‹‹ቤዛ እንሁን!›› ወገን ተርቧል፤ እንድረስለት! የበጎ ፈቃደኝነት ኮሚቴ ተቋቋመ::

በትላንትናው እለት በገለፅነው መሰረት በሀገራችን በተከሰተው ቀውስ (ድርቅ/ርሃብ) ዙሪያ ‹‹ያገባኛል!›› የምንል ዜጎች በበጎፈቃደኝነት ኮሚቴ አቋቁመናል፡፡ ዛሬ ባደረግነው አስቸኳይ ስብሰባ የተገኙ 13 ሰዎች የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡

1. ሁላችንም እንደዜጋ ከራሳችን በመጀመር ሚናችንን መወጣት ይኖርብናል፡፡ በዚህም መሰረት ከእያንዳንዳችን በነፍስ ወከፍ በትንሹ ከ100 ብር በመጀመር እንድናዋጣ፤
2.
3. በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን (ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ ጓደኛ፣ የስራ ባልደረባ…..) በማስተባበር ለእነዚህ ወገኖቻችን አስቸኳይ የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታ ማሰባሰብ፤
4.
3. ቀጣይነት ያለው የገቢ ማሰባሰቢያ ስልቶች ተቀይሰው በአፋጣኝ ወደተግባር እንዲገባ፤
4. መንግስት የቅድሚያ ተነሳሽነት (initiative) ወስዶ ‹‹ብሔራዊ የእርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚቴ›› በፍጥነት እንዲያቋቁም ግፊት ማድረግ፤

5. ከዓለም-ዓቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች፣ በውጪ ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣ ከታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም አጋር ሊሆኑ ከሚችሉ ማንኛቸውም ተቋማት ጋር የቀረበ የስራ ግንኙነት በመፍጠር ለተጎዱ ወገኖቻችን በአስቸኳይ መድረስ፤
6.
7. እስካሁን ያሉና ወደፊትም ሊከሰቱ የሚችሉ ሁነቶችን እግር በእግር እየተከታተሉ ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወቅታዊ መረጃን ማድረስ፤
8.
7. የዚህን ሀገራዊ ቀውስ ሙሉ ገፅታ የሚያሳይና ለቀጣይም የአስቸኳይ እርዳታና ዘላቂ የምርምር ስራዎች ግብአት በሚሆን ደረጃ፤ መረጃዎችን ሰብስቦ በሰነድ፣ በምስል፣ በድምፅ አጠናቅሮና ሰንዶ በአንድ የመረጃ ቋት ማዕከል ማስቀመጥ፤

በመሆኑም ቅድሚያ የተሰጠው ገንዘብ የማሰባሰብ ሥራ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡ ለዚሁ ዓላማም በተወከሉ ሰዎች ስም፡-

ሀ. ወ/ት ሜሮን አዲስ ገብረፃዲቅ ለ. ወ/ት መስከረም ያረጋል ማህተመ ሐ. አቶ ሀብታሙ ምናለ ፍሰሐ …… በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ የባንክ ሒሳብ ቁጥር (1000143645987) ተከፍቷል፡፡
ከዚህም በተጨማሪነት ኮሚቴውን በአመራርነት እንዲያገለግሉ ሰብሳቢ፣ ዋና ፀሐፊና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችን ምልዓተ-ጉባዔው መድቧል፡፡

Getachew Shiferaw's photo.

በዚህም መሰረት፡-
ሀ. ኤልያስ ገብሩ ጎዳና /ሰብሳቢ/ ለ. ኢዮኤል ፍሰሐ ዳምጤ /ዋና ፀሐፊ/
ሐ. አናንያ ሶሪ ጉታ /የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ/ ሆነው የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ተወስኗል፡፡
የምልዓተ-ጉባዔው አባላት ዝርዝር
1. ስለሺ ሐጎስ በርሔ
2. ሜሮን አዲስ ገብረፃዲቅ
3. ሐብታሙ ምናለ ፍሰሐ
4. ጋሻው መርሻ ይማም
5. በላይ ማናዬ ደመቀ
6. ዘሩባቤል ጌታቸው ዝቅአርጌ

