በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ አቃቤ ህግ የጠየቀው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ

በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ አቃቤ ህግ የጠየቀው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ … አቃቤ ህግ የሽብርተኝነት ክስ መስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ተበይኖላቸው በነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የጠየቀው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ፡፡


ዛሬ ህዳር 6/2008 ዓ.ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ የተጠየቀውን ይግባኝ መዝገቡን መመርመሩን በመግለጽ ዝርዝር ሁኔታውን በንባብ ሳያሰማ በአጭሩ፣ ‹‹ይግባኙ ያስቀርባል ብለናል›› ብሏል፡፡በመሆኑም ይግባኝ የተጠየቀባቸው ተከሳሾች ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃም ሰለሞን በቀረበባቸው ይግባኝ ላይ በአካል ቀርበው የቃል ክርክር ለማድረግ ለህዳር 29/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

የስር ፍርድ ቤት በነጻ እንዲሰናበቱ ቢበይንም፣ ሁሉም ተከሳሾች አሁንም ድረስ በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

2 Comments on “በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ አቃቤ ህግ የጠየቀው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ”

  1. በጎሳ ተደራጅተው ያለማንም ጤያቂ የህዝብ ሃብት በግልጽ እየዘረፉ ሃብት በሃብት በሆኑበት ሃገር ሌቦቹ አሳሳሪ ሆነው ንጽኡሕኣን ዘእጎች እንደበግ እየታሰሩ ማየት እንዴት አይምሮን ይሰቀጥጥኣል?ሕግ በሌለበት ሃገር ስለፍትህ ማውራትስ በራስ መቀለድ አይሆንም?
    የሚደንቅ ነው ጎበዝ!በአሁኑ ግዘእ ኢትዮጵያ ውስጥ እስር ቤቶች የንጽኡን ማጎሪያ ሲሆኑ ሌቦቹ አሳሪዎች:ዳኝኦች:ከሳሾች እንደሆኑ በግልጽ እያየን ነው::እስከመቼ እንደዚህ ያለበደል ተሽክመን እንኖራለን?እያንዳዳችን መፍትሄ እንፈልግ እንጂ አለበለዚያ እየጤፍኣን እኮ ነው::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*