ዘረኛውና አረመኔው የወያኔ አገዛዝ የስዊድን ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ የታሰሩ ባልደረቦቻቸዉን ክስ በኢትዮጵያ ተገኝተዉ እንዳይከታተሉ ከለከለ

አፋኙና አረመኔው የወያኔ አገዛዝ ሽብርተኞች ናቺሁ በማለት ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞችን አስሮ እንደሚገኝ የሚታወስ ሲሆን የጋዜጠኞቹን የፍርድ ቤት ክስ ሂደት ለመከታተል ጥያቄ ያቀረቡትን የታሳሪ ጋዜጠኛ ባልደረቦች የወያኔው አገዛዝ ወደ ኢትዮጵያ እንደይገቡ መከልከሉ ታወቀ።

የሁለቱ ታሳሪ ጋዜጠኞች ማለትም ማርቲን ሺቤይ እና ጆሃን ፕርሰን ክስ የሚሰማዉ በመጪዉ ሳምንት ዉስጥ ኦክቶበር 18 ቀን መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ በችሎት ላይ ለመገኘት ቪዛ የጠየቁ የስዊድን የሬዲዮና የቴሌቪዢን ጋዜጠኞች እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ የመግቢያ ፈቃድ እንዳልተሰጣቸዉ ለማወቅ ተችሏል።

ሽብርተኞች ናችሁ በመባል ከታሰሩት ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች አንዱ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ዉስጥ ታስሮ እንደነበር ዘረኛው መለስ ለኖርዌይ የዜና አገልግሎት የገለጸ ቢሆንም የስዊድን ጋዜጠኞች ቃል አቀባይ የመለስ አባባል ትክክል እንዳልሆነ ተናግሩአል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በስዊድን የሚገኙ ጋዜጠኞች በስቶክሆልም የክሮኖ-በርግ እስር ቤት ዙሪያ በመገኘትና እጆቻቸዉን በማስተሳሰር የስዊድን መንግስት በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ እጂ ለወደቁት ለእስረኞቹ ትኩረት ይሰጥ ዘንድ ተቃዉሟቸዉን በሰላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል። ይህ ጋዜጠኞቹ የጀመሩት የተቃዉሞ ሰልፉ ሁለቱ ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት እስኪቀርቡ ድረስ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።

ኦላ ላርስሞ የተባሉት የስዊድን የፀሃፊዎች ማህበር ሊቀመንበር፤ ” የስዊድን ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ካልተፈቀደላቸዉ በጋዜጠኞቹ ላይ ምን ሊደርስ እንደሚችል አናዉቅም” በማለት ስጋታቸዉን ተናግረዋል።

ባለፈዉ አርብ በጉተንበርግ እና በስቶክሆልም የስዊድን ጋዜጠኞች በተመሳሳይ ሁኔታ መንግስት እስረኞቹን እንዲረዳ የጠየቁ ሲሆን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ጠ/ሚኒስትሩ መንግስታቸዉ አስፈላጊዉ ሁሉ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ መናገራቸውም ታውቁአል።

ሁለቱ ስዊድናዊያን ጋዜጠኞች ከኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር አማፅያን ጋር ከተያዙበት ከጁላይ አንድ ቀን ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

አሸባሪው የወያኔ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሽብርተኝነት ታፔላን በመለጠፍ በርካታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር አካላትንና አክቲቪስቶችን እንዲሁም በርካታ ጋዜጠኞችን ወደ እስር ቤት ማጎሩ ይታወቃል።