7. ሰባህ ሙባረክ አወል
8. ጌታቸው ሽፈራው አንዳርጌ
9. ሮቤል አያሌው ሀይሌ
10. ኤልያስ ገብሩ ጎዳና
11. አናንያ ሶሪ ጉታ
12. ኢዮኤል ፍሰሐ ዳምጤ
13. መስከረም ያረጋል ማህተመ
በዚህ አጣዳፊ ‹‹ሀገራዊ ቀውስ›› የተነሳ ወገናችን የሆነው ኢትዮጵያዊ በየዕለቱ የሞትና የእርዛት አደጋን እየተጋፈጠ ነው፡፡ ከዚህ ቀውስ በአስቸኳይ ይወጣ ዘንድ ሁላችንም አለን በምንለው የሃሳብ፣ የገንዘብ፣ የቁሳቁስ፣ ወዘተ… ድጋፍ ልንረባረብ ይገባል! በመሆኑም ያላችሁን ማንኛውንም የመፍትሔ ሀሳብ በግልፅነት ታመላክቱን ዘንድ የዜግነት ድርሻችሁ ግድ ይላችኋል፡፡

አንድ ሆነን ለወገናችን እንድረስለት!!!

ሕዳር 04 ቀን 2008 ዓ.ም

4 Comments on “‹‹ቤዛ እንሁን!›› ወገን ተርቧል፤ እንድረስለት! የበጎ ፈቃደኝነት ኮሚቴ ተቋቋመ::”

  1. እኔ የምኖረው በሰሜን አሜሪካ ነው። የአገራችንን እጅግ ስር የሰደደ ችግር በዚህ ይፈታል ብየ ባላምንም መቶ US$100 dollar ባልገደደኝ እናንተ ግን ወያኔ ላለመሆናችሁ ወይንም virus ወያኔ እውስጣችሁ ላለመኖሩ ምን ማረጋገጫ ላግኝ ? ስለሽ ሐጎስ ያልችሁትስ የርዕዮት ዓለሙ እጮኛ ይሆን ? ገንዘቡንስ ወያኔ እንደማይቀማችሁ ምን ዋስትና አለ ?ወያኔ ዕራብ በአገሪቱ የለም የተቃዋሚዎች የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚያደርጉት የልማታዊ መንግስታችነን ስም ለማጥፋት ነው እያለ ነው። እውነተኞች ክሆናችሁ በጣም ይቅርታ።ይኽነን ያህል ነው ወያኔ እምነታችን የሸረሸርው።

  2. በኮሚቴው ላይ እምነት ካላደረብህና የመርዳት ፍላጎቱ ካለህ ሁለት ነገሮች ማድረግ የምትችል ይመስለኛል። አንዱና ቀላሉ መንገድ በምታምናቸው በቤተሰቦችህ በኩል ልከህ መርዳት ወይንም ደግሞ በታወቁት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንደ መቆዶንያ አይነቶች አገር በቀል ድርጅቶች በኩል መርዳት ትችላለህ። ዝም ከማለት ግን ትንሽ መለገስ ይሻላል። እኔ ግን እግዚአብሄር ፈቅዶልኝ አገር ቤት ሄጀ ሙሉ ጌዜየን ድኃ እየረዳሁበት ባሳልፈው ደስተኛ እሆናለሁ።

  3. ሳተናው አሊ
    የረሃብ ዋና ምክንያት ምንድን ነው?
    ዝናብ፣ወንዝ፣ደመና፣ምንጭ ሳይኖራቸው /የሌላቸው ሃገሮች ርሃብ የሚባል አያውቁትም ፡፡
    እኛ ግን ዝንታለም በሰዎች ስግብግበነት በምቀኝነት ወንዞች፣ሰራተኛ ሕዝብ እያለን ለምን ተራብን?
    ርሃብ አለ እንዴ በኢትዮጵያ? ረሃብ መኖሩን የሚነግሩን በዕዳን ናቸው
    የርሃቡ መንስኤ ስግብግብነት፣ሌብነት የምሁራን ስስታምነት ወዘተ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*