሰ እንደመጣና በንግድ ስራቸው ላይ ከፍተኛ ፈተና እንደጋረጠባቸው ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡   
“ከ5ሺ ዶላር ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ለባንክ ፕሮፎርማ ካስገባን በኋላ እድል ከቀናን ከ3 እና 4 ወር በኋላ ነው የምናገኘው” የሚሉት ባለሃብቱ፤ በችግሩ የተነሳ ሠራተኛ በትነው ስራ ፈተው እስከመቀመጥ መድረሣቸውን ገልፀዋል፡፡
የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ የሆኑ ግለሰብም ፋብሪካቸው በውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ከውጭ ጥሬ እቃ ማስገባት መቸገሩን ጠቅሰው ባለፉት 4 ወራት ኢንዱስትሪያቸው ለከፍተኛ ኪሣራ እየተዳረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ “መንግስት በተደጋጋሚ ችግሩ በአጭር ጊዜ ይቀረፋል” የሚል ምላሽ ሲሰጠን ቆይቷል ያሉት ስራ አስኪያጁ፤ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ችግሩ ይበልጥ እየተባባሰ መጥቷል ብለዋል፡፡
በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ችግሩ ካልተቃለለላቸው ሠራተኛ እስከመቀነስ የሚደርስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ የጠቀሱት ስራ አስኪያጁ፤ በቅርብ የሚያውቋቸው ፋብሪካዎችም ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዳቸውን እንደታዘቡ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ በአስመጪነትና ላኪነት የንግድ ስራ ላይ የተሠማሩ ሌላው አስተያየት ሰጪ፤ የዶላር እጥረቱ ስራቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዳስተጓጐለባቸው ጠቁመው፤ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ እልባት ካላበጀለት የስራ ዘርፋቸውን ለመቀየር እንደሚገደዱ ተናግረዋል፡፡
“የምንዛሬ ጥያቄ ስናቀርብ በአሁን ሰአት መንግስት ከውጭ ስንዴ እያስገባ ስለሆነ ትንሽ ታገሱ የሚል ቀጥተኛ ያልሆነ የቃል መልስ እየተሰጠን ነው ብለዋል – ባለሀብቶቹ፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሃጂ ኢብሣ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ “ይሄ የኛም
ጥያቄ ነው ትክክለኛ ምላሽ የሚገኘው ከብሔራዊ ባንክ ነው” የሚል ምላሽ የሰጡን ሲሆን የብሔራዊ ባንክ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ መስፍን ደምሴ ጋር ደውለን መረጃ ለማግኘት ብንሞክርም በደብዳቤ መጠየቅ እንዳለብን ተገልፆልናል፡፡  

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ከደቡብ አፍሪካ ደርባን የአይን እማኞችን ጠቅሶ የአሜሪካ ድምጽ እንግሊዘኛው ድህረገጽ እንዳለው ባለፈው ሳምንት ብቻ ስድስት ኢትዮጵያውያን የውጪ ዜጎች ይውጡልን በሚሉ ደቡብ አፍሪካውያን መገደላቸው ታውቋል::ዮናስ ፍቅሩ ይባላል በደርባን ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ሲሆን ስድስቱንም ሟጮች ያውቃቸዋል::ሁሉም በ20ዎቹ እድሜ ክልል …

በደቡብ አፍሪካ ስድስት ኢትዮጵያውያን ተገደሉ::ደቡብ አፍሪካውያን ለውጪ ዜጎች ያላቸው ጥላቻቸው አገርሽቶባቸዋል::‪ Read more »

በዚህ ሳምንት በማዕከል የሚደረገው ለውጥ ይፋ ይሆናል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለክፍላተ ከተማና ለወረዳዎች 1,600 አመራሮችን ሾመ፡፡ ለተሿሚዎቹ ባለፈው ሳምንት ለሦስት ቀናት የቆየ የፖሊሲ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሙስናና በብልሹ አሠራር ገምግሞ ካሰናበታቸው አመራሮች በተጨማሪ፣ ከዲፕሎማ በታች የትምህርት ደረጃ ያላቸውን አመራሮች አንስቷል፡፡ በእነዚህ ተሿሚዎች ምትክ ለአሥሩ ክፍላተ ከተሞችና ለ116 ወረዳዎች የተሾሙት 1,600 አመራሮች ከመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ናቸው ተብሏል፡፡ 

