ዓለም አቀፉ የገንዘብና የልማት ተቁአም አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያ የገንዘብ ፖሊሲ በጣም ምስቅልቅሉ የወጣ ነው በማለት አጣጣለው

በያዝነው ጥቅምት ወር ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በይፋ ያመነው መረጃ እንደሚያመለክተው በሃገሪቱ እየታየ ያለው የገንዘብ ግሽበት መጠን አሁንም እያሻቀበ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ የምግብ ሸቀጦች ዋጋም እየናረ መሆኑ ታወቀ። ይሄው ሪፖርት እንደአመለከተው የገንዘብ ግሽበት መጠን ከ 40.1 በመቶ በላይ ሲሆን በምግብ ዋጋዎች ላይ ያለው የግሽበት መጠን ደግሞ 51 በመቶ መድረሱ ታውቁአል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለፈው መስከረም ወር የነበረው የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ  ሸቀጦች ዋጋ የ25 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቅሶአል።

የዋጋ ግሽበቱን በተለያዩ ክልሎች በመከፋፈል ያወጣው ይሄው ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ እጂግ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት የታየው በቤሻንጉል ጉምዝ ክልል እስከ 60 በመቶ በመድረስ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ የደቡብ ክልል፣ የጋምቤላ፣ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልሎች የክፍተኛ ዋጋ ግሽበት ሰለባዎች መሆናቸው ታውቁአል።  በአንጻሩ ዝቅተኛ ግሽበት ተከስቶባቸዋል የተባሉት ክልሎች ደግሞ አዲስ አበባ ድሬ ዳዋና የትግራይ ክልል መሆናቸውም ታውቁአል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ዓለም አቀፉ የገንዘብና የልማት ተቁአም በያዝነው ወር ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ የአምስት አመት እቅድ የተጋነነና ውጤታማ ለመሆኑም የሚያጠራጥር መሆኑን የገለጸ ሲሆን የዓለም ባንክም ተመሳሳይ የሆነ ሪፖርት አውጥቱአል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቁአም አይ ኤም ኤፍና ወርልድ ባንክ የዘጋቢዎቻቸውን ጥናት ዋቢ በማድረግ እንደገለጹት ኢትዮጵያ እየተከተለች ባለው የድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ የአምስት አመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ አስፈላጊውን መስፈርት ያላሙዋላ ነው ብለውታል።

የአምስት አመቱ የልማት ግቦች የተጋነኑና ሊሳኩ አይችሉም የሚሉባቸውን ነጥቦች የገንዘብ ተቋማቱ ዘርዝረው ያቀረቡ ሲሆን የዘራፊው መለስ መንግስት እየተከተለ ያለው ገንዘብን የመርጨት ፖሊሲ የገንዘብ ግሽበት በማስከተሉ፣ አደጋው በመጪዎቹ አምስት አመታት በተመሳሳይ ሁኔታ ሊቀጥል ይችላል ብለዋል።

በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ዙሪያ ያሉ በርካታ ማነቆዎችን የዘረዘሩት አይኤም ኤፍና የወርልድ ባንክ አጥኝዎች የወያኔው አገዛዝ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ጣልቃ ገብነት ቀንሶ የንግዱ ማህበረሰብ በስፋት እንዲሳተፉበት እንዲያደርግ መክሯል።  ሙስና ሌላው ችግር መሆኑን የጠቀሱት ተቋማቱ ዘረኛው አገዛዝ  ሙስናን ለመከላከል አቅጃለሁ ቢልም የመተግበሪያ መንገዱን ግን አላስቀመጠም ብለዋአል።

የዘረኛው አገዛዝ ቁንጮ አገኘሁት ለሚለው የኢኮኖሚ እድገት ሁሌም የአለማቀፍ የገንዘብ ድርጅቶችን በዋቢነት እንደሚጠቅስ የሚታወቅ ቢሆንም  ቀደም ብሎ አይ ኤም ኤፍ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚና ገንዘብ ፖሊሲ ላይ ይፋ ያደረገው አሉታዊ ሪፖርት የዘራፊዉን አገዛዝ ቁንጮ መለስ ዜናዊ እጂግ አበሳጭቶ እንደነበር አይዘነጋም።