የማላዊ መንግስት ፖሊስ 20 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ይዞ አሰረ::
የማላዊ መንግስት ፖሊስ 20 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ይዞ አሰረ::
የማላዊ መንግስት የደድዛ አውራጃ ፖሊስ በሞዛምቢክ እና በማላዊ ድንበር ላይ በሕገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ገብተዋል ያላቸውን 20 ኢትዮጵያውያንን በመያዝ ማሰሩን አስታወቀ::በሕገወጥ መንገድ ማላዊ በመግባት ወደ ሞዛምቢክ ለማቋረጥ የሞከሩት እንዚሁ ኢትዮጵያውያን በእጃቸው ምንም አይነት የመግቢያ ፈቃድ እና የጉዞ ሰነድ ማስረጃ የሌለ ሲሆን እንዚሁኑ የተያዙትን ሕገወጥ ስደተኞች የድንበር ፖሊሶች ከኢሚግሬሽን ቢሮ አሳልፎ መስጠቱ ታውቋል::
በርካታ ኢትዮጵያውያን አሁንም ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ መሆናቸውን ይህ ዘገባ ያሳያል