እነዚህ ተሿሚዎች አዳዲስና ከዚህ ቀደም በአስተዳደር መሥሪያ ቤቶች በተለያዩ ደረጃዎች ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው፡፡ ለእነዚህ ተሿሚዎች ባለፈው ሳምንት ከማክሰኞ ጥቅምት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት የቆየ የፖሊሲ ማብራሪያ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ 

የፖሊስ ማብራሪያውን የሰጡት የአዲስ አበባ አቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ይስሐቅ ግርማይና የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃን ናቸው፡፡ 

በፖሊሲ ማብራሪያው እነዚህ ተሿሚዎች በከተማው መልካም አስተዳደር ማስፈን፣ የፀረ ሙስና ትግል በብቃት ማካሄድ እንዳለባቸውና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት መሥራት እንደሚኖርባቸው፣ በፖሊሲ ማብራሪያው ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ከአቅም ግንባታ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተለይ አቶ ይስሐቅ በሥልጠና ወቅት እንደተናገሩት፣ ከዲፕሎማ በታች የትምህርት ደረጃ ያላቸው ከኃላፊነት የተነሱ አመራሮች በቀጣይ ትምህርታቸውን የሚቀጥሉበት አሠራር ይፈጠራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የተነሱት የቀድሞ አመራሮች በጥቃቅንና በአነስተኛ ማኅበራት ተደራጅተው የተለያዩ ሥራዎችን እንዲያካሂዱ ይደረጋል ሲሉ አቶ ይስሐቅ በሥልጠናው ወቅት መግለጻቸው ታውቋል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በክፍላተ ከተሞችና በወረዳዎች ሲያካሂድ የቆየውን ሹም ሽር በማጠናቀቅ፣ ትኩረቱን በማዕከል ደረጃ በሚያካሂደው ለውጥ ላይ አድርጓል፡፡ በዚህ ሳምንት መጨረሻ በማዕከል ደረጃ የሚያካሂደውን የመዋቅርና የባለሥልጣናት ሹም ሽር ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡      

 

ጥቅምት 20 ለ21 አጥቢያ 2008 ዓ.ም. የልጃቸውን ጓደኛ በሽጉጥ ተኩሰው በመግደል የተጠረጠሩ ሐኪም፣ ከነመሣሪያቸው በቁጥጥር ሥር ውለው እየተመረመሩ መሆኑ ታወቀ፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 13/14 ልዩ ሥፍራው ማጂክ ካርፔት በሚባለው ትምህር ቤት አካባቢ የተገደለው ወጣት ቴዎድሮስ ሲሳይ ይባላል፡፡

ቴዎድሮስ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን በዕለቱ የማንቸስተር ዩናይትድ ግጥሚያ ሲመለከቱ አምሽተው በዚያው ሲዝናኑ ያመሻሉ፡፡ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት አካባቢ ሟች ቴዎድሮስና ጓደኞቹ በግድያ ወደተጠረጠሩት ዶ/ር ተስፋዬ ያዕቆብ (በሰላም ከፍተኛ የጥርስ ክሊኒክ የጥርስ ሐኪም ናቸው ተብሏል) ቤት መሄዳቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡

የተጠርጣሪው ልጅ መጠጥ ሲቀምስ የመጮህና የመበጥበጥ ባህሪ እንዳለበት የሚናገሩት የዓይን እማኞች፣ ጓደኞቹን ይዞ ቤቱ እንደደረሰ ባህሪው በመነሳቱ ሟችና ሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ከግቢ ወጥተው በመሄድ ላይ እያሉ ተጠርጣሪው ሽጉጥ ይዘው መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ አንደኛው ወጣት ኳስ ሲያዩ ማምሸታቸውን በማስረዳት ላይ እያለ ተጠርጣሪው ወደ ሟች ተጠግተው በመተኮስ እንደገደሉት የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

የሟች ጓደኞች ተጠርጣሪው ሐኪም ሆን ብለው እንደገደሉት የገለጹ ቢሆንም፣ ተጠርጣሪው ግን ባርቆባቸው እንደሆነ ለፍርድ ቤት ማስረዳታቸውን ሪፖርተር ከፖሊስ ያገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

ተጠርጣሪውን ሐኪም በቁጥጥር ሥር አድርጎ በመመርመር ላይ የሚገኘው ፖሊስ፣ ፍርድ ቤት አቅርቦ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡ ሟች ቴዎድሮስ ሲሳይ በሳሪስ አቦዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀኑ ስምንት ሰዓት የቀብር ሥርዓቱ መፈጸሙም ታውቋል፡፡

 

በማላዊ ታስረው የነበሩት ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰውም እዚያው እስር ቤት እስከዛሬ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥ ወደ 200 የሚሆኑ ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ፣ እስካሁን እስር ቤት ስለሚገኙት ፍልሰተኞች ጉዳይ የት ደርሷል?

