አቡጉዳ – መድረኩ ወደ ግንባር ተሸጋገረ
የኢትዮጵያ አንድነት ፌደራላዊ መድረክ (መድረክ) አባሉ በሆኑት ድርጅቶቹ መካከል ያለዉ መቀራረብና መተሳሰር የበለጠ በመጠናከሩ፣ ከ«ጥምረት» ወደ «ግንባርነት» መዘዋወሩን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። በዚህም መድረኩ፣ የዉስጥ አሰራሩን የበለጠ ወደ አንድነት በማምጣት፣ አባል ድርጅቶቹም አንድ ጽ/ቤት መጠቀም የሚችሉበትም ሁኔታ የተፈጠረ ሲሆን፣ በአመራር አባላቱ መካከልም ያለዉን መቀራረብና መተሳሰር የበለጠ ያሳድገዋል ተብሎም ይጠበቃል። መድረክ በኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ላይ […]