ዘረኛው መለስ ዜናዊ በኖርዌዬ ጉብኝቱ ”ስለምታደርጉልን የኢኮኖሚ እርዳታ እንጂ ስለሰብአዊ መብት ተቆርቋርነታችሁ ለመስማት ዝግጁ አይደለንም” ሲል ምዕራባዊያንን ማስጠንቀቁን በኖርዌይ የሚታተም አንድ ታዋቂ ጋዜጣ ዘገበ

አፍተን ፖስተን በመባል የሚታወቅ ዋንኛው የኖርዎይ ጋዜጣ ባለፈው ማክሰኞ እትሙ ይፋ እንዳደረገው ኖርዌይን ጎብኝቶ የተመለሰው ፋሽስቱ መለስ ዜናዊ ስለ ኢኮኖሚ እርዳታና የልማት ትብብር እንጂ በሰባዊ መብት አያያዝና በዲሞክራሲ ላይ ምንም አይነት አስተያየት ከምዕራባዊያኑ ለጋሾች ለመቀበል ፍቃደኛ እንዳልሆነ መናገሩን  ገለጸ።

በኖርዌይ አገር በተጠራው አለም አቀፍ ስብሰባ ከተጋበዙ መረዎች መካከል የስብሰባ አዳራሹን ያናወጠ የተቃውሞ ሰልፍ የተካሄደው በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ላይ ብቻ እንደነበር የገለጸው አፍተን ፖስተን ጋዜጣ፤ የኖርዌይ ጠቅላይ ምንስቴር ጃን ስቶልተንበርግና ውጪ ጉዳይ ኤሪክ ሶልህም፤ በእስር ላይ ስለሚገኙት ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች፤ በኦጋዴን ክልል እየተፈጸመ ስላለው ሰቆቃና በጸረ ሽብርተኝነት ዘመቻ ስም በቅርቡ ስለታሰሩት ከመቶ በላይ ጋዜጠኞች፤ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎቻቸው ጉዳይ ከአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ጋር እንደተነጋገሩ ተዘግቦአል።

መለስ ዜናዊ ኖርዎይ ባዘጋጀቺው በዚህ አለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ኦስሎ ከተማ በገባበት ያለፈው ዕሁድ ምሽት ለተሰብሳቢዎች ስለ ስብስባው ዝግጅት ማብራሪያ በተሰጠበት ሆቴል ፊት ለፊትና በማግስቱ ሰኞ ከተደረገ ስብሰባ አዳራሹ ፍቲ ለፊት በተደረገው ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ መለስ ዜናዊ ደረቱን ቀና አድርጎ አንዳይራመድ በመደረጉ፤ የኖርዌይ መንግሥት ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ እንኳ ለመገኘት ድፍረት ሳያገኝ እንደቀረ ተዘግቦአል።

የኢትዮጵያን ባንድራ ጨርቅ ነው በማለትና ታሪኳንም በማንቋሸሽ “ምንሊክ በወረራ የፈጠሯት አገር ነች” ሲል የነበረው መለስ ዜናዊ፤  ለአፍተን ፖስተን ጋዜጣ በሰጠው ቃለመጠይቅ አገራችን ቅኝ ያልተገዛች ነጻ አገር ስለሆነች ስለ ስብአዊ መብትና ዲሞክራሲ የሚሰብኩ የውጭ አገር መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አያስፈልጉንም ማለቱ ብዙዎችን ኢትዮጵያዊያንን አስገርሞአል።

ቀደም ሲል የምዕራባዊያን እርዳታና ድጋፍ እንዳይቀርበት የመድበለ ፓርቲ ሥርአት እየተከተለና በሂዴት እየጎለበተ የሚሄድ ዲሞክራሲ በአገሪቱ እንደዘረጋ በልበሙሉነት ይናገር የነበረው የወያኔው ቁንጮ መለስ ዜናዊ፤ በዚህ የኦስሎ ጉብኘቱ ተስፋ የቆረጠ በሚመስልበት አነጋገር በአገራችን ፖለቲካ ጉዳይ አትግቡብን ሲል መናገሩ ፈረንጆቹንም ጭምር እንዳስገረመ ለማወቅ ተችሎአል።