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የመርካቶ ቁጥር ሁለት ቅርንጫፍ ከፍተኛ ኦዲተርና ሦስት ኦፊሰሮች ጉቦ በመቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል ጥቅምት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ተከሰሱ፡፡

ተከሳሾቹ የግል ተበዳይ አቶ ዮሐንስ ጥጋቡ የተባሉትን በጨርቃ ጨርቅ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴ፣ ‹‹ግዢና ሽያጭ አልተጣጣመም፣ በቆጠራ የሚፈጠረውን ጉድለት ባላንስ እናደርግልዎታለን፤›› በማለት ሁለት ሚሊዮን ብር ጉቦ መጠየቃቸውን፣ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመሠረተው ክስ ያስረዳል፡፡

የጉቦ መቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞች አቶ መሠረት ታደሰ የተባባሪዎች ምልመላና ሥልጠና ኦፊሰር፣ አቶ አበበ ደቦ ቡልቱሜ የኢንቬስትጌሺን ከፍተኛ ኦዲተር፣ አቶ አያና ጋሩማ የኢንተለጀንስ አሰባሰብ ጀማሪ ኦፊሰር፣ አቶ ሀብታሙ ታደሰ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምቦ ቅርንጫፍ ኦፊሰርና አቶ አብዲሳ ደቦ ቡልቱሜ የባንኩ የሰው ኃይል አስተዳዳር ባለሙያ ናቸው፡፡

ተከሳሾቹ ከላይ የተጠቀሰውን ሁለት ሚሊዮን ብር ጉቦ የጠየቋቸው አቶ ዮሐንስ ባለመስማማታቸው፣ አንደኛ ተከሳሽ አቶ መሠረት አደራዳሪ መስሎ ነጋዴውን በመቅረብ፣ ‹‹ኦዲተሮቹ ብዙ ገንዘብ መቀበል ስለለመዱ አንተ ሁለት መቶ ሺሕ ብር ብትሰጣቸው ምንም አይደለም፤›› ቢላቸውም ተበዳዩ አለመስማማታቸውን ክሱ ይጠቁማል፡፡ 

የነጋዴውን አለመስማማት የተረዱት ተከሳሾች ያላቸውን ዕቃ ብዛት በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋቸው እንደሰጧቸው የሚገልጸው የዓቃቤ ሕግ ክስ፣ በዝርዝር የሰጡት ዕቃ ጉድለት እንደሚያመጣና ጠቅላላ የዕቃውን ብዛት እንዳልሰጧቸው ሲገልጹላቸው፣ ተበዳዩም ካልተቆጠረ እንደማይታወቅ በመግለጽ እንደተከራከሯቸው ክሱ ያስረዳል፡፡

የግል ተበዳዩን በተለያየ መንገድ ስላስጨነቋቸው ግንቦት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ለአንደኛ ተከሳሽ አራት መቶ ሺሕ ብር መስጠታቸውን፣ በድጋሚ በተለያዩ ቀናት በድምሩ ሁለት መቶ ሺሕ ብር መስጠታቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ ተከሳሾቹ ሰነዱን ሲመረምሩ ተበዳዩ 12 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ከፍተኛ ዕዳ እንደሚመጣባቸው ማወቃቸውን በመንገር፣ ተበዳዩን በማስጨነቅ አራት መቶ ሺሕ ብር እንዲሰጧቸው ማድረጋቸውን፣ በአጠቃላይ በተለያዩ ቦታዎች በመቅጠር ተከሳሾች ከተበዳይ 1.2 ሚሊዮን ብር መቀበላቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡

አቶ መሠረት የተባለው ተከሳሽ ጉቦ በመቀበል ያገኘውን ገንዘብ ለመሰወርና ለመደበቅ፣ አምቦ ከተማ ለሚኖረውና ለአራተኛ ተከሳሽ ወንድሙ አቶ ሀብታሙ አምስት መቶ ሺሕ ብር መስጠቱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡ አቶ ሀብታሙ የገንዘቡ አመጣጥ ሕገወጥ መሆኑን እያወቀ፣ አምቦ ከተማ ቀበሌ 02 ውስጥ ስፋቱ 200 ካሬ ሜትር ቦታ በ140 ሺሕ ብር በእናቱ ስም እንደገዛለት፣ 100 ሺሕ ብር ደግሞ ለሌላ ግለሰብ እንዲያስቀምጥለት መስጠቱን ክሱ ያብራራል፡፡ አቶ አበበ ደግሞ ለአቶ አብዲሳ 287,900 ብር ሲሰጠው ገንዘቡን መሬት ውስጥ መቅበሩን፣ አቶ አያና የተባለው ሦስተኛ ተከሳሽ ደግሞ በአምቦ ከተማ 400 ካሬ ሜትር መሬት በ80 ሺሕ ብር በመግዛት በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ ለማሰመሰል መሥራታቸውን ክሱ ያብራራል፡፡

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ ፈጽመዋል በተባለው ጉቦ መቀበል ከባድ የሙስና ወንጀልና በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሙስና ወንጀል የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸዋል፡፡

     

 

ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት መስተዳድሩ የባጃጅ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ያወጣውን ህግ የተቃወሙ አሽከርካሪዎች የ3 ቀናት የስራ ማቆም አድማ ካደረጉ በሁዋላ፣ የተወሰኑ አሽከርካሪዎች ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለኢሳት ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አሽከርከሪዎች እንደሚሉት ፣ ወደ እስር ቤት ከተወሰዱ በሁዋላ ጨማቸውን አውልቀው፣ እጆቻቸው በሲባጎ ገመድ ወደ ሁዋላ ታሰሮ የወስጥ እግራቸውን …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

የተመድ ፀጥታ ጥበቃ ም/ቤት በኤርትራ ላይ በጎርጎሪዮሳዊው 2009 ዓም የጣለውን የጦር መሪያ ማዕቀብ ባለፈው ሳምንት እስከ እስከ ኅዳር፣2016 ዓም አራዘመ። ምክር ቤቱ የወሰደው ይህ ውሳኔ የአውሮጳ ኅብረት በስደተኞች ጎርፍ የገጠመውን ቀውስ የስደተኞች መፍለቂያ ከሆኑት ኤርትራን ከመሳሰሉ ሃገራት ጋር ባንድነት መፍትሔ ለመሻት በያዘበት ወቅት ነው።

(በብአዴን/ኢህዴን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የጻፍኩት) የህወሓት ፈተና – ‹‹የታገልኩት፣ የቆሰልኩት፣ የሞትኩትም እኔ ብቻ ነኝ እና የታሪኩ ባለቤትም የትግሉ ውጤት ይበልጥ ተጠቃሚም መኾን ያለብኝ እኔ ነኝ››። ይህ ትርክት ጫፍ ሄዶ ሄዶ ኢዲሞክራሲያዊነት እና ጠባብነት የወለደው ኾኖ ወደ ትምክህተኝነት ሊያድግ ይችላል። ኣብዛኞቹ የዚህ ፈተና ሰለባ የኾኑ የድርጅቱ ኣባሎች ብ1993ቱ የድርጅቱ የውስጥ ትግል የተሸኙ ሲኾን የነሱ ደጋፊዎች እዚሁ የማሕበረሰብ ሚዲያ ላይ የሚያሳዩት ትምክህት አሁንም አለ። ድርጅቱ የዚህ አይነቱ አዝማሚያ ዋናው ፈተናው ሲኾን በቀጣይ የቀሩ ትርፍራፊ የማጽዳት ስራዉን አጠናክሮ የማካሄድ ሓላፊነት አለበት። ይህንን ፈተና ተቋቁሞ እኩልነት በመቀበል የታገልነው በጋራ እና ለጋራ ጥቅም ነው በማለት እዚህ ለበቃ አብዛኛው አባሉን በዚህ አስተሳሰብ ዙሪያ ማሰለፍ ከቻለ ህወሓት ውጤታማ ይኾናል። ብአዴን፦ ያለፉ ስርዓቶች፣ በተለይ የአጼኣዊው የዘውድ ስርዓት፣ ናፍቆት። ይህ በእኩልነት ያለማመን የአንዳንድ የብአዴን ትልቁ ፈተና ነው። የጥንት ታሪኮች የአንድ ብሔር ይኾኑ ዘንድ የመመኘት ከዚህ በዘለለም የትምክህት ሃይሉ የሚያራምደው በአለፉት ስርአቶች የተፈጸሙ በደሎች የመካድ አዝማሚያ። ብአዴን የዚህ አይነቶቹ አባላት ሽኝቶ ብቻ ሳይኾን የተፈጠረው አዲስ የኢትዮጵያዊነት የእኩልነት ትርጉም አልጥም ብሏቸው ወደ ድሮ አመለካከታቸው በመኮብለል ብዙ አባላቶቹ እና አመራሮች ሳይቀር ከመስመሩ ወጥተዋል። አንዳንዶቹ ወደ ትክክለኛ ቀለማቸው በመሄድ ፓርቲዎች አቋቁመው ብአዴንን ዞረው ታግለዉታል። ይህንን ፈተና ተቋቁሞ የጋራ ሀገር ነው ያለን የልፉት ስርዕእቶች ሁላችንንም በድለዋል። እነዚህ ስርዓቶች ላይመለሱ በተባበረ ክንድ ተወግደዋል። ስርዓቶቹን ለማስወገድ የአማራ ብሔር ተወላጆችም አኩሪ ተጋድሎ መፈጸማቸውን ማስተማር […]

አትሌት ከላሊ ንጉሴ አብርሃ

ከላሊ ንጉሴ ይባላል፡፡ የረዥም ርቀት እና ማራቶን ሯጭ ሲሆን አሁን የሚገኘው በስደት ቶሮንቶ፣ ካናዳ ውስጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ያሳለፈውን የህይወት ተሞክሮ በማስመልከት ከኢትዮጵ ዛሬ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፤ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ማጣርያ ግጥሚያ ለመሳተፍ ወደ ቦትስዋና በቅርብ ለሄዱት 10 የኤርትራ ብሔራዊ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የፖለቲካ ጥገኝነት የቦትስዋና መንግስት ፈቅዶላቸው እንደነበር ይታወሳል። ስፖርተኞቹ ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቦትስዋና ቡድን ጋር ከተጫወቱ በውኃላ ነው ወደ ሃገራቸው በሚወስዳቸው አውሮፕላን ላይ አንሳፈርም በማለት በቦትስዋና ጥገነት የጠየቁት።

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የፖሊስ ምንጮች እንደገለጹት አንድ የአየር ጤና የፖሊስ ባልደረባ በህክምና እጦት መሞቱን ተከትሎ፣ የክፍለከተማው ፖሊሶች ስራ በማቆም ተቃውሞአቸውን ከገለጹ በሁዋላ፣ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ፖሊሶች መልቀቂያ አስገብተዋል። የመቀሌ ከተማ ተወላጅ የሆነው ኦፊሰር የማነ በኩላሊት ህመም ሲሰቃይ ከቆዬ በሁዋላ፣ በፖሊስ ሆስፒታል ተገቢውን ህክምና ባለማግኘቱ፣ በግል ለመታከም 16 ሺ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

በውጭ ከሚኖሩ ዜጎች፣ ወደ ኢትዮጵያና ኬንያ የሚላከው ገንዘብ መጠን እያደገ በመሄድ ላይ መሆኑ ተገለፀ። በዚህ መንገድ ወደ ሁለቱ ሃገራት የሚገባው የውጭ ምንዛሬ ከሰሃራ በስተደቡብ ከሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት ጋር በንፅፅር ሲታይ ከፍተኛ መሆኑን የዓለም ባንክ አስታውቋል።

መንግስት በርሃብ ለተጠቁት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ታወቀ • በርሃብ የተጠቁት ዜጎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው • ‹‹ሰው በርሃብ እያለቀ ነው›› • ‹‹የሚላስ የሚቀመስ የለም፡፡ ቤተሰባችን ፈርሷል›› • ‹‹እርዳታ ቢሰጥማ ከዚህ ድረስ አንመጣም ነበር፡፡›› መንግስት በርሃብ ለተጎዱት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ …

መንግስት በርሃብ ለተጠቁት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ታወቀ • በርሃብ የተጠቁት ዜጎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው Read more »

ክብደትን መቀነስ የልብ በሽታን ለማስወገድ ትክክለኛውመንገድ ነው፡፡ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት የደም ቅዳ ሴሎቻችን እንዲጠቡ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህ ሳቢያም የኮሌስትሮል ዝቃጮች እንዲሰበሰቡና እጢ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ አደገኛ የልብ ህመም እንዲከሰትብዎ ምክንያት ይሆናል፡፡ ክብደትዎን በመቀነስ በተለይም የሆድ አካባቢ ቦርጭዎን በማጥፋት የደም ቅዳ …

የልብ በሽታን ለመከላከል … ክብደትዎን ይቀንሱ Read more »

“እኔ በቁሜ ብሸለምም ሽልማቱ ለሌሉት ባልደረቦቼም ነው” (አርቲስት ዙፋን) “ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች ፈልጉ” ተብሎ ነው፤ተመርጬ የተቀጠርኩት · ተወዛዋዥነት ለዘመናት ተንቆ የኖረ ሙያ ነው ትላለች የ50 ዓመት የኪነ ጥበብ ጉዞሽ እንደሚዘከር ቀደም ብሎ መረጃ ነበረሽ? በሰማሽ ወቅት ምን አልሽ? የአንጋፋ አርቲስቶችን …

የ50 ዓመታት የከያኒ ህይወት- ከኮረዳነት እስከ እማወራነት! Read more »

  Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተለያዩ አይነት የሙስና ወንጀሎች ሲሰሩ በጉምሩክ እና ገቢዎች መስሪያ ቤትን የሙስና ወንጀል የለም ብሎ ባይካድም ከጥቅማቸው ይልቅ የሕዝብ አደራ አንበላም የሚሉ ሰራተኞች ለሕወሓት ስውር እጆች አንታዘዝም በማለታቸው በሙስና ስም ጥቃት እየደረሰብን …

ለሕወሓት ስውር እጆች ታዛዥ ስላልሆንን እየተጠቃን ነው ሲሉ የጉምሩክ ሰራተኞች ይናገራሉ:: ‪ Read more »

ተወዳጅ የማህበራዊ ሚዲያ የሆነው ፌስቡክ አገልግሎቶቹን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያዘመነ እና አዳዲስ መተግበሪያዎችን እያስተዋወቀ ይገኛል። በቅርቡ አዲስ የቪዲዮ ማጫወቻ አገልግሎት ማስታወቁም ይታወሳል። ታዲያ ፌስቡክ ገፃችን ላይ የሚመጡ እና የወደድናቸውን ቪዲዮዎችን ቀለል ባለ መንገድ እንዴት አውርደን ለራሳችን መያዝ እንችላለን የሚለውን እንመከለታለን። …

ፌስቡክ ገፃችን ላይ የሚመጡ እና የወደድናቸውን ቪዲዮዎችን ቀለል ባለ መንገድ እንዴት አውርደን ለራሳችን መያዝ እንችላለን ? Read more »

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወሳኝነታቸውን ያሳዩበት መድረክ

በኢትዮጵያ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እስከዛሬ ሲደረጉ ከነበሩ ከንግግር ያልዘለሉ የቁርጠኝነት ማሳያዎች አንድ እርከን የዘለለ እንደሆነ የተነገረለት በጥናት ላይ የተመሠረተ ውይይት፣ በቅርቡ በመንግሥት ከፍተኛው አስፈጻሚ አካል ተካሂዷል፡፡

ይህ ለሕዝብ ከወትሮው በተለየ በከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ወቀሳና ተጠያቂነትን ያስነሳው ውይይት፣ መነሻ ምክንያቱ ታች መሬት ተወርዶ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ የዳሰሳ ጥናት መካሄዱ ነው፡፡ የጥናቱ አቅራቢዎች በውይይቱ ወቅት የችግሩን ስፋትና መጠን ሲያስረዱ፣ ለወትሮው የሐሳብ ልዩነቶቻቸውን ከመጋረጃ በስተጀርባ በመጨረስ ለሕዝብ አንድ ሆነው በመቅረብ የሚታወቁት የኢሕአዴግ ቱባ ባለሥልጣናት፣ በአደባባይ ልዩነቶቻቸውን በግልጽ ያወጡበት ውይይት እንደነበር ታይቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአገሪቱ ቁንጮ ባለሥልጣን ሆነው ከመጡበት ጊዜ  ጀምሮ፣ በግልጽ የሥልጣን ባለቤትና የገዥው ፓርቲ አቅጣጫ የመወሰን ሥልጣን እንዳላቸው ያሳዩበትም ነበር፡፡ በተለይ በመሬት፣ በኢንቨስትመንት፣ በፍትሕና በተለያዩ መስኮች በጥናቱ የቀረበው አሳሳቢ ሥጋት ካልተወገደ አደገኛነቱንም በማስጠንቀቅ አውስተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፅንኦት በመስጠት ለአገሪቱም ሆነ ለሕዝቡ አደገኛ የሆነውን የመልካም አስተዳደር ችግር መታገል የሕዝብ አመኔታን እንደሚያስገኝ አስታውቀው፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትም በውስጣቸው መደንገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ከውይይቱ በኋላ ባለሥልጣናት በብሔር፣ በዝምድና፣ በጥቅማ ጥቅምና በመሳሰሉት ከተሳሰሯቸው ኔትወርኮቻቸው እንዲላቀቁም አስጠንቅቀዋል፡፡ ዝርዝሩን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ ወይም በ ፖለቲካ ገጽ ይመልከቱ፡፡

 

ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት መግባባትና መተባበር ሊቀመንበር የሆኑት የአቶ ፈንታሁን ብርሃኑ የ13 አመት ሴት ልጅ በአንድ ወጣት በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ ስትገደል፣ ሌላው የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ አበራ ሃይለማርያምም በዚሁ ወጣት ተገድለዋል። አቶ ፋንታሁን ለኢሳት እንደተናገሩት ጎረቤታቸው የሆኑት አቶ አበራ የተገደሉት ምናልባትም ጩኸት ሰምተው ልጃቸውን ለመታደግ በመሞከራቸው ሳይሆን …

ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታይዋን በሚባለው አካባቢ ይሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች፣ ሆን ተብሎ በተቀሰቀሰ እሳት ድርጅታቸው እስከ ሙሉ ንብረታቸው እንደወደመባቸው ለኢሳት ተናግረዋል። ድርጊቱ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ የተፈጸመ ሲሆን፣ መንግስት በአካባቢው ለሚያሰራው መንገድ ድርጅቶችን በማቃጠል ካሳ እንዳይከፍል ለማድረግ ነው በማለት ነዋሪዎች ተናግረዋል። በቃጠሎው ከ15 በላይ የንግድ ድርጅቶች የወደሙ ሲሆን፣ ፖሊሶች ህዝቡ …

በፌዴሬሽኑ ተልካሻ አሰራር ስህተት የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ታገደ ፌዴሬሽኑ በሚሰራው ተደጋጋሚ ስህተት ትምህርት የሚሰጥ እርምጃ መወሰድ አለበት !!! በፌዴሬሽኑ ተልካሻ አሰራር ምክንያት የኢትዮጵያ ሴቶች ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያውጭ ሆነ በወንዶች ብሄራዊ ብድን ቢጫ ካርድ ትምህርት ያልወሰደው የኢትዮጵያ የእግር …

በፌዴሬሽኑ ተልካሻ አሰራር ስህተት የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ታገደ Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

የጀርመኑ ኮሜርስ፤የዩናይትድ ስቴትሱ ሲቲ እና የኬንያው ንግድ ባንኮች በአዲስ አበባ ቢሮ የመክፈት እቅድ ሰንቀዋል። በኢትዮጵያ ቢሮዎቻቸውን የከፈቱት የውጭ ኩባንያዎች ግን በዘርፉ ያለምንም ገደብ የመስራት ፈቃድ የላቸውም።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከህገ መንግስቱ ጀምሮ አዋጅና በሌሎችም የዜጎችን መብት የሚደነግጉ በርካታ መሰረቶች ቢኖሩም ለይስሙላ ህጋዊ ሥርዓት እንዳለ ከማስመሰልም አልፎ ለአገዛዙ ማጥቂያና መግዢያ ከመሆን ባለፈ የዜጎችን መብት እያስከበሩ አይደለም፡፡ ባለፉት 6 ወራት እንኳን ህግ እንደተቀበረች፣ በዚሁ አገዛዙ ውስጥ ተፅዕኖ ያለው የፍርድ …

ከነካባው የተቀበረውን የፍትህ ሥርዓት ነፃ ለማውጣት ትግላችን አጠናክረን እንቀጥላለን! (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ) Read more »