ሽቅርቅር ቫንኩቨር፤ የውጭ ሀገር ኑሮና የኢትዮጵያ ተስፋ
አትክልት አሰፋ (ከቫንኩቨር ካናዳ)
ዛሬ ጠዋት በጣም ጠዋት 4 ሰእት ከ11
ገበሬው በጉን ለመሸጥ በግ ተራ ገብቷል። በግተራው ገዥና ሻጭ በርከት ብለው ይተራመሳሉ። በጉን ለመሸጥ ከቆመው ገበሬ ጋር የተጠጋው ገዥ ‘ስንት ናት’ ብሎ አንዷን በግ ይጎትትና ወገቧንም ይፈትሻል። በጓ ታስላለች። እንዴ ምንድነው? ይላል ገዥ ገበሬውን እያየ በመደናገጥ። ገበሬው ዝም ይላል። ከእንደገና ወገቧን ያዝ ያደርጋታል፤ ገዥ። አሁንም በጓ ታስላለች ‘ምን ሆና ነው ታስላለችሳ’ ይላል ገዥ። አሁንም ገበሬ ዝም ይላል። “አትናገርም እንዴ ያስላታል፤ አሟታል እንዴ?” ቢለው ገዥው: “መሆኑ ነዋ” አለ ገበሬው ጋቢውን ተከናንቦና ውሸት ላለመዋሸት ተጨናንቆ። የሚያስላትን በግ ቢችል ሊሸጥ ነበር ሀሳቡ አስተዳደጉ ውሸትን ስላላስተማረው ውሸቱን መቀላመድና አታሎ መሸጥ አልወደደም። እናም በጓን ለገበያ ቀርባለች፤ ግን ግን በጓ በገበያ ላይ አለችም የለችምም።