በኖርዌይው ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገኘው ህዝብ የአረመኔው መለስ ዜናዊን ወደስብሰባ አዳራሽ ማምራት በርቀት በተመለከተ ጊዜ ቁጣው ፈንቅሎትና ለሰልፍም የተፈቀደለትን ቦታ በመጣስ ወደ መለስ ዜናዊ የመገስገስ ሙከራ በማድረጉ ሥነሥር ዓት ለማስከበር በቦታው ከነበሩት የኖርዌዬ ፖሊሶች ጋር ተጋጭቶ እንደነበርና በዚህም የተነሳ ሶስት ኢትዮጵያዊያንን ለተወሰኑ ሰአታት ታስረው መለቀቃቸው መግለጻችን ይታወሳል።

ይህ በዚህ እንዳለ መለስ ዜናዊ በኖርዎይ ለስብሰባ መገኘቱን ለመቃወም ከስዊድን ሃገር የተንቀስቃቀሰው ግብረሃይል ተወካዮች በውጪ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የዘረኛው አገዛዝ ነጋዴ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ ወደውጪ ሃገራት የሚልኩአቸውን ማናቸውንም ሸቀጦችና ልዩ ልዩ ባህላዊ ምግቦች በውጪ ሃገራት ከሚገኙ የወያኔ ተባባሪ ነጋዴዎች ግዢ እንዳይፈጽሙ በማለት ጥሪ አቀረቡ። የግብረሃይሉ ተወካዮች ይህንን ጥሪ ያቀረቡት ባለፈው ሰኞ በኖርዎይና አካባቢዋ የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን  ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደሆነም ዘጋቢያችን ከኦስሎ ኖርዎይ ባስተላለፈልን ዘገባ አመልክቱአል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ባሁኑ ሰአት በቀን አንዴ መብላት ተስኖት ይገኛል ያሉት በኖርዎይና አካባቢዋ የሚገኙት ኢትዮጵያዋኢያን፤ ህዝባችን የሚበላ ነገር አጥቶ በሚሰቃይበት በዚህን ሰ ዓት የፋሽስቱ አገዛዝ ባልስልጣናትና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ትርፍ ለማጋበስ ሲሉ ለአገር ውስጥ ፍጆታ ያልበቃውን ጤፍ እንጀራ፣ በርበሬ፣ ሽሮ፣ የመሳሰሉትን መሰረታዊ ምርቶች በገፍ  ወደ ውጪ ሃገራት እየላኩ ነው ስለዚህም መፍተሄው ወጪ ያለነው እንዚህን መርቶች አንጠቀምም ማለት ብቻ ነው ብሎዋል።

ከስዊድን ወደ ኖርዎይ የተንቀሳቀሱት እኚሁ የግብረሃይሉ ተወካዮች ከምግብ ሸቀጦች ባሻገርም፣ ባህላዊ ልብሶችንና ጫማዎችን፣ ጌጣ ጌጦችን በአጠቃላይ በዘረኛው አገዛዝ የንግድ ድርጂቶችና ግለሰቦች አማካኝነት ከኢትዮጵያ ወደ ውጪ ሃገራት የሚላኩ ምርቶችን ባለመግዛት በንግድ ዘርፉ የተሰማሩ የወያኔ ኢህ አዴግ ባለስልጣናትን ኢኮኖሚ ማቀዝቀዝ እንደሚገባው በአንክሮ ገልጸዋል።

ቀደም ብሎ በምርጫ 97 ወቅት የቅንጂትን አሸናፊነት ዘረኛው የወያኔ  አገዛዝ ውድቅ ባደረገበት ወቅት የቅንጂት መሪዎች የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔ ኢህአዴግ ምርቶችን እንዳይገዛ ምክር ